>

ልቅና መቋጫ ያጣው የዘር ብሔርተኞችና ጎሰኞች ኢትዮጵያን የማተራመስና የመበታተን አባዜ መሠረታዊ ምክንያቶች (አጭር ጥናታዊ ፅሁፍ - ግርማ ብርሃኑ, PhD)


ልቅና መቋጫ ያጣው የዘር ብሔርተኞችና ጎሰኞች ኢትዮጵያን የማተራመስና የመበታተን አባዜ መሠረታዊ ምክንያቶች

 

(አጭር ጥናታዊ ፅሁፍግርማ ብርሃኑ, PhD)

 

Girma Berhanu, PhD
Professor,
Department of Education and Special Education,
University of Gothenburg
Box 300, 40530 Göteborg
Sweden
E-mail: girma.berhanu@ped.gu.se

 

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ እንደ ሀገር በመቀጠል ረገድ በሠመረ በዳበረና ፀንቶ በቆየ ሉዓላዊነቷ ላይ የተጋረጠ ወይም ያጠላ አስተማማኝ ያልሆነ አስጊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ በወቅቱ ያሉት እሳቤዎችና መዋቀራዊ ማስተካከያዎች እና ተቋማዊ መሠረቶች ዋንኛ የአሃዳዊ ኢትዮጵያ ብሔራዊነት(Pan Ethiopian Nationalism) መሰናክሎች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ እነዚህም በኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ግንባር/የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ኢህአዴግ/ህወሃት)[1]  የተወጠኑና ጎሣን መሠረት አድርገው የተፈጠሩ የፖለቲካ ሃይሎች እኩይነት ያስከተለው ጥፋት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ህወሃት ከጨወታ ውጪ ሆኗል፡፡ የኦሮሞ ብሔርተኞች ደግሞ መድረኩን ይዘውታል፡፡ እኛ እንደምንለውም አዲስ ኣይነት የጎሣ ትምክህት ወይም አጉራ ዘለልነት ጠንቅ ሃገሪቷን እንደቀድሞዋ ዩጎዝላቪያና[2] በመሳሰሉት ሀገራት እንደታየው ወደ አርስ በርስ ጦርነትና መከፋፈል እያመራች ነው፡፡  የጎሣ ጥላቻ በተመላበት ሁኔታ የተደቀነው ሥጋት አደገኛና ጨፍጋጋ መፃዔን ያረገዘ ነው፡፡

ዜጋን መሠረት ያደረገ ፖለቲካ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ባለ ብዝሃ ባህል ሀገራት ተመራጭ አካሄድ እንደሆነ በምርምሮች ማጠቃለያ ላይ የሚበረታታ ጉዳይ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ታዬ (Taye , 2017)[3] በትክክል እንዳስቀመጠው ይህን ሥራታዊ ህመም ለማከም መንግሥት ብዝህነትንና በኢትዮጵያ ያለውን ጎሣዊ ፌደራል አወቃቀርን ለፖለቲካዊ ማራመጃ  መጠቀሙን አቁሞ ጉዳዩ የከፋ መልክ ከመያዙ በፊት በአፋጣኝ እንደገና መመርመር አለበት፡፡ ዘር ተኮርና ጎሣዊ ያልሆነ፣ መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ መመስረት ብቸኛ አማራጭ፣  በትክክል የሚሰራና ያለውን ዓይነተኛ የግጭት መንስዔ በማጤን የመረጋጋት ዋስትና፣ ፍትሃዊነትና ኢኮኖሚ ልማትን የሚያስተናግድ ነው፡፡ ቢራራ(2019) እንዳስቀመጠው በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚወደሱት፣ የሚከበሩትና የሚመለኩት በኢህአዴግ ጊዜ ከተወለዱት ኢትዮጵያውያን ይልቅ በጃማይካኖችና በሌሎች በካሪብያን በሚኖሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም በተለያየ አህጉራት በሚኖሩ ራስተፈሪያውያን ዘንድ ነው፡፡ ህወሃትና ኦነግ እንዲሁም ሌሎች የጎሣ ግንባሮች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያዊነትን የሚያጣጥል ተግባራትን ባለፉት 40 ዓመታት ሆን ብለውና በተቀነባበረ መልኩ እያራመዱ ይገኛሉ፡፡ 

መረጃው በሚገባ ያላቸው በሁሉም ሂደት ያለፉ  ምሁራን በተደጋጋሚ ጊዜ እንደሚያስጠነቅቁት በመሠረተ-ጎሣ ፖለቲከኞች ዕብደት  የኢትዮጵያን በጎ የብዝህነት ገጽታ፣ ለረጂም ጊዜ የቆየውን የህዝቧን አንድነትና[4] መሥተጋብር ለጎጂ ፖለቲካቸው በማዋል የተዘፈቁ ናቸው፡፡ 

በዚህ አጭር ጽሁፍ ኢትዮጲያን ለመበታተን አንድ አንድ ቡድኖች ወይም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነን ተብዬዎች  ያላቸውን ምክንያትና ጥልቅ ፍላጎት እንዲሁም የችግሩን አሳሳቢነት ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች እንደ ማሽን ጥርሶች የተያያዙ በመሆናቸው ሁሉም በመደጋገፍ በተመሣሣይ ጊዜ የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ማስገንዘብ የምፈልገው በዚህች ጥንታዊ ሀገር አንድነት፣ ህልውናና ክብር  ላይ ያንዣበበው አደጋ የሚመዘዘው ከሚከተሉት የተቆላለፉ ምክንያቶች ወይም መንስዔዎች ሲሆን እነርሱም ድንቁርና፣ ጭፍንነት፣ የአመለካከት ግርዶሽ፣ ራስን ማካበድ፣ የላሸቀ ማህበራዊ ንቃት፣ የማንነት ዝቅጠት፣ የበታችነት ስሜት አስተሳሰብ ዝንባሌ፣ አቅልንና የአዕምሯችንን ተግባር የሚነኩ ስሜቶችና ግልጽ ባህሪያት፣ ሌሎች  ሥነልቦናዊና የግል ምክንያቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ምክንያቶች እንዴት ማሰብ እንዳለብን ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉና፣ በሂደትም የዕለታዊ ሕይወታችንን ውሳኔዎቻችና ግንኙነቶታችንን የሚነኩ ናቸው፡፡ ግለ-ሃሳቡ ጠለቅ ያለ ትንተና እና ሰፋ ያለ የምልከታ ጭብጥ ይፈልጋል፡፡ ለአሁኑ ግለ-ሃሳቡን አስመልክቶ ብሩህ ለማድረግ እንዲረዳ አርቆ አስተዋዩን ፈላስፋ ዶክተር ተድላ ገ. ወልደዮሃንስን መጥቀስ ይበቃል፡፡ 

የኦሮሞ ብሔርተኞች – ኦባንግ ኦሜቶን ተመልከቱ – ሌሌች ኢትዮጵያውያን አሱን በሚሉት አሉታዊ መንገድ ላይ ተመስርቶ ፖለቲካን አያራምድም፡፡ የሱ ፖለቲካ እንደ ማንኛውም ሰውና ኢትዮጵያዊ በሚቻለውና ማድረግ በሚገባን ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ኦሮሞዎችን በሚያንቋሽሹ ቃላት ቢጠሯቸው ይህም ማለት ከማናቸውም ጎሳ በሆነ ሌላ ሰው ላይ ሊሰነዘር የሚችለው ዓይነት ቢሆንም በምክንያትነት ተወስዶ የኦሮሞ ብሔርተኞች ተብዬዎች በቅሬታ ፖለቲካ ላይ ተመስርተው ንቅናቄ ሲመሰርቱ ኦባንግ ሜቶ ግን እንዲህ ዓይነቱን ነገር አላደረገም፡፡ ከኦባንግ ሜቶ ተማሩና ማልቀስ አቁሙ፡፡ እናንት ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ከዚህ ቀደም ት/ቤት ደጃፍ መርገጥ ካልቻለው ህብረተብ የተሸለ ነገር ማድረግ ካልቻላችሁ የመማራችሁ ፋይዳ ምኑ ላይ ነው?የኦሮሞ ብሔርተኞች ስለናንተ አፈርን! (Personal communication, 2019)

ለመርትኦዎቼ መሠረት የሆኑኝን ጽንሰሃሳቦችና አሳማኝ ጭብጦችን በቀጣዩ የምርምር ጽሁፌ በዝርዝር አስረዳለሁ፡፡ በዚህኛው ጽሁፌ ግን የኢትዮጵያን ሉዐላዊነትና አንድነት ላይ ሥጋት የደቀኑትን ዋና ዋና ነጥቦች አስቀምጣለሁ፡፡ እነዚህን ነጥቦች አንድ የሚያደርጋቸው የውሸት ትርክት[5] ድርድሮች፣ ውዥንብሮችና “ቁንጽል ዕውቀትን¨ ጨምሮ የግል ሁኔታዎች መሆናቸው ነው፡፡ የአሜሪካን የሥነልቦና ማህበር ግብረሃይል በተሰጠው ትርጉም ዕውቀት ማለት ውስብስብ ሃሳቦችን መረዳት፣ ከአካባቢ ጋር በብቃት መዋሃድ፣ ከልምድ መማር፣ በብዙ የምክንያዊነት ዓይነቶች መሳተፍ፣ ከአስተሳሰብ በመነሳት መሰናክሎችን መወጣት መቻል ማለት ነው (Neisser, 1996, ገፅ.1)[6]፡፡ ይህን ስል ግን በተለመደው የአዕምሮ ልቀት እካሄድ ታሳቢ በሆኑ የሥነ-ልቦና መለኪያዎች ውስጥ ጠለቅ ብዬ መግባት አልፈልግም፡፡ ሆኖም ግን ባለፉት 20  እና ከዚያም በላይ ዓመታት ዘርን መሠረት ያደረጉ ፖለቲከኞች/ጠባብ ብሔርተኞችን ስብእናን በተመለከተ  በጥንቃቄ በተሰጡ ትንታኔዎች የታዘብኩት የተለመደ ነገር ቢኖር ከሁለቱም ማለትም ከታሪካዊና ወቅታዊ ሁኔታዎች መማር እንደማይፈልጉ ነው፤ የነሱ እንቅስቃሴ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ከግምት ውስጥ እንደማያስገቡም ነው፡፡ ከሀገርና መንግሥት ግንባታ ጋር ተያይዞ ያለውን ውስብስብ ሁኔታ፣ በሰላም አብረው በሚኖሩ ጎሳዎች መካከል ጥላቻን መፍጠርና ብጥብጥ ማስነሳት የሚያስከትለውን ጣጣ አይረዱም፡፡

ፕሮፌሰር ጎርደን ሃድሰንና[7] የሥራ ጓዶቻቸው አላዋቂነት/ቁንጽል ዕውቀት፣ በጥላቻ የተመላ ዕምነትና ማህበራዊ ወግ አጥባቂ ፖለቲካን አስመልክተው በርካታ ጽሁፎችን አዘጋጅተዋል፡፡ 

ግኝቶቻቸውም የዙሪያ ጥምጥሙ መረጃዎችን የሚመለከቱ ናቸው፡-ቁንጽል ዕወቀት ያላቸው ሰዎች ለውጥን የሚያጨናግፍ በአጸፋውም ጭፍንና አንድን ዘር ወደ ሚያስበልጥ[8] ማህበራዊ ወግ አጥባቂ  አመለካከት ያጋድላሉ፣ ዝቅተኛ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ለምን በከፋፋይና ወግ አጥባቂ ርዕዮቶች ውስጥ ይሰምጣሉ? ምክንያቱም እንደዚህ ዓይነት ርዕዮቶች በባህሪያቸው ውስብስቡ ዓለም ውስጥ በቀላሉ መግባት የሚያስችሉ አወቃቀርና ሥርአት  ስላላቸው ነው፡፡ 

ለመሆኑ ዘር አበላላጮች፣ ጠባብ ብሔርተኞችና ዘረኞች ደደብ ናቸውን? የአሁን ጊዜ ምርምሮች  እንደሚነግሩን ለሁለቱም ጥያቄዎች የሚመጥነው ምላሽ አዎ[9] የሚለው ነው፡፡ 

አክሎግ ቢራራ (July 28, 2019) በትክክል እንዳስቀመጠው ግዙፍ ውሸቶች፣ አላዋቂነት[10]፣ የተዛቡ መረጃዎችና ሃሰተኛ ትርክቶች በአማራዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን አስከትለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግራ ሃይሎችና የዘር-ብሔርተኞች በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ/ህወሃት) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ) ለግማሽ ምዕት  ዓመታት አማራን ትምክህተኛ፣ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና ህዝቦች ጨቋኝ ፣ በዥባዥና ጨካኝ አድረገው ሲቀሰቅሱ ኖረዋል፡፡ ይህ ፈጽሞ የወረደና ሃሰተኛ ትረካ በትምህርት ቤቶችም ጥላውን አጥልቶ ዛሬ በዕድሜያቸው የበሰሉ ወጣቶች ጥላቻን፣ ጥርጣሬንና ስም ማጥፋትን እንዲያራምዱ፣ በአንድ አንድ ሁኔታዎች ደግሞ በአማራዎች ላይ ግድያና እስራት እንዲፈጸም አድርጓል፡፡ በመሠረቱ አማሮች እንደ ህዝብ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደሉም፡፡ 

ሃይሌ ላሬቦ[11]  የኢትዮጵያን ታሪክ ማዛባትና ማጥላላትን በተመለከተ ለኦሮሞ ምሁራን የምሰጠው ምላሽ በሚለው ጽሁፉቸው ላይ በትክክል እንዳስቀመጡት ለእነዚህ የተማሩግለሰቦች የምሰጠው የመጨረሻ ምክር ቢኖር በራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ምክንያት መርዘኛ ወሬ ከሚነዙ ይልቅ ለርሱ/ለርሷ የዘር ምንጭ፣ ሃይማኖት ወይም ቋንቋ፣ ትውልድና ማንነት ቦታ ባለመስጠት እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በሁለንተናዊው ለማብቃት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ በቃ ትምህርት ማለትም ይኸው ነው! የኢትዮጵያ ጠላቶች ድህነት፣ መሃይምነት፣ በሽታና ድንቁርና ናቸው እንጂ እናንተ እንደምታስቡት ሚኒሊክ ወይም አማራ አይደለም፡፡ በፍሬ ከርስኪና ዕርባና ለሌለው ፖለቲካ ህዝብን በመከፋፈል ጊዜያችሁን ከምታጠፉ ይልቅ የህዝቡን መከራና የሞት መጠን በጠንካራ ሥራ የማቃለል ዓላማ አንግባችሁ ጊዜያችሁን በቁም ነገር ላይ ማዋል ይጠበቅባችኋል፡፡  አድናቆታችሁን ስጡም አትስጡም ሚኒሊክ ጽኑ መሠረት ጥሎ ማለፉ ሃቅ ነው፡- ማንኛችንም በየትኛውም የዓለም ክፍል አንገታችንን አቅንተን በአይበገሬ የራስ መተማመን መንፈስ እንድንቀሳቀስ ያስቻለንን ኩራት አጎናጽፎናል፡፡

አክሎግ ቢራራ(July 28, 2019) በተጨማሪ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የበላይነትና በተለጣፊው የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) ተባባሪነት እንደ እ. ኤ. አ. በ1991 ሲመሠረትም ሆነ፤ ቋንቋና ዘር መሠረት ያደረገው ህገመንግሥትም  እ. ኤ. አ. በ1994 ሲረቀቅ አማራን በማግለል መሆኑን ጠቅሷል፡፡ 

 

በጊዜው ከኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ውሰጥ የአማራ ህዝብ ቁጥር አብላጫ ነበረው፡፡ አማራን ማግለል የሚያረጋግጥልን ጉዳይ ቢኖር ግራ ዘመሞች፣ የውጭ ሃይሎችና[12] የብሔር ግንባሮች ርዕዮተዓለማዊና ፖለቲካዊ ትረካ ሃሰት መሆኑን ነው፡፡ 

ኢትዮጵያ የባህር በሮቿን ያጣችውም በዘር ጥላቻና በሀሰተኛ ትረካ ነው፡፡ በመቀጠልም ሃይ ባይ ባጣና ባልተገታ መልኩ[13] ሰብአዊነት ላይ ያነጣጠሩ አሰቃቂ ወንጀሎች አማራ ላይ ተፈጽመዋል፡፡ ሁለቱም ማለትም የትግራይ ዘረኞችና የኦሮሞ አክራሪ ብሔርተኞች የፀረ-አማራነት ስሜትንና አያይዘውም ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን በማራመድ የአማራን ህዝብና ሌሎች ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያንን (አንድ ኢትዮጵያዊነትን) ቀንደኛ ጠላቶቻቸው አድርገዋቸዋል፡፡ 

ጥላቻ፣ ወራዳ ምግባሮችና እና መሠረተ ቢስ ትረካዎች ሀገሪቷን ለመበታተን አስቀድመው በመሣሪያነት በሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ሁለቱም የቅኝ ግዛት ሃይሎች ማለትም ሃሳዊ-ታሪክ ፀሃፊዎችና ሚስዮናውያን አማራን ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ጋር ለማጋጨት ቀደም ሲል የነበሩ ጥቃቅን ሁኔታዎችን በማባበስ የጎሣ ግጭቶችን ያስተዋወቁበትን መንገድ በመንቀፍ ረገድ እጅጉን ቀጥተኛና የማናወላውል መሆን አለብን፡፡ 

የሩዋንዳ ድህረ-ቅኝ ግዛት የጎሳዎች ደም መቃባት የተቀሰቀሰው ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ ጥላቻ ሳይሆን እ. ኤ. አ.  በ1900 እና በ1960 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ቅኝ ገዢዎች ሆን ብለው የሸረቡት ሴራ ነው፡፡ የሩዋንዳ ካቶሊክ መሪዎች ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር  በአስፈላጊነታቸው ሲለዋወጡ የነበሩ ማህበራዊ ሁኔታዎችን ወደ ማይለወጡ የዘር ማንነቶች ለመቀየር የባንያሩዋንዳን ማህበረሰብ በመከፋፈል የሁቱ-ቱትሲ ጎሣዊ ግንድን ፈጥረዋል፡፡ ሁሉም ሚስዮናውያን፣ የቅኝ አገዛዙ ባለሥልጣኖችና የሩዋንዳ ቁንጮዎች ሁቱና  ቱትሲ በሚል ሁለትዮሽ የፖለቲካ እሳቤ ውስጥ ተዘፍቀዋል(ገጽ 173)[14]፡፡

 ይህ ዝንባሌ  እንደ ሞራላዊ አስተሳሰብ  ጉድለት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በኸሽቲፈር፣ ኢስማኤል እና ሞግሃዳም(2011) [15] እንደሚሉት በመሠረቱ የሞራል አሰተሳሰብ የማናችንም ሰዎች ዋና የማሰብ ብቃት ነው፡፡ ይህም ልዩና ግልጽ ዓይነት የሞራል አስተሳሰብ ተደርጎ የሚወሰድና ከሁለቱም ማለትም ከስሜታዊነት ከሚመነጨውና በንቃት ከሚገኘው አስተሳሰብ ነፃ የሆነ ነው፡፡ የሞራል አሰተሳሰብና የፅንሰ ሃሳቡ ቃላት አመጭዎች የሆኑት ሌኒክ እና ኪየል ሃቀኝነት፣ ሃላፊነት፣ ይቅር ባይነት እና ርህሩህነት[16] የተሰኙ አራት አይነት ብቁ የሞራል አስተሳሰቦችን ለይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም በሚባል ደረጃ ጎሣዊ ብሔርተኞች እነዚህ ክህሎቶችና እሴት ይጎድላቸዋል፤ እንዲሁም በሚዘገንን ሁኔታ ሞራላዊ አስተሳሰባቸው የወረደ ነው፡፡ 

ውሸትና ሰይጣናዊ አስተሳሰቦች የላሸቀ ሞራላዊ አዕምሮ ያላቸውን ሰዎች ይጠናወታቸዋል፡፡ ሁሉም በሚያስብል ደረጃ ጎሣዊ ብሔርተኞች በዚህ አንድ ቦታ በታጠረ እንከን የተበከሉ ናቸወ፡፡ አክሎግ ቢራራ(2019) እነርሱን ወይም ድርጊታቸውን እንደፈረጀው ታላቅ የሃሰቶች ግንብ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ምሁራን፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቁንጮዎች መካከል ያለው ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ የዕውቀት ክፍተት ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡ ይህም መረን በወጣ የተዛባ መረጃና ጠብ ያለሽ በዳቦ ዓይነትና ይሄ ነው በማይባል ያልለየለት/ግርድፍ/ ፖለቲካ የሚመራ ነው፡፡ የአማራን ታሪካዊና የሃገር ግንባታ ሚና ሆን ብሎ አሌ ማለትና ያልተገባ መረጃ መንዛት በዓለማችን ውስጥ እጅግ አደናቀፊ፣ ያልረገበ፣ አውዳሚና አደገኛ አንደምታ አላቸው ከሚባሉት መካከል የጥፋት መንሥዔ ነው፡፡ 

የኔ ቀጣይ ግብዓት ራስን ከፍ ከፍ ማድረግና የበታችነት ስሜት ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡ እነዚህን ሁለት ግብዓቶች አንዱ አንዱን በመተካት መጠቀም ይቻላል፡፡ ጎሣዊ ብሔርተኞቻችን የታላቅነት መርዘኛ ስሜትና ራስ አምላኪነት የተጠናወታቸው ኛቸው፡፡ ምርምር እንደሚያመለክተው ራስን ከፍ ከፍ የማድረግ አዝማሚያ በውስጥህ ከሚሰማህ ትንሽነት ስሜት የሚመነጭ ነው፡፡ ትንሽነትን ለማካካስ በሌሎች ዘንድ ራስህን ከፍና ከፍ አድርገህ ለመታየት የምታደርገው ሁኔታ በጊዜው ከምትኖረው ህይወት በላይ የተጋነነ ሆኖ ሲታይ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ባህሪያት ከስሜትና አዕምሮ መዛባት የሚመነጩ ናቸው።

እነዚህ ችግሮች ሊወገዱ የሚችሉት ከራስ በመነጨ ጠለቅ ያለ ተጋፋጭነት በመፈወስ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ከሚሉትና ከሚያደርጉት አኳያ እኔ የተከታተልኳቸው አብዛኛዎቹ  ጽንፈኛ ብሔርተኞች የለፍላፊነት፣ የጉረኝነት፣ የበላይነት ለማምጣት የታለመ የራስ አምላኪነትና የተፎካካሪነት ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡

ይህም በጃዋር መሃመድና ጌታቸው ረዳ ላይ እንደታዘብነው የቁጡነት፣ የጭካኔና ነገሮችን በራሳቸው መንገድ ለማስኬድ ጫና የመፍጠር ባህርይን የሚዳዳ ነው፡፡  በሃሰተኛ ውግዘቶች፣ ስም አጥፊ ዘመቻዎች፣ ውዥንብሮችን የመንዛት፣ የሰውን ማንነት የሚያጠለሹና አጥፊ ሃሜታዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ራሳቸውን ላይ የሚያስቀምጡ ሰዎች ምንጊዜም ከፋፍለህ ግዛ/ድል አድርግ የሚለውን ስልት በሰዎች ላይ የበላይነት ለማግኘት ይጠቀሙበታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ሰላሳ ዓመታትም ስንታዘብ የኖርነውም ይህንኑ ነው፡፡ እዚህ ላይ የራስ አምላኪነት ጽንሰሃሳብ ጠቃሚነት አለው፡፡ ለምን ብትሉ  እንደ አንድሪው ዲ. ብራውን(1997),[17] ከሆነ የቡድንና የተቋምን ባህሪ በማጥናት ረገድ ራስ አምላኪነት ንድፈሃሳብ ጠቃሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ልክ ግለሰቦች የራሳቸውን ክብር በራስ ወዳድነትን  በማስጠበቅ ዘዴ ለመቋቋም ማለትም አሌ ባይነት፣ ልክ ነኝ የሚለውን በማስረጃ ለማስረገጥ መዳዳት፣ ከውስጥ በመነጨ የተጋነነ እኔ በልጥ ባይነት፣ በባለቤትነት ስሜት፣ ራስን በማግዘፍ  ጭንቀትን ለማቃለል የሚሞከርበት ሁኔታ በግልባጩም ለቡድኖችና ለድርጅቶች የሚሰራ ነው፡፡   

ይህም ቡድኖችና ድርጅቶች የራስን ጥቅምና ክብር  የሚያስተካክሉበትን ባህሪ ለመረዳት አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ከበስተጀርባው ያለውን የድርጅት አባላት አስተዋጸኦ  መሠረታዊ መንስዔ ለማወቅ ያስችላል፡፡ እነዚህን ሁሉ ባህርያት እንደ ህወሃትና አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች በመሳሰሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ እናገኛቸዋለን፡፡ ለምንድ ነው ጥፋተኛ አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች የአሻጥሩ መፈልፈያ ዕምብርት የሆነችውን መቀሌ ከተማን የሚጎበኙት? የወሎን አካባቢስ የኦሮሞ ግዛት ነው ብሎ ማወጁስ አንደምታው ምንድነው?[18] ሰውየው ምንም አያውቅም፤ ሆኖም ግን ሁሉንም ነገር እንደሚያውቅ ያስባል፡፡ ይህ የፖለቲካ ህይወትን በትክክል ያመለክታል ጆርጅ በርናርድ ሾው፣ ሜጀር ባርባራ።

በኢትዮጵያ ውሰጥ ቁጥራቸው ከፍተኛ በሆኑ ጎሣዎች መካከል ብጥብጥ ለመፍጠር አደገኛ ፍላጎት ባላቸው የጎሣ ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተብዬዎች የሚካሄደው እኩይ፣ የክህደት እርምጃና አመኔታ የማይጣልባቸው ስብከቶች የጊዜው ዓይነተኛ ፈሊጦች ሆነዋል፡፡ ይህም ከብዙ አስርት ዓመታት በፊት በትግራይ ካድሬዎች ተጀምሮ አሁን ደግሞ በኦሮሞ ዘረኞች ተጠናክሮ የቀጠለ ነው፡፡ የቅርብ ጊዜ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው ፐሮፌሰር እዝቅኤል ገቢሳ[19]  ከዋልታ ቴለቭዥኑ[20] ስሜነህ ባይፈርስ ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ከአሰፋ ጃለታ(2001) መጽሃፍ (Fighting Against the Injustice of the State and Globalization: Comparing the African American and Oromo Movements) የሚል ርዕስ ከሰፈረው ይዘት ጋር ተመሳሳይነቱን ማየት ይቻላል።   

እነዚህ ሁለት ማሳያዎች ናቸው፡፡ በነዚህ ምሁራን ሥራዎችና በተከታዮቻቸው በተሰጡት አስተያየቶች ላይ  የተደረገው ጠለቅ ያለ ንባብ እንደሚያመለክቱት ሃቀኛና ተዓማኒ መሠረት የሌላቸው ናቸው፡፡. በመጽሃፎቻቸው ወይም በሌሎች ህትመቶቻቸው ላይ የተጠቀሱት ደረጃቸው የወረዱ የጥናትና ምርምር መረጃዎች ለዘመናዊ የማህበራዊ ሣይንሥ/ታሪክ በከፍተኛ ደረጃ የማይጠቅሙ ፍሬ-ፈርስኪ ሃሳቦች ናቸው፡፡  እኔ የፈረጅኋቸው ፖለቲካዊ ዘረኝነትን በራስ የሚያራምዱ እኩይ ድሮች/የተለመጡ እግሮች መሆናቸውን ነው፡፡ እነዚህ ግልብ ቅስቀሳዎችና አንዳችም ውክልና የሌላቸው መነሳሳቶች ለብዙሃን ፍጅት፣ መፈናቀል፣ አለመረጋጋትና ብጥብጥ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ድቀት ምክንያት ሆነዋል።

ካለመማር ማንኛችንም እጅግ ወደሆነው የተማሩ ሰዎችን ሙሉ በሙሉ የመቀበልና የማምለክ አስከፊ አዘቅት ውስጥ ይከተናል ጂ. ኬ ችሰተርተን።

በሚገባ በሚሰራና በትክክለኛ የፌደራል አወቃቀር የብሔር ማንነት፣ የቋንቋ ማደግ፣ እኩልነትና የባህል ብዘሃነትን ማክበር ያለውን ጠቀሜታ አላጣጥልም፡፡ አሁን ያለው ህገመንግሥትና የፌደራል አወቃቀር ግን የማይሰራ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለመበታተን[21] የተዘጋጀ ቅንብር ነው፡፡. የራስ ፈላጊነት ስብእና የተጋነነ ተበዳይ ነኝ ባይነት፣ ራስን ሰለባ የማድረግ ዝንባሌ፣  የዘር ማንነትን ለፖለቲካ ትርፍ ማዋልና ሃሰተኛ ትርክቶች ለሰቆቃ፣ ለሀገር ውስጥ መፈናቀል፣ ለሞትና  በጉርብትና በሚኖሩ የተለያዩ ጎሳዎች መካከል መተማመን እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል፡፡. ኢትዮጵያ በዓለም እጅግ ደሃ ሃገሮች ከሚባሉት መካከል አንዷ የሆነችና በተደጋጋሚ ረሃብ እየተጠቃች ያለች ሃገር ሆና ሳለ እነዚህን አዳዲሰ ሰው ሰራሽ ችግሮች መጨመር የዘር ማጥፋት ቅንብር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ 

ኢትዮጵያ የምትፈልገው ነገር ቢኖር ከአሃዳዊ(ከአንድ) ኢትዮጵያዊነት(pan-Ethiopianism) ጎን ለጎን ትክክለኛ ፌደራሊዝም ነው፡፡  እርግጠኛ ነኝ አመዛኙ አብላጫ የኢትዮጵያ ህዝብ መኖር የሚፈልገው በሰላማዊዋ ኢትዮጵያ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ሥር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ዓመት በበዓለ ሹመታቸው ላይ እንደተናገሩት የኛ ማንነት እርስ በርሱ የተሳሰረና የተዋሃደ ስንወለድም ኢትዮጵያውያን ስንሞትም ኢትዮጵያውያን ነን”  ብለዋል፡፡ ከልባቸው እንዳሉትም ተስፋ አደርጋለሁ

እዚህ ላይ ግን በጣም የሚያሳዝን ነገር ቢኖር ግን በትግራይ ካድሬዎችና በአክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች  የንጉሠ ነገሥት ሚኒሊክን ማንነትና ስመ ጥርነትን እንዲሁም የአድዋን ድል የማጣጣሉ ጉዳይ ነው፡፡ የአውሮፓውያኖች አፍሪካን የመቀራመት ግስጋሴ  በብቃት የቀለበሰች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ለመላ አፍሪካዊነትና ለዓለማቀፋዊ  ፀረ-ቅኝ አገዛዝ[22]  እንቅስቃሴ ብቸኛ ፋና-ወጊ መሆን የቻለች ሃገር ናት፡፡  የዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያን በሮማ ቅኝ አገዛዝ የታደገ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ሀገሮች እንደ ሌላው የዓለም ህብረተሰብ[23] እኩል የሃገርነት ደረጃ እንዳላቸው ያሳወቀ ነው፡፡  ይህም ድል የተገኘው በተባበረ የኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራና በሌላው ኢትዮጵያዊ ጥረት የተገኘ ነው፡፡ ድሉ የማንም ኩራት ነው፡፡ የሞራል አስተሳሰብ ካልጎደላቸውና ሃቁን ማጣጣል ካልፈለጉ በስተቀር ለመሆኑ እነዚህ ጎጠኞች  ለምንድር ነው ይህን ወርቃማ ታሪክ ለማጥፋት የፈለጉት?! አልዶስ ሃክስሌ ሃቅ እነዲዘነጋ ስለተፈለገ ብቻ መታወቅ መቀጠሉ አይቀሬ ነው (ሃክስሌ / Huxley, Complete Essays 2, 1926-29)

እ. ኤ. አ.  በኦገስት እሁድ 4፣ 2019 በተባበሩት መንግሥታት የቅርብ ጊዜ ስሌት መሠረት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 110 ሚልዮን 344 ሺህ 154 መድረሱን መጥቀሱ በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን  50 ሚልዮን እና ከዚያም በላይ የሆኑትን ከ80 በላይ የሆኑ ብሄር ብሄረሰቦችንና በብሄር ብሄረሰቦች መካከል የጋብቻ ትሥሥር ያላቸውን ጨምሮ በማግለል የፖለተካዊው ሂደት በብቸኝነት በሦስቱ ብሔሮች(ኦሮሞ፣ አማራና ትግራይ) ዙሪያ እየተሸከረከረ ነው፡፡ እንደኔ ግንዛቤ ከሆነ እነዚህ ቡድኖች የወደፊቷን  ኢትዮጵያ በተመለከተ በሁሌ ሥጋትና ጭንቀት የተዘፈቁ ናቸው፡፡ 

እስከ አሁን ድረስ ኢትዮጵያ በርካታ የተለያዩ ህዝቦች በአጠቃላይ በሚባል ደረጃ በከተሜ ማህበረሰብነት በሙሉ መረጋጋት የሚኖሩባት ሃገር ነች፡፡ እንደ አንዳንድ የሚነዱ ፖለቲከኞችና ጎሣዊ ብሔርተኞች የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ተብዬዎች፣ በጎተራ ሙሉ የሃሰት ትርክትና አጭበርባሪና እኩይ ምክንያተች ሳይሆን በታሪክ ሂደት እንዳስተዋልነው ሐረርና አዲስ አበባን በመሳሰሉ በርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች የተለያዩ ህብረተሰቦች በአንድነት የኖሩባቸው ሲሆን የዛሬዎቹ ኢትዮጵያውያውያንም በዘር ልዩነቶች ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በመቻቻል ረገድ አበውን ወይም አያት፣ ቅድመ ኣያቶቻቸውና ኣባቶቻቸውን የሚመስሉ ናቸው፡፡ 

ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣን ባህል መሠረት ያደረገ የአንድነት ስሜት፣ ታማኝነትና ተቆርቋሪነት የአንዲትን ሃገር ጥብቅ ትሥሥርን የሚያመጣና በሌላ መልኩም ከደለበ ታሪክ በተመዘዙ እንዲሁም እዚህ ለመኖር በወሰኑ ሁሉ የጋራ ዕጣ ፋንታ አንድ አካልነት ይፈጥራል፡፡ 

በዚህ የማሳያ ጽሁፍ የጎሣዊ ብሔርተኞችን አጀንዳዎች ናቸው የሚባሉ ምክንያቶች፣ መንስዔዎችና ፍላጎቶች ነቅሼ ለማውጣት ሞክሪያለሁ፡፡ እዚህ ላይ የኔ ማሳሰቢያ የሚሆነው የህወሃት ካድሬዎችና ሌሎች ጎሰኞች(የፀረ-ኢትዮጵያ እንዲሁም ፀረ-አማራ ቅስቀሳ አራማጆች) በአጥፊ ውሸትና አሉባልታ የተጠመዱ መሆናቸውን ነው፡፡ ይሀንን ሃሰተኛና የተምታታ መረጃ በተቀነባበረ ጥረት መዋጋት አስፈላጊ ነው፡፡ 

የኔ ትንታኔ እንደሚያመለክተው ድንቁርና፣ አደገኛ ፍላጎቶች፣ ዝቅተኛ የሞራል አስተሳሰብና ሆን ብሎ መጃጃል የነዚህ ሁሉ ጽኑ ጎሣዊ ብሔርተኞች የጋራ መገለጫዎች ወይም ባህርይ ናቸው፡፡እነዚህ በማተራመስና በመበታተን አባዜ የተጠመዱ ለራሳቸው ወገኖቼ እንኳዋን በሃቀኝነት የሚቆረቆሩም አይደሉም፡፡ የነሱ ቀዳሚ መነሳሻ ሥነልቦናዊና ግላዊ ምክንያቶች ናቸው።ይህም የነሱን በሽታ አስመልክቶ ያደረግሁት ምርመራ ነው፡፡ ለዚህም መፍትሔው፣ አማራጭ ፈውሱና ወደሚበጀው የሚያቀናው ጎዳና በክፍል ሁለት የሚቀርብ ይሆናል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ልበ ቅን ከሆነው  ድንቁርናና ሆን ብሎ ከመጃጃል በላይ የበለጠ አደጋ የለም ” ማርቲን ሉተር ኪነግ ጁኒየር። 

ዋቢ ምንጮች

[1] TPLF was the main and most powerful party within the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, the so-called ruling political coalition which consists of four political parties.

[2] https://21stcenturywire.com/2019/07/22/ethiopia-ethnic-apartheid-and-the-globalist-colonizers-playbook/

[3] https://www.accord.org.za/ajcr-issues/ethnic-federalism-conflict-ethiopia/

[4] What you are about to read should be of concern to you whether you live in America, France, Ethiopia or any corner of the world. For there is a nefarious ploy that has been used throughout the ages to splinter society into the ghettos of imposed identities and divisive ideologies. https://21stcenturywire.com/2019/07/22/ethiopia-ethnic-apartheid-and-the-globalist-colonizers-playbook/. Ethiopia: Ethnic Apartheid and the Globalist Colonizers’ Playbook. July 22, 2019 By 21wire.

[5] One culprit is the false narrative accusing Amharas of “chauvinism,” neftegna, oppression and other abusive and marginalizing terms to describe Amhara culpability and guilt. Tragically not only for Amharas and others whose dedication to Ethiopia is irrefutable, the false narrative is deep, wide and corrosive. It will take decades of reeducation to erase the narrative due to ignorance and inability to change, especially among political elites, intellectuals and activists. (Ethiopia’s Policy Logjam and Unintended Consequences.ECADF in Opinions July 28, 2019.   https://ecadforum.com/2019/07/28/ethiopias-policy-logjam-and-unintended-consequences/

[6] Neisser, U. (1996). Intelligence: Knowns and unknowns. Washington, DC: American Psychological Association.

[7] Hodson, G., & Earle, M. (2017). Anti-Semitism. In F.M. Moghaddam (Ed.), The SAGE Encyclopedia of Political Behaviour (pp. 28-30). Thousand Oaks, CA: SAGE.  http://dx.doi.org/10.4135/9781483391144.n19

[8] Hodson, G., MacInnis, C.C., & Busseri, M.A. (2017). Bowing and kicking: Rediscovering the fundamental link between generalized authoritarianism and generalized prejudice. Personality and Individual Differences, 104, 243-251. DOI: 10.1016/j.paid.2016.08.018

[9] Hodson, G., Turner, R.N., & Choma, B.L. (2017). Individual differences in intergroup contact propensity and prejudice reduction.  In L. Vezzali & S. Stathi (Eds). Intergroup contact theory: Recent developments and future directions(Series: Current Issues in Social Psychology) (pp. 8-30). New York, NY: Routledge.

[10] Ignorance leads to deaths and massive incarcerations. Ignorance keeps Ethiopia poor, backward and vulnerable to external threats. Ignorance deters development. Ignorance leads to the destruction of investment properties (Birara, 2019). (Ethiopia’s Policy Logjam and Unintended Consequences.Why willful ignorance should be combatted now. https://theworldnews.net/et-news/ethiopia-s-policy-logjam-and-unintended-consequences.

[11] “My response to Oromo Intellectuals for their Misrepresentation of, and attack on, Ethiopian History. (Professor Haile M. Larebo)

[12] A few weeks ago, Herman Cohen—a neocon warmonger who used to be George Bush’s Assistant Secretary of State for African Affairs—tweeted a most malicious slur against Amhara people in a naked attempt to further incite tribalism and fan the flames of hatred that is threatening to unleash the dark forces of sectarianism upon Ethiopia. At a time where uncertainty was sweeping across the country after a supposed “regional coup d’etat”—which was an outlandish and oxymoronic media narrative being peddled by the Ethiopian government—there was a one-two punch that pushed Ethiopia closer to the brink of conflagration. (https://21stcenturywire.com/2019/07/22/ethiopia-ethnic-apartheid-and-the-globalist-colonizers-playbook/). Compare Herman Cohen’s statement with Abyssinia: the powder barrel by Roman Procházka, Freiherr von. London, British international news agency [1936?] 

[13] Ethiopia’s Policy Logjam and Unintended Consequences. Posted by: ECADF in Opinions July 28, 2019. https://ecadforum.com/2019/07/28/ethiopias-policy-logjam-and-unintended-consequences/(by Aklog Birara)

[14] Carney, J. J. (2012). Beyond tribalism: the hutu-tutsi question and catholic rhetoric in colonial Rwanda. Journal of Religion in Africa, 42, 172-202.

[15] Tanner, C. & Christen, M. (2014). Moral Intelligence – A Framework for Understanding Moral Competences. In M. Christen et al. (eds.), Empirically Informed Ethics: Morality between Facts and Norms (119-136). Zurich, Switzerland: Springer International Publishing.

Beheshtifar, M., Esmaeli, Z., & Moghadam, M. N. (2011). Effect of moral intelligence on leadership. European Journal of Economics, Finance and Administrative Sciences, 43, 6-11.

[16] Lind, Georg (2008). “The meaning and measurement of moral judgment competence: A dual-aspect model”. In Fasko, Daniel Jr; Willis, Wayne (eds.). Contemporary Philosophical and Psychological Perspectives on Moral Development and Education. Hampton Press. pp. 185–220.

[17] Brown, A.D (1997). Narcissism, Identity, And Legitimacy. Academy of Management Review VOL. 22, NO. 3.  Published Online: 1 July1997 Doi: https://doi.org/10.5465/amr.1997.9708210722.

[18] Not only does the Professor engage in selective denunciation, he spreads ethnic hatred.  In most of his political discussions, interviews, speeches, and writings he instigates conflict between Amharas and Oromos.  In an essay that appeared on  Ethiomedia on October 20, 2016, he lists (by quoting another author) ethnic slurs directed at the Oromo more people supposedly by Amhara people, as an example of how the Amharas have oppressed, marginalized, and dehumanized the Oromo people for more than hundred years. In the eyes of many Ethiopians, as Donald Donham keenly observed, the “Galla were pagans. They were uncivilized. Ye Galla chewa ye gomen choma yellem (it is impossible to find a Galla gentleman as it is to find fat in greens) or again Galla inna shinfilla biyatbutim aytera (even if you wash them, stomach lining and a Galla will never come clean).” In one Amharic expression, Oromos were equated with human feces: “Gallana sagara eyadar yegamal” (Galla and human feces stink more every passing day). In another, even Oromo humanity was questioned: “Saw naw Galla?” (Is it human or Galla?). What was the purpose of listing these ethnic slurs?  Why stoop so low?  ………. it is to create resentment, animosity, and hostility among Oromos against the Amhara people. But what he should have realized is that ethnic, racial, or regional slurs are not unique to Ethiopia.  They are ubiquitous elsewhere as well.  Still, intellectuals don’t resort to using slurs to bolster their arguments. https://www.satenaw.com/the-intellectual-bankruptcy-of-hizkiel-gebissa/ Gemechu Aba Biya.

[19] In  an interview on August 1 with Semeneh Biafers of Walta TV, Hizkiel  Gebissa  makes many deceitful statements, as he has done in the past. It’s time to take him to task.  He describes himself as a public intellectual dedicated to defending human rights in Ethiopia. But a glimpse of his interviews, speeches, and writings reveal that the man is neither an intellectual nor a human rights advocate; rather, he is an intellectually bankrupt and dishonest imposter. https://www.satenaw.com/the-intellectual-bankruptcy-of-hizkiel-gebissa/ Gemechu Aba Biya.

[20] https://borkena.com/2019/08/02/professor-ezekiel-gebissa-interview-with-simeneh-bayfers-of-walta-tv/. Professor Ezekiel Gebissa interview with Simeneh Bayfers of Walta TV.

[21] ‘The term Balkanization has frequently been used in reference to Ethiopia’s ethnic federalism, which has been codified in the country’s dysfunctional constitution that curiously defines politics, citizenship, rights and privileges on ethnic grounds.  Strictly speaking, there are no political or administrative terms in history that can fully and adequately explain the bizarre experiment that we see unraveling in Ethiopia. Nonetheless, a term, which comes close to describing the policies of the current government and the unfolding ethnic violence and repression, is ‘bantustanization,’ which has its origin in apartheid South Africa. The ‘Bantustanization’ of Ethiopia and Its Looming Dangers  (by Dawit W Giorgis) https://theworldnews.net/et-news/the-bantustanization-of-ethiopia-and-its-looming-dangers. 18:48 / 31.07.2019 ECADF

[22] Pankhurst, K.P. (1998) The Ethiopians: A History, The Peoples of Africa Series, Oxford: Blackwell Publishers, ISBN 0-631-22493-9

[23] The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire by Raymond Jonas (Cambridge, Massachusetts: Belknap Press, 2011)

 

 

Filed in: Amharic