>

ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ ከወራት እስራት በኋላ ተፈታ!!!

ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ ከወራት እስራት በኋላ ተፈታ!!!
ዳዊት ሰለሞን
 
* ኢህአዴግ መቼ ይሆን ሰዎችን በግፍ እያሰሩ ማስረጃ ፍለጋ ካልተገኘም የፈጠራ ክስ ምስረታውን የሚያቆመው???
ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ ከወራት እስራት በኋላ የመንቀሳቀስ መብቱን አግኝቶ ለጊዜው ከቤተሰቦቹ ተቀላቅሏል ። በሪሁን የታሰረው ማዕከላዊን ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረግ፣ከአሁን በኋላም በፖለቲካ አመለካከቱም ይሁን ሐሳቡን በመግለፁ ማንም እንደማይታሰር በተነገረ ቅፅበት ነው።
የለውጡ መሪ የሚባለው የኢህአዴጉ ሊቀመንበር በይፋ “አስረን ማስረጃ አንሰበስብም “ማለታቸው ባይዘነጋም እነበሪሁን እየተጎተቱ ወህኒ ተጥለው ማስረጃ ሲፈለግባቸው ለመቆየቱ የፍርድ ቤት ምልልሳቸውን በማየት መረዳት ይቻላል። አሁን ከወራት እንግልት በኋላ “በሪሁን ወደቤት ሂድ “ተብሏል።
በቃ አሁን መንግስት ደግ ነው እንበል መቼ ነው ግን ንፁሃንን እየጎተቱ ማሰርና ማስረጃ ማፈላለግ መንግስትን ካሳ የሚያስከፍለው ? በየትኛው የኢትዮጵያ መንግስት ዘመን ይሆን ዜጎችን ማሰር የመጨረሻው አማራጭ የሚሆነው ? ጊዜያቸውን በጠረጠርኳቸው ሰበብ በከንቱ ማቃጠል ፣ስማቸውን ማጥፋትና ለእንግልት መዳረግ መንግስትን ተጠያቂ ሊያደርገው ካልቻለ ማሰር ቀላሉ መንገድ እንደሆነ ይቀጥላል ።
Filed in: Amharic