>

በባለጌ ዘመን የማይዋረደው ብልግና ብቻ ነው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

በባለጌ ዘመን የማይዋረደው ብልግና ብቻ ነው!!!
ቬሮኒካ መላኩ
 
” መላእክት ለመርገጥ የሚፈሩትን ቦታ ቂሎችና  ባለጌዎች ይሯሯጡበታል “(The place For fools rush in where angels fear to tread )  ይላሉ እንግሊዛውያን።
 መላእክት ለመርገጥ  የሚፈሯትን ቅድስት ቤተክርስቲያን በባለጌዎች እየተዋረደች ነው።በባለጌ ዘመን የማይዋረደው ብልግና ብቻ ነው።
 ከ2ሺህ አመታት በላይ ታፍራና ተከብራ የኖረችው ተዋህዶ ሃይማኖት በዘመን አመጣሽ ባለጌዎች እየተደፈረች ነው።  አባ ባህሬ  ከ500 አመታት በፊት “ጠፍአ አገርነ “( አገሬ ጠፋች) ያሉት ተመሳሳይ ፍዳ ገጥሟቸው ነበር። ያሁኑ የባሰ ሆነ።
አሁን መንግስት ተብየው  የማፊያ ቡድን የብሄር ተቃርኖው አገሪቱን አለመበታተኑን ቆጭቶት የሀይማኖት ተቃርኖውን እያጦዘው ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው በመንግስት  Green light መሆኑን አለመረዳትም የዋህነት ነው።
ሆኖም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለጥፋት ሀይሎች ምላሽም ማስጠንቀቂያም ሰጥታለች፤ ህግም ካለ በህግ አምላክ ብላለች፤

https://m.youtube.com/watch?feature=youtu.be&v=ClPn9LEGJJ8

Filed in: Amharic