>
5:13 pm - Thursday April 18, 9224

እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ስለቤተክርስቲያኔ አንድነት እየመሰከርኩ እና እያስተማርኩ እሰዋለሁ!!! (ብጹዕ አቡነ ናትናኤል)

እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ስለቤተክርስቲያኔ አንድነት እየመሰከርኩ እና እያስተማርኩ እሰዋለሁ!!!
ብጹዕ አቡነ ናትናኤል
የምስራቅ ወለጋ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ናትናኤል ይናገራሉ።•••”ስለ እውነቱ ከሆነ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመላው ሃገራችን ከጫፍ እስከ ጫፍ ቤተ-ክርስቲያን በከባድ ፈተና ላይ እንዳለች ለማንም ግልፅ ነው። ለዚህም ማሳያ በየአካባቢው የሚቃጠሉ አብያተክርስቲያናት የሚሞቱ ካህናት እና ምዕመናን ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂየኦሮሞ ቤተክህነት ከሚባለው አጀንዳ ጋር በተገናኘ እንቅስቃሴውም ሆነ ዓላማው ምንም ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ይህን ስልህ ደግሞ በማስረጃ ነው። በእኔ ሃገረ ስበከት ዝማሬው ቅዳሴው ስብከቱ ሁሉ ሁሉንም ባማከለ መልኩ በኦሮምኛ በአማርኛ እና በግዕዝ ነው።
እኔም እራሴ በክልሉ አገልግሎቱ በስፋት እንዲሰጥ ካለኝ ፍላጉት እና ጉጉት የተነሳ በመንበረ ጵጵስናዬ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሮምኛ ቀድሼ አቁርቤ ሰብኬ ጀምሬ ያስጀመርኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በቢሮ ስራም ደብዳቤዎች በኦሮምኛ ሲመጡ የምናስተናግደውም ሆነ የምንመራው በኦሮምኛ ነው፡፡ እኔም በኦሮምኛ የመጣን ደብዳቤ ስመራ በኦሮምኛ ነው።ከዚያ ውጭ  ቅዱስ ሲኖዶስን ማክበር ያስፈልጋል። ከቃለ ዓዋዲው ውጪ መንቀሳቀስ ከበድ ያለ መንፈሳዊ ቅጣት ያስከትላል፡፡ ከዚህ ውጪ የሚመጣ ካለም እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ስለቤተክርስቲያኔ አንድነት እየመሰከርኩ እና እያስተማርኩ እሰዋለሁ። ምክንያቱም ከአባቶቼ የተቀበልኩት አደራ እና ሃለፊነት ነውና!”
Filed in: Amharic