>
5:13 pm - Saturday April 20, 2667

የትግራይ ባንዳዎች!!! (ናትናኤል አስመላሽ)

የትግራይ ባንዳዎች!!!
ናትናኤል አስመላሽ
ከትግራይ የበቀሉ በጣልያን ጊዜ የነበሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች አያት እና አባት ባንዳ መኖራቸው ለማንም ድብቅ አይደለም፣ ከመለስ ዜናዊ አያት እስከ ስብሓት ነጋ አባት። እነዚህ የባንዳ ልጆች የስልጣን ባለቤት ሲሆኑም እሳቸውን የሚመስሉ ባንዳዎች ትግራይ ውስጥ ፈጥረዋል፣ የዘመኑ የትግራይ ባንዳዎች ደግሞ  የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ በጠላትነት የሚፈርጁ፣ የቂም በቀል እና የጥላቻ አባት እና መምህራን የሆኑ፣ መምህር ገብረኪዳን እና መምህር ሙሉወርቅ ናቸው።
.
ሁለቱም በህወሓት ታሪክ ውስጥ ላባቻወ ጠብ ያላደረጉ ናቸው፣ የትግራይ ወጣት ደደቢት ገብቶ ሲዋጋ እና ደሙ ሲፈስ እነዚህ ባንዳዎች አስመራ እና አዲስ አበባ ተደብቀው ነበር! ትናንት የ፸ እንደርታው ጀግና ነብዩ ስሑል ሚካኤል ሃተታ ፸ እንደርታ የሚል መፅሃፉ ሲያስመርቅ ባንዳነታቸው በደምብ አስመስክረዋል። ሁለቱም የዘመኑ ባንዳዎች ባንዳ ከመሆናቸው በፊት ከዚህ ቀደም በነብዩ የተፃፈ መፅሓፍ አስመርቀዋል፣ ዘንድሮ ነብዩ በህወሓት ታስሮ ተደብድቦ ከወጣ ቦሃላ እሱንም እንደ አማራ ህዝብ በጠላትነት ፈርጀው ህወሓትን ፈርተው በመፅሓፉ  ምርቃት ላይ አልተገኙም።
.
ባንዳዎች እስካሁን ድረስ በትግራይ የተፃፉ ህወሃትን የሚያሞጉሱ መፅሓፍቶችን  እና የ አማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የሚያጣጥሉ መፅፋቶች ማስመረቅ እና ከፊት መታየት ጀግንነት ሲያደርጉት ቆይተዋል፣ ትግራይ ትግራይ ሲሉን ከርመው ስለ ፸ እንደርታ ታሪክ ሲፃፍ ግን ወንጀል ሆነ እና ቤታቸው ውስጥ ተደብቀው ተቀምጠዋል።በነሱ ሂሳብ የ፸ እንደርት ታሪክ የትግራይ ታሪክ አይደለም ማለት ነው፣ ስብሓት ነጋ “ትግራይ ማለት ዓድዋ አኽሱም እና ሽሬ(አሽዓ)” ብቻ ነው እንዳለው ማለት ነው።  ብዛት ያለው ወጣት ፍራቻውን ሰብሮ በምርቃቱ ላይ ተገኝተዋል፣ ነብዩም ቀጣዩ የ፸ እንደርታ ብላታ ሃይለማርያምነቱን አስመስክረዋል።
.
ፈይስቡክ ላይ ቀን ከለሊት የሚፅፉ የትግራይ አክቲቪስቶቭ በፍራቻ እንካንስ በምርቃቱ ላይ ሊገኙ በገፃቸው እንካን ስለ ነብዩ መፃፍ አልቻሉም። አማራ ጠላታችን ነው ኦሮሞም ጠላታችን ነው የሚያዋጣን መገንጠል ብቻ ነው ለማት ግን ማን ይቅደማቸው። የትግራይ ህዝብ ከህወሃት አገዛዝ ነፃ እንዳይወጣ እንቅፋት የሆኑት ደግሞ ተምረናል የሚሉ ባንዳዎች ናቸው። የ፸ እንደርታ ወጣት ካሁን ቦሃላ ለህወሓት የተቀበረ ፈንጅ ሆኖባታል፣ በፍራቻ ቤቱ የተቀመጠ ግን ደግሞ የህወሓትን ሞት የሚመኝ አብዛኛው የኢፈርት ሰራተኛም አንድ ቀን ፍርሃቱን ይሰብረው እና ህወሓትን በቁምዋ ይቀብራታል፣ ጊዜ ለኩሉ፣ ይህ አልፎ ባንዳዎች በታሪክ የሚጠየቁበት ጊዜ ቅርብ ነው። ስለ አፄ የውሃንስ ኢትዮጲያዊነት የሚያጣጥሉ ባንዳዎች፣ ስለ ኢትዮጲያ የሚዘምር የ፸ እንደርታው ጀግና ነብዩ በጥላቻ ቢያዩትስ ለምን ይገርማል!
Filed in: Amharic