>

የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” (ጥናታዊ ጽሑፍ | ክፍል ሁለት) ጌታቸው ረዳ)

የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” 
 
    (ጥናታዊ ጽሑፍ    |   ክፍል ሁለት ) 
 ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
በአሰፋ ሃይሉ
በካሊፎረኒያ ስቴት በሳን ሆዘ ከተማ በሃያት ሪጀንሲ ሳንታክላራ ሆቴል በሰኔ 26/2006 (July 3/2014) በሞረሽ ወገኔ የአማራ ሲቪክ ማሕበር በተዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ በአቶ ጌታቸው ረዳ የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ።
ጌታቸው ረዳ ( getachre@aol.com ) :-
የትግራይ ብሔረተኞች የአማራ ጥላቻቸው ከሌሎች ጎሳዎች ይልቅ ለምንድነው የበረታው? የሚለው መመለስ አለብኝ? ይህ ብቻ ሳይሆን “የትግራይ ብሔረተኛ ስሜት” መመንጨት የጀመረው መቸ ነው? የሚለውም አብረን ከመለስን ለጥላቻው መንስኤ ምዕራፉ ከየት አንደጀመረ ለመረዳት ይረዳናል።
/… ካለፈው የቀጠለ።/
የትግራይ ብሔረተኛነት ስሜት መታየት የጀመረው የትግራይ መሳፍንቶች እርስበርሳቸው ለስልጣን ሲሉ የአንድ አውራጃ ሕዝብ ከሌላው አውራጃ ጋር በደም፤ በአጥንት፤ በሃብት እና በሰራዊት ብዛት እየተኩራሩ በላቀ ተወልጄነት ወይንም “ትግሬነት” በመናናቅ ‘አውራጃዊ ስሜት’ በሕዝቡ ስሜት ላይ እንዲታነፅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ለስልጣን ሲሉም የአንድ እናት ወይንም የአጎት ልጆች እርስ በርሳቸው እስከመገዳደልም ደርሰዋል።
ይህ የበላይነት እና አውራጃዊ ስሜት አክሱሞች በዓድዋዎች ዓድዋዎች በአክሱሞች፤ አንደርታዎች እና ዓጋሜዎች በመላ የትግሬ እና ኤርትራ ተወልጄ ገዢዎች ላይ የበላይነት ለማረጋጋጥ ሲሉ አውራጃዊ ስሜት እንዲስፋፋ አድርገዋል።
ይህ የእርስ በርስ አከባቢያዊ የመናናቅ ስሜት እንዳለ ሆኖ፤ ከሸዋ ወይንም ከጐንደር፤ ከወሎ ወይንም ከሌላው አካባቢ አዲስ ገዢ/ጉልበተኛ ሲነሳባቸው ግን ‘አውራጃዊ የመከፋፋል ስሜታቸውን ወደ ጎን በማቆየት” ሁሉም ባንድነት “የትግሬ ብሔረተኛነት ስሜት” በማሰባሰብ እንደ ባዕድ በሚመለከታቸው የሌሎች አካባቢ ነገሥታት/ጉልበተኞች ላይ ያምጻሉ።
የንጉሡ ስም ካልተሳሳትኩ በአጼ አምደጽዮን ጊዜ ይመስለኛል……… በገዢነት ወደ እንደርታ በመጡበት ጊዜ () ትግራይ ውስጥ ከተወልጀዎች ውጭ የሆኑ ከድሃ መደብ ቤተሰብ የተገኙ ትግሬዎች ወይንም ከሌላ አካባቢ የመጡ በንጉሡ ስለተሾሙ “ሓለስተይቶት” አይገዙንም በማለት ጠባብ የትግራዋይነት ስሜት አንጸባርቀዋል። ሓለስተይቶት ማለት “የበታቾቻችን/ዲቃላዎች” ወይንም በአሜሪካኖቹ አሰያየም “ኔገር” አይገዛንም አንደማለት ይመስለኛል።
ዛሬ የምትሰሙዋቸው አንዳንድ የወያኔ ሰዎችም ሆኑ ኤርትራዊያኖች እርስ በርሳቸው ሲነታረኩ/ሲጣሉ/ሲከፋፈሉ “እዚኦም ባ ል መንዮም!?” (እነዚህ እነማን ይባላሉ?!) በመባባል አርስበርሳቸው በመናናቅ የሚያሰምዋቸው ቃላቶች ከዚያ ዘመን የወረሱዋቸው ትምክህታዊ ባህሪያቶች ናቸው። ለምሳሌ የወያኔው ብስራት አማረ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ‘ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ’ አንደወረደ፤ በጸጥታ መ/ቤት ሐላፊዎች ትዕዛዝ “ወደ አገር አንዳይገባ” ታግዶ ወደ መጣበት አሜሪካ አንደተመለሰ ከታወቀ በሗላ ‘ገዛ ተጋሩ’ በሚባል አፍቃሬ የወያኔ ‘ፓል ቶክ’ መድረክ ስለሁኔታው ተጠይቆ ሲያብራራ፤ የተጠቀመበት ቃል ያንኑ ቃል ነበር። “እነዚያ ዲቃላቆች” ነበር ያላቸው።
ያም ሆነ ይህ፤ ከሌላ አካባቢ የመጡ ሹመኞች በግማሽ የተወለዱ ትግሬ ገዢዎችን ‘ዲቃላዎች’ ወይንም ‘ባዕዳን’ ወይንም “ሓለስተይቶት” አይገዙንም በማለት ጠባብ የትግራዋይነት ስሜት አንጸባርቀዋል።
ያም ሖኖ በሌሎቹ አከባቢ ጉልበተኞች ቢገዙም ስሜታቸውን ‘በማመቅ’ አንዳንዴም ‘በማመጽ’ እስከ አጼ ዮሐንስ ድረስ ቆይተዋል። አጼ ዮሐንስ በነገሱበት ወቅት ግን የትግሬ ሕዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ ተገዝቶላቸዋል። እስካሁን ድረስም የልጅ ልጆቻቸውን “ደቂ ላሕምና” (የላሜ ቦራ/ የላማችን ልጆች” እያሉ ይጠሯቸዋል።ለምሳሌ የትግራይ
ሕዝብ በደረግ ጊዜ “ልዑል ራስ መንገሻ ስዩምን “ወዲ ላሕምና” አናስጠቃም በማለት ስለጮኸ ደርግ እርምጃ ከመውሰድ ተገ’ዶ ነበር።
ዮሐንስ ከሞቱ በሗላ ዘውዱ በምኒልክ ሲተካ፤ ትግሬዎች ከፍተኛ የሆነ “የባዶነት ስሜት” ወይንም ‘emptiness’/ a sense of generalized boredom) ተሰምቷቸዋል። የባዶነት ስሜት ለምን ሊሰማቸው ቻለ?
የትግሬ ሕዝብ ለዘመናት በራሱ አስተዳዳሪዎች የመገዛት ልምድ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የቆየ ስለሆነ፤ የካባቢው ሕዝብ ምንም ኩፉ ስርዓት እና ጨካኝ ገዢ ቢሆንም በአካባቢ ገዢ የመገዛት ፍላጎታቸው የበረታ ነው። ለዚህም ልዩ ምክንያት አለው። ምክንያቱም ስልጣን የያዘው ሕዝቡ ሳይሆን ገዚዎቹ ቢሆኑም “ስልጣን የያዙ ገዢዎች ትግሬዎች ከሆኑ፤ የትግራዋይነት ጉልበት እና የበላይነት ስሜትን በስነ ልቦናቸው እንዲቀረጽ በማድረግ በሌሎች ጐሳ ገዢ መደቦች ላይም ሆነ በሌሎች ጐሳዎች ላይ የበላይነት ስሜት አንዲያድርባቸው ሆኗል።”
እንግዲህ ከዚህ በመነሳት የትግራዋይነት ስሜት ከዘመነ አክሱም ጀምሮ እየተገነባ የመጣው የበላይነት እና የጉልበተኛነት ስሜት በሕዝቡ ስሜት በመቀረጹ ከትግሬ ሌላ ገዢ ካስተዳደራቸው፤ ጉልበታማነታችን እና እንዲሁም የትግሬነት የበላይነት ክብራችን ‘ተነጠቀ’ በሚል ስሜት በመነሳሳት የሌላው ጐሳ ንጉሥ በባዕድነት በመመልከት “ገዢዎች ኖረን ተገዢዎች አንሆንም” በሚል ስሜት “እሩቅ ትዝታ” ውስጥ በመግባት የስልጣን መለዋወጡ ጉዳይ ተፈጥሮአዊ መሆኑን ላለመቀበል ‘የተጠቂነት ስሜት’ አድሮባቸው ‘አንገዛም’ በማለት ጦርነት እና ግጭት ይፈጥራሉ። ጦርነቱ እና ግጭቱ በዛው ሳይወሰን፤ “ረዢም እና ጥልቅ የጥላቻ አጥር” በመገንባት ረዢም የሚጓዝ፤ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ የጥላቻ ውርስ ‘የማስተላለፍ ባሕል’ እያስረከቡ አልፈዋል።
ስለሆነም ነው የትግሬ ብሔረተኞች አጼ ዮሓንስ በመተማ ጦርነት ከተሰው በሗላ፤ ተከትለው የዙፋኑን መንበር የተረከቡት የሸዋው ንጉሠ ነገሥት “ምኒልክን” አንደጠላት እና ባዕድ ንጉሥ አድርገው በመመልከት፤ የትግሬ ሥልጣን ‘ወደ ሸዋ ተዛወረ’ በሚል ቁጭት የተነሱት የዘመኑ መሳፍንቶች ከንጉሥ ምኒልክ ጋር አለመጣጣም ፈጥረው “በሸዋ አንገዛም” በማለት ንትርኩ ወደ ሕዝቡ ተላልፎ መለስተኛ ጦርነት በትግራይ አካባቢ ተካሂዷል። ያ ዘመን፤ የትግሬ ብሔረተኞች በቁጭት የምኒልክን ዘመን “ዘመነ ሸ” ወይንም “ዘመነ ሸዌ” በማለት ይጠሩታል።
በትግሬ ብሔረተኞች ጸሓፊዎች መሰረት፤ ‘የሸዋ እና የትግሬ መቃቃር’ “ዘመነ ሸ” የሚሉት በንጉሥ ምኒልክ ዘመን ብቻ ሳይወሰኑ የትግሬ ብሔረተኛነት በሸዋ ነገሥታት እና በትግሬ ገዢዎች ቅራኔ የተፈጠረበት ዘመን ወደ ሗላ በመጎተት ታሪካዊ እና መሰረታዊ ቅራኔዎቻችን መነሻዎች ከሚሏቸው ነጥቦች ውስጥ አንዲህ ይገልጹታል።
የማነ ገብረመስቀል፤ የተባለው “ቀዳማይ ወያነ” የሚል መጽሐፍ የጻፈ ጸሐፊ በትግርኛ አንዲህ ይላል፦
“የትግሬ ሕዝብ ብረት አንስቶ ለመታገል የተገደደበት ለቀዳማይ ወያኔ አመጽ መነሻ በወቅቱ በተከሰቱ ምክንያቶች ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፤ ለዘመናት መፍትሄ ሳያገኙ በሕዝቡ “የልቦና ግምጃ ቤት” መሽገው የነበሩ “ታሪካዊ እና መሰረታዊ” ምክንያቶችም ጭምር ነው።”
ዶ/ር ክንፈ አብርሃም የተባለ ሌላው የትግሬ ምሁር (ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል) እነኚህ የሚከተሉት ምክንያቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የትግራይ ሕዝብ በሸዋ ገዢ መደቦች ላይ “ጥላቻ” አሳድሮ ነፍጥ አንሰቶ ሊታገላቸው ትልቅ ምክንያት ሆኖታል የሚላቸው ምክንያቶች እንዲህ ይዘረዝራል።
(ሀ) በሥልጣን ሽሚያ ምክንያት የተፈጠረው ፖላቲካዊ ግጭት በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጠረው ስሜት፤ የጀመረው፤-
“ከአክሱም መንግሥት መዳከም ወዲህ፤ እና አንዲሁም ድንግተኛ የሆነ ያልተጠበቀ የአጼ ዮሐንስ አራተኛ ሞት ተከትሎ የመጣው የሸዋ መንበረ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ “ትግሬዎች በትክክለኛ የፖለቲካ/ሥልጣን ሚዛን ላይ አይደለንም። ሥልጣናችን እና ታሪካችን በሸዋ ገዢ መደቦች ተነጥቀናል።” ክንፈ አብርሃም (2001- Ethiopia from Empire to Federation p.223) የሚል ስሜት አሳድረዋል።
ቀዳማይ ወያነ የሚል መጽሐፍ ደራሲ የማነ ገብረመስቀል ድግሞ እንዲህ ይላል፡-
“የሥልጣን ሥርወ መነግሥት እና ሥልጣኔ ማዕከላዊ መሰረቱ ትግራይ ውስጥ እና በትግሬዎች እጅ እያለ፤ በተንኮል ወደ ሸዋ ተወስዷል፤ ስለሆነም (ትግሬዎች) በሸዋ ገዢዎች ላይ ከፍተኛ ጥላቻን አከማችተዋል። በዚህ ሳይወሰን ቅራኔው ወደኋላ ብንሄድ የሸዋው የሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት የሆነው “ይኩኖ አምላክ” ሥልጣን ከያዘ በኋላ የእንደርታ (ትግራይ) ገዢ የነበረው ዓብየዝጊ እራሱ የሰለሞን ሥርወ መንግሥት ነኝ ብሎ በሚጠራው “ቡድን” ላይ ዓመፅ አካሄዷል። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ትግራይ ውስጥ በሸዋዎች ላይ ብዙ ተቃውሞዎች ተቀጣጥለዋል።” (የማነ ገብረመስቀል ‘ቀዳማይ ወያነ’ ገጽ 23)
እንግዲህ የትግራይ ብሔረተኞች ከሸዋ ጋር ቅራኔ የፈጠሩት ከይኩኖ አምላክ (12ኛው ምእተ እዝጊ) ዘመን የጀመረ ነው ብለው ነግረውናል።
የማነ ‘ቀዳማይ ወያነ’ በሚባለው የትግርኛ መጽሐፉ በሰፊው የገለጸው ባጭሩ አሳጥሬ ነጥቦቹ ለናንተ ጀሮ እንዲመች ላቅርብ። እንዲህ ይላል፦
“የአክሱም መዳከም ተከትሎ ትግሬዎች ከተዳከሙ በኋላ፤ ትግርኛ ተናጋሪው ሕዝብ በተለይም ለሁለት ከተከፈለ በኋላ (ኤርትራ እና ትግራይ ማለቱ ነው)፤ ኩፉኛ ተዳክሟል። ትግሬዎች ለመዳከም የመጀመሪያ ተጠያቂዎች አድርጐ የሚያቀርባቸው አነዚያ አፄ ዮሓንስ ከሞቱ በሗላ የመጡ የሸዋ ገዢ መደቦች ናቸው።” ይላል። የማነ ገብረመስቀል።
ይህንን በተመለከተ “ዶ/ር ክንፈ አብርሃምም” እንዲህ ይላል፤-
“በእርግጥም ትግርኛ ተናጋሪ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች በተንኰል እርስ በርሳቸው በመከፋፋል እና በማዳከም በትግርኛ ተናጋሪ ሕዝቦች በኩል ሲነሱ የነበሩ ተቃውሞዎች ለመቆጣጠር ይጠቀሙባቸው ነበር።” ክንፈ አብርሃ (ዘኒ ከማሁ)፤
በመጨረሻ የማነ አንዲህ ይላል።
“ የትግራይ ሕዝብ በ19ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ጀምሮ “ብሔራዊ ማንነቱ እና የፖለቲካ መንበሩ እየተሸረሸረ በመሄዱ በተለያየ ጊዜ እና ቦታ ፀረ-ሸዋ ገዢ መደቦች ተቃውሞውን አሳይቷል። የመጀመሪያው ማለትም “የቀዳማይ ወያነ አብዮትም” ለዘመናት “ጸረ ብሔራዊ ጭቆና እና የበታችነት ስሜት” በላዩ ላይ የጫኑበትን የሸዋ ገዢ መደቦችን ለመጣል የታገለበት ሕዝባዊ አመጽ አንደነበረ ነው ብዙ ተማራማሪዎች የሚገልጹት” ሲል የማነ ገብረመስቀል፤ ለትግራይ ብሔረተኛ ስሜት መነሻው እና መቸ እንደጀመረ (ማለትም በእንደርታው አብየዝጊ እና በይኩኖ አምላክ ጀምሮ ማለት ነው) ሊገልጽልን የሞከረው።
እንዲሁም የወያኔው መስራች እና የሽምቅ ተዋጊው ሃይል የጦር መሪው የነበረው ወዳጄ ዶ/ር አረጋዊ በርሄም በበኩሉ አንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል።
“የትግሬዎች ብሔራዊ ጥያቄ፦ ለረዢም ጊዜ የነበረ እና ስር የሰደደ የራሱ ተጨባጭ ምክንያቶች ይዞ ሲጓዝ ቆይቶ የተነሳ ነው። በተለይም የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖለቲካ ከትግራይ ከተነሳ በኋላ፤ በውስጥ መሰሪ ተንኰል (“በሸዋ ገዢዎች”) እና በውጭ ጣልቃ ገብነት፤ ከትግራይ ገዢ መደቦች መዳፍ ወጥቶ ወደ አማራ ገዢ መደቦች ከገባ በኋላ የትግራይ ገዢ መደቦች ከነበራቸው የፖለቲካ ሥልጣን እየተገፉ ከመጡ በኋላ ነው “የትግራይ ብሔራዊ ጥያቄ መነሳት” የጀመረው። ዛሬም ቢሆን ማዕከላዊ የፖለቲካ ሥልጣን አሁን ካለበት ተነሥቶ ወደ ትግራይ መዛወር አለበት የሚል እምነት ያለቸው አሁንም በርካታ የትግራይ ተወላጆች አሉ።” (Aregawi Berhe: 2008) Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilization in Ethiopia. P45)
አንግዲህ የትግራይ ብሔረተኞች መነሻ ጥያቄ ባጭሩ፦
(1) ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የነበረው የትግራይ የሥልጣን የበላይነት በሸዋዎች ተነጠቀ፤
(2) ከሸዋ እና ከመሳሰሉ አማራ ተወላጆች ወደ ትግራይ አስተዳዳሪ አድርገው በመሾም ጥንት የነበረ ‘ፍትሕ እና ሰናይ አስተዳዳር’ አንዲፈርስ ተደርጓል፤
(3) የትግራይ ታሪካዊ ቅሪቶች እና ባሕላዊ እሴቶች ተዳክመዋል፤
(4) ከፍተኛ የትግራይ መኳንንት እና ባላቦቶች እስር ቤት አንዲማቅቁ ወደ አንኰበር እና ጋሞጐፋ ተወስደው ለሞት ተዳርገዋል።
(5) የትግራይ ሕዝብ በአማራዎች በምጣኔ ሐብት ከሌሎች ጐሳዎች በተለየ መልኩ አንዲደኸይ፤ ቋንቋው አንዲረገጥ ተደርጓል……ወዘተ….ወዘተ…
የሚሉ አበይት ምክንያት የሚሏቸው አነኚህ ቢሆኑም።
ለትግራይ ብሔረተኛነት ስሜት ዓይን አውጥቶ ምክንያት ሆኖ ቀዳሚ መከራከሪያቸው ሆኖ የቀረበው ግን ‘ሥልጣን ከትግራይ ማዕከል ወጥቶ ወደ ሸዋ መግባቱ” የትግራይ ብሔረተኞች ስሜት ተነክቷል። በመሖኑም በቁጭት ተመልክተው ከሸዋ/ ከአማራ ጋር ቅራኔ ያስገባቸው ዓይነተኛው ምክንያት ግን እስካሁን ድረስ ያልተፈተሸ ለመጀመሪያ ጊዜ “ወያኔዎች እና እኔ ብቻ” የፈተሽነው በአንድ የጥንት ትግሬ ጸሐፊ ተጽፎ የተገኘ ሰነድ ይህ የሚከተለው ዓብይ ምክንያት ነው።
ዮሐንስ ከመቱ በሗላ በ1882 ዓ.ም ታሕሳስ ወር ውስጥ ምኒሊክ የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ እና ትግራይን ለማረጋጋት በርካታ ሰራዊታቸውን ይዘው ወደ ትግራይ ዘመቱ። በወቅቱ በሕይወት የነበሩት የአፄ ዮሐንስ እህት የሆኑት ወ/ሮ (እቴጌ ) ድንቅነሽ የወንድማቸው ዙፋን በሸዋ እጅ በመግባቱ የሚከተለው የቁጭት እና የንቀት ግጥም በትግርኛ ገጠሙ፦
ጹሑፉ እንዳይራዘምብኝ ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጐምኩትን ብቻ ላቅርብ፡ እንዲህ ሲሉ ለምኒልክ ገጠሙላቸው፡
አንደምን አለክ
ንጉሥ ሆይ፤ ንጉሥ ምኒልክ
ያመጡልን ነበር ቅቤ ማር በትዛዝ፤
ያመጡልን ነበር ላም በሬ በትዛዝ፤
አልነበሩም ወይ የዮሐንስ ታዛዥ?
ይታዘዙ ነበር ብለው እጥፍጥፍ፤
ለጥ ሰጥ ብለው አንዳጎዛው ምንጣፍ።
ዮሐንስ ግን ሲሞት አንደዋዛ፤
ተደብቀው ቆይተው በሽምዛ (ሽምዕዛ ቤተክርስትያን አካባቢዎች ትግራይ ውስጥ የሚበቅል ለመደበቅ የሚያመች አጠር ያለ ቅጠል የበዛበት ዛፍ ነው)
ሰተት ብለው ገቡ አንደዋዛ።
ለመሆኑ ዛሬ ምን አመጣዎት
‘ሰተት ብለው ገቡ ሰው በሌለበት ቤት?”
በማለት ተቃውሞአቸውን ገልጸው ነበር።
ምኒልክ በ1882 ዓ.ም ወደ ትግራይ ሲመጡ፤ የዮሐንስ ዘሮች የሆኑ መሳፍንቶች እና ተወልጄዎቹ አንዲህ ባለ ተቃውሞ ሲገልጹ፤ ሕዝቡስ ምን ዓይነት ስሜት እና ቅሬታ አንጸባርቆ ነበር?
/ ክፍል ሦስት … ይጥላል።/
🥇🥈🥉
• ሙሉ ጥናታዊ ጽሑፉን ከድረገፅ ላይ ለማንበብ ለምትሹ፥ በሚከተለው አድራሻ ይገኛል፦
• የጥናት ጽሑፉን በpdf ለማግኘት ለምትሹ፥ በቀጣዩ አድራሻ ይገኛል፦
ለጥናታዊ ጽሑፉ አቅራቢ – ለእውነተኛው ምሁር ጌታቸው ረዳ – (Ethiopian Semay:  http://ethiopiansemay.blogspot.com/  ) አሁንና በቀሪው ክፍል ለማቀርበው የጥናት ፅሑፉ እና ስለ ሀቅ ሲል ለተላበሰው የሕሊና ብርታት በድጋሚ የከበረ ምስጋናዬን ከአድናቆት ጋር በአክብሮት አቀርባለሁ።
ክፍል ሦስት ይቀጥላል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ።
ቸር ሰንብቱልኝ።
Filed in: Amharic