መምህር ታዬ ቦጋለ አረጋ
በኢትዮጵያ በአጠቃላይና በተዋህዶ ሀይማኖት በተለይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ሲከፈት ይህ የመጀመሪያው አይደለም። መለስ ዜናዊና ታጋይ ጳውሎስ ከዋልድባ ገዳም ጀምሮ በሠሩት ሴራ – በፍጥነት ተጠርተው ጉዳያቸው በሰማይ ችሎት ዕየታየ ነው።
*
ጓድ በላይ፦ የኦህዴድ የፓርላማ ተወካይ፣ የኦሮሚያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አመራር ከመሆኑም ሌላ – በኦሮማራና መላው ኢትዮጵያ ትግል ወቅት በተደጋጋሚ ሳይጠራ እየጠየቀ ጭምር – ከእኛ ጋር በአንድ ለእናቱ Think tank ቡድን ይሰበሰብ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም በዋቄፈና/ኢሬቻ በዓል ላይ ዋና አጋፋሪ ከመሆኑ ሌላ – ከእኔ ጋር በግል በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ተወያይተን እናውቃለን። የለየለት ካድሬና ለእምነት ቁብ የማይሰጠው ግለሰብ ሲሆን – የግል አቋሙና መሻቱ ብዙም መነሻዬ አይደለምና ልለፈው።
*
ጓድ በላይ ፓትርያርክ ጳጳስ ኤጲስ ቆጶስ – ሌላው ቀርቶ ቆሞስ ደረጃ ላይ የማይገኝ – ተራ ቄስ ነው። ከሲኖዶስ ውሳኔ ውጭ የትም መድረስ አይችልም። አንድ አማራጭ ብቻ አለው – እንደ ተሀድሶዎች የራሱ ኑፋቄ ይዞ – የግል እምነት ማቋቋም።
*
መጯጯህ ሳያስፈልግ ኦሮሚያ ውስጥ ልክ እንደ ትግራይ አማራ እና ሌሎች ክልሎች – ዜማዎችና ቅዳሴዎች በግእዝ – ስብከት በአማርኛና በኦሮምኛ እየሄደ ነው።
የአጀንዳው ባለቤት ሃጂ ጃዋር መሀመድ እንደመሆናቸው – በማይመለከታቸው ገብተው ባይፈተፍቱ እየመከርን – ሙስሊም ቤተሰቦቻችን ዘንድ ሄደው አረብኛ ቀርቶ መስጊድ በኦሮምኛ ይሁን እንደማይሉ ሁሉ – እጃቸውን ከእናት ቤተክርስቲያን እንዲያነሱ እየጠየቅን – በእሳት መጫወታቸው እንደሌላው አጀንዳ ሳይለበልባቸው እንደማይመለስ ልንመክራቸው እንወዳለን።
ኢትዮጵያዊ በየትኛውም አጀንዳ ጊዜ ሊሰጥህና ሊታገስህ ይችላል። በእምነቱ ከመጣህበት ግን – አንዴ ከመቁረጥህ በፊት አስር ጊዜ ለካ። መከላከያውና የፀጥታ ኃይሉ ጭምር በእምነቱ አይደራደርም። ‘ዓሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል’ እንዳይሆን። ምእመኑ እንኳን ስብከትና አምልኮ ሌላውንም በምክክር ማድረግ ይችልበታል። አትሸቅጡ!