>

ምኒልክን እንጠላለን ርስቱን ግን እንወዳለን ማለት አያዋጣም! (አቻምየለህ ታምሩ)

ምኒልክን እንጠላለን ርስቱን ግን እንወዳለን ማለት አያዋጣም!
አቻምየለህ ታምሩ
ሰማዩንም ምድሩንም የኛ ነው የሚሉት ኦነጋውያን እሹሩሩ ማለቱ ማብቃት አለበት። «ዳግማዊ ምኒልክን ውደዱ፣ ኢትዮጵያዊ ናችሁ፣ የጋራ ታሪክ አለን» እያሉ ማላዘኑ ምንም ፋይዳ ያለውም። «ዳግማዊ ምኒልክን እንጠላለን» ፣ « እንደ ኢትዮጵያ የጋራ ታሪክ የለንም» ወዘተ…ሲሉ  እንደዚህ ካላችሁ «በወረራ የያዛችሁትን የዳግማዊ ምኒልክ ርስትም አብራችሁ ጥሉ»፣ «የኢትዮጵያን ታሪክ ከጠላችሁ አገራችሁ ኢትዮጵያ አይደለም» ሊባሉ ይገባል።
ኦሮምያ የሚባለው በኢትዮጵያ እምብርት ላይ የበቀለው እባጭ የሚያካልለው  ምድር ኦሮሞ ወረራ ከመጀመሩ ከ1522 ዓ.ም. በፊት የኢትዮጵያ ክፍልና የዳግማዊ ምኒልክ አባቶች ርስት ነበር። ኦሮሞ በዚህ የኢትዮጵያ ክፍል እንደ ዋርካ የተንሰራፋው ከ1522 ዓ.ም. ጀመሮ በየስምንት ዓመቱ በአባዱላ እየተመራ ባካሄደው ወረራ የዐፄ ምኒልክ አባቶችን አጥፍቶ፣ ማንነታቸውን ቀይሮ፣ የዘር ማጥፋት አካሂዶና ከርስታቸው አፍልሶ ነው። ኦሮሞ የዐፄ ምኒልክ ን አያቶች ርስት ሁላ በመውረር  እንደተንሰራፋ  ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ጀምሮ ያለውን የኢትዮጵያ ነገሥታት ትውልድ ታሪክ  ወስጄ እንደሚከተለው አስረዳለሁ።
ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ  ከምድር ወገብ ሶስት ዲግሪ እስከ አስራ ስምንት ዲግሪ፤ ከግሪንዊች ሜሪዲያን አስራ ሶስት እስከ አርባ ስምንት በመለስ የነበረውን  የኢትዮጵያ  መሬት ከ1314-1344 ዓ.ም.  ያስተዳደሩት የዐፄ  ዐምደ ጽዮን የልጅ ልጅ ናቸው። ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ከ1426 – 1460 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት ናቸው። ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የተወለዱት ከአባታቸው ከዐፄ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግሥት ክብረ እግዚ በ1391 ዓ.ም. ሲሆን የተወለዱት ከአዋሽ ወንዝ አጠገብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው ቦታ ፈጠጋር አውራጃ ውስጥ ነው። ፈጠጋር ከኦሮሞ ወረራ በኋላ የጥንት ስሙ ተቀይሮ አርሲ ተብሏል። የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ እናት ንግሥት ክብረ እግዚ የፈጠጋር  ባላባት ልጅ ናቸው።
ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ በኋላ ኢትዮጵያን ከ1460-1470 ዓ.ም. ያስተዳደሩት ልጃቸው ዐፄ በእደ ማርያም ናቸው። ዐፄ በእደ ማርያም የተወለዱት በ1440 ዓ.ም. ሲሆን እናታቸው እቴጌ ጽዮን ሞገሷ የደዋሮ ገዢ የነበሩት የጋራድ አሕመድ ልጅ ናቸው። ደዋሮ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ የጥንት ስሙ ተቀይሮ ምዕራብ ሐረርጌ ሆኗል።ከዐፄ በእደ ማርያም በኋላ ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት የመጀመሪያ ልጃቸው ዐፄ እስክንድር ናቸው። ዐፄ እስክንድር ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት ከ1471-1487 ዓ.ም. ሲሆን እናታቸው ንግሥት ኢሌኒ የደዋሮ ጋራድ ልጅ ናቸው። ዐፄ እስክንድር ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ ኢትዮጵያን ማስተዳደር የጀመሩት ወንድማቸውና ሁለተኛው የዐፄ በእደ ማርያም ልጅ የሆኑት ዐፄ ናዖድ ናቸው። ዐፄ ናዖድ ኢትዮጵያን የገዙት ከ1486-1500 ዓ.ም. ሲሆን እናታቸው የዳዋሮ ገዢ  ልጅ የሆኑት እቴጌ ናዖድ ሞገሷ ናቸው። ከዐፄ ናዖድ በኋላ የነገሡት ዐፄ ልብነ ድንግል ሲሆኑ ኢትዮጵያን ከ1501-1532 ዓ.ም. ገዝተዋል።
ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ጀምሮ እስከ ዐፄ ልብነ ድንግል ያሉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ሁሉ ትውልዳቸው ከደዋሮ [ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ምስራቅ ሐረርጌ የሆነው] እና ከፈጠጋር [ከኦሮሞ ወረራ በኋላ አርሲ የሆነው] ይሳባል። ይህ ማለት ቀደም ብዬ ለዘረዘርኳቸው የኢትዮጵያ ነገሥታት ደዋሮ[ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ምስራቅ ሐረርጌ የሆነው] እና ፈጠጋር [ከኦሮሞ ወረራ በኋላ አርሲ የሆነው] ያባቶታቸው ርስት ነው ማለት ነው። ደዋሮና ፈጠጋር ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ጀምሮ እስከ ዐፄ ልብነ ድንግል  ድረስ ያሉት የኢትዮጵያ ነገሥታት አባቶች ርስት በነበረበት ወቅት ኦሮሞ ገና የገዳ ስርዓትና ወረራ አልጀመረም ነበር።
እንቀጥል! ዐፄ ልብነ ድንግል ከወለዷቸው ልጆች መካከል የመጨረሻው ልጃቸው አቤቶሁን ያዕቆብ  ይባላሉ። አቤቶሁን ያዕቆብ አቤቶሁን ሥርወ ቃልን የወለዱ ሲሆን አቤቶሁን ሥርወ ቃል ደግሞ  ነጋሲን ወልደዋል። አቤቶሁን ነጋሲ ሥርዎ ቃል  በኢማም  አሕመድ ጦርነት የተለያዩትን
የደቡቡን የነዐፄ ልብነ ድንግል አባቶች ርስት ከሰሜኑ  የኢትዮጵያ ክፍል ጋር  ወደቀድሞው አንድነቱ ለማምጣት በዶቃቂት  የተቋቋመው የሸዋ  ስርዎ መንግሥት መስራች ናቸው። ከአቤቶሁን ነጋሲ በኋላ ሸዋ የተመሰረተውን  ስርዎ መንግሥት የመሩት  ልጃቸው አቤቶሁን አብዬ ናቸው።
ከአቤቶ ሁን በኋላ  የገዙት ልጃቸው መርድ አዝማች አምሐ ኢየሱስ ናቸው። ከአምሐ ኢየሱስ በኋላ ግራኝ ያጠፋቸውን የኢትዮጵያ ክፍሎች ለማቅናት ሸዋ ላይ የተመሰረተው ሥርዎ መንግሥት መሪ  ልጃቸው አስፋው ወሰን ናቸው። ከመርድ አዝማች አስፋው ወሰን በኋላ ሸዋን የገዙት ልጃቸው መርድ አዝማች ወሰን ሰገድ ናቸው። ከመርድ አዝማች ወሰን ሰገድ በኋላ ሸዋንና  የተቀሩትን ኦሮሞ የወረራቸውን  የነዐፄ ልብነ ድንግል አባቶች ርስት በማስመለ  የገዙት ልጃቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ናቸው። ከንጉሥ ሣህለ ሥላሴ በኋላ  በስርዎ መንግሥቱ የተሾሙት ልጃቸው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ናቸው። ከንጉሥ ኃይለ መለኮት በኋላ ሸዋን [ከዐፄ ቴዎድሮስ ቤተ መንግሥት ከወጡ በኋላ] እና   የአባቶቻቸው የነዐፄ ልብነ ድንግል ርስት የሆነውን የዛሬውን ኢትዮጵያ ምድር  ያስተዳደሩት ልጃቸው ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ናቸው።
ከፍ ብዬ ከዘረዘርሁት እንደተመለከተው ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ትውልዳቸው ከዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ ከአቤቶ ያዕቆብ ይመዘዛል። ከዐፄ ልብነ ድንግል ደግሞ ትውልዳቸው ከደዋሮ [ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ምስራቅ ሐረርጌ የሆነው]፣ ከሐድያ [የዛሬውን ባሌ በከፊል ያካትታል] እና ከፈጠጋር [ከኦሮሞ ወረራ በኋላ አርሲ የሆነው] እንደሆነ ተመልክተናል። ይህ ማለት  ኦሮሞ ነባሩን ሕዝብ አፍልሶ የያዘው ደዋሮና ፈጠጋር የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አባቶች ርስትና ቅድመ አያቶቻቸው የተወለዱባቸውና የወለዱባቸው አውራጃዎች ነበሩ ማለት ነው። ለዚህም ነበር  ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክም  ሆነ ከሳቸው በፊት የነበሩት በግራኝ  አሕመድ ጦርነት የተለያዩትን  የደቡቡን የነዐፄ ልብነ ድንግል አባቶች ርስት ከሰሜኑ  የኢትዮጵያ ክፍል ጋር  ወደቀድሞው አንድነቱ ለማምጣት በሸዋ የተቋቋመው ስርዎ መንግሥት መሪዎች ሁሉ ወደ ደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል ማለትም ወደ ሐረርጌ፣ አርሲና ባሌ ሲዘምቱ «የአባቶቼን አገር ላስመልስ ነው» ይሉ የነበረው።
እንግዲህ! ዐፄ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች ከቦረና ተነስተው የወረሯቸውንና እንደ ዋርካ ተስፋፍተው የያዟቸውን የዳግማዊ ምኒልክ አያቶች ርስትና አውራጃዎች የሆኑትን እነ ደዋሮን፣ባሊን፣ ፈጠጋር፣፥ ቢዛሞን፣ እናርያንና የጥንቱን ዳሞትን  አብረው መጥላት አለባቸው። «ወንድ እወዳለሁ፤ ግን ጭኔን ያመኛል» እንዳለችው አይነት ግራ ገባት ሴት አይነት ምርጫ አይሰራም። ኦነጋዊ  ሁሉ ዳግማዊ ምኒልክን እንዲወድ አይገደድም። ዳግማዊ ምኒልክን የሚጠላ ግን የዳግማዊ ምኒልክን ርስት መልቀቅና ወደመጣበት ወደ ቦረና መሄድ አለበት። የኢትዮጵያን ታሪክ የሚጠላ አዎ አገርህ ኢትዮጵያ አይደለችም፤ ስለሆነም የጋራ ታሪክ የለንም።
ባጭሩ ዳግማዊ ምኒልክን እንጠላለን እያሉ የዳግማዊ ምኒልክን ርስት ግን እንወዳለን ብሎ ነገር የለም! ዳግማዊ ምኒልክን እንደጠላህ  ሁሉ በገዳ ተደራጅተህ በየስምንቱ ዓመቱ እየወረርህ የያዝኸውን  የዳግማዊ ምኒልክን ርስትም ጥላና  በወረራ ይዘህ  እስካሁን ለተጠቀምህበት  አፈላማህን  ከፍለህ ምድሩን  ላፈለስሀቸው ለባለቤቶቹ ለቀህ ወደ ቦረናህ ግባ! ምኒልክን ጠልተህ በምኒልክ ርስት ላይ ምን ትሰራለህ?!
Filed in: Amharic