>

ዘረኛው፣ ሙሰኛው፣ ሞራለ ቢሱ የአድዋው ዶ/ር መንበረ ጸሀይ ታደሰ በጓሮ በር ተመልሶ መጥቷል!!! (ብሩክ አበጋዥ)

ዘረኛው፣ ሙሰኛው፣ ሞራለ ቢሱ የአድዋው ዶ/ር መንበረ ጸሀይ ታደሰ በጓሮ በር ተመልሶ መጥቷል!!!
ብሩክ አበጋዝ
እያንዳንድህ የጠሚ ዓቢይ አድናቂ የሆንክ ኦሮሞም ሆንክ ደጋፊና ተቃዋሚ አማራ በዚህ ሠዓት ትህነግ ከፖለቲካ አጋሮቿ ጋር የምታደርገውን ነገር እያየህ የፖለቲካ መስመሩ ካልገባህ ደንዝዘሃል ለማለት እገደዳለሁ።
.
28 ዓመት ሙሉ ሲገድለን፣ ሲፈልጠን፣ ሲያስረን ሲያንገላታን የነበረው ትህነግ  ዳግም ወደ ስልጣን ለመምጣት ከተገንጣይ ኦሮሞ ጽንፈኞች እና ያረጀ ያፈጁ ሌሎች ፖለቲከኞች ጋር ደፋ ቀና ሲል እኛ አሁንም የፖለቲካ መላቅጡ ጠፍቶን ቆሞ ተመልካች ሆነናል።
በተለይ ከአማራው በኩል ይኼን የሚገነፍል ወጣት በተሳሳተ መንገድና እሳቤ በመምራት ቁዘማ ውሰጥ እንዲገባ ከማድረግ ይልቅ ወቅታዊና ተጨባጭ የፖለቲካ አሰላለፎችን ብጥርጥር አድርጎ ተንትኖ ለሕዝቡ ጠቃሚ አቅጣጫ የሚያሳዩ ጥቂት ሰወች መጥፋታቸው እጅግ የሚያበሳጭ ነገር ነው። ትህነግ እየቆፈረ ያለውን ጥልቅ ጉድጓድ ባለመረዳት አሁንም የጠሚ ዓቢይ መንግስትን ድክመትና የሚሰራቸውን ስህተቶች እየቆጠሩ እነሱኑ ማጮህ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሜዲያወችና አክቲቪስቶች የዘነጉት ነገር ትልቁንና ለመምጣት ዳር ዳር እያለ ያለውን ዋና ጠላት ነው።
.
እያንዳንዱ ወገን የተፎካካሪ (የተወዳዳሪ) ትንተና አድርጎ በቅደም ተከተል የትኛውን ቀድሞ መዋጋትና ማሸነፍ እንዳለበት ካልተረዳ ገና አሁንም የማንም መጫወቻ መሆናችን አይቀርም። ከሁሉም የሚቀድመው ግን አሁን በሀገሪቱ ላይ ያለውን የፖለቲካ አሰላለፍን በጥንቃቄ መረዳት መቻሉ ላይ ነው። ትህነግ መቀለ ላይ ባደረገው ስብሰባ የውግዘት መዓት እየደረሰበት ያለው ADP እና ODP ናቸው። ለዚህ ውግዘት ተባባሪ ሆነው የቀረቡት ደግሞ የእነ ጃዋር አንጃ እና ሌሎች አሮጌ ፖለቲከኞች መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል።
.
ጃዋር ከኦዴፓ ባለስልጣናት የተወሰኑት ጋር ሊሞዳሞድ ይችላል፣ ጃዝ እያለ እያስፈራራም ጉዳዩን ሊያስፈጽምና መረጃ ሊቀበልም ይችላል፣ ኦዴፓወችም ህዝብ ሊያሳምጽ ይችላል በማለት እሱ የሆነ ነገር ባለቁጥር ሊደናበሩ ይችላሉ ነገር ግን አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን ያለብን ጃዋር የእነ ጠሚ ዓቢይን መንግስት አሽቀንጥሮ ለመጣል ከፍተኛ ጥረት እያደረገና ከትህነግ ጋር በአንድ ላይ አጀንዳ እየተቀባበለ መሆኑ ላይ ነው።
.
እነ ጃዋርና መሰል ጽንፈኞች ጠሚ ዓቢይን የአማራ አጀንዳ አስፈፃሚ እያሉ ፕሮፖጋንዳ እየሰሩበት ነው፣ እነ ደረጀ ገረፋ የኦዴፓ ደጋፊ ነን በማለት የሚጽፉትን ተቃውሞ አስተውለህ ካላየህና የእነ ጠሚ ዓቢይና የጽንፈኛው ጃዋር አንጃ ልዩነት ካልገባህ ደንዝዘሃል ማለት ይቻላል። ትህነግ ስልጣን ለመያዝና ፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የምትችለው ኦሮሞውንና አማራውን በማጋጨት ነው፤ ይኼ ዘመን የማይሽረው አቅጣጫዋ ነው። ይኼን አቅጣጫዋን የሚከሽፍበት መንገድ እንዴት ነው የሚለውን ሁልህም ወደ ራስህ ተመልሰህ አስብ።
.
የጠሚ ዓቢይ መንግስት ብዙ ስህተቶችን እየሰራ አሳዛኝ ውሳኔዎችንም እያሳለፈ እየተመለከትን ነው፤ ይኼን መካድ የማንችለው በየቀኑ እየተፈጸመ ያለ ነገር ነው። ይኼን መተቸት፣ መገሰጽና እንዲስተካከል ለማድረግ ከመታገል ጎን ለጎን ግን ትህነግ እና አክራሪና ጽንፈኛው የኦሮሞው አንጃ የሚያደርጉትን ነገር መታገል እና የእነሱ መሳሪያ አለመሆንም ግዴታ ልናደርገው ይገባል።
.
ጠሚ ዓቢይን በኢትዮጵያዊ አንድነት አመለካከታቸው ልንጠራጠራቸው አይገባም አድሎ ምናምኑ ሊኖር ይችላል። አማራ ተብሎ እንኳ ጎንደር ጎጃም እየተባለ ስንት ነገር እየተሰራ እያየን ያኛው ሊገርመን አይገባም። ምንም እንኳ ትክክል ያልሆነ እና መታገል ያለብን ነገር ቢሆንም፤ ያለውን ስህተት እየነቀፉና እየታገሉ ሌላኛውን ጭራቅ ግን አርቆ መቅበር አስፈላጊ ነው። በተለይ አንዳንድ ከትህነግ ጋር መደራደርና ተነጋግረን አብረን መስራት እንችላለን የምትሉ ቂላቂሎች ይህን የሞኝ እሳቤያችሁን ወዲያ በሉት።
.
ለማንኛውም 28 ዓመት ሕገ መንግስት ሲጥስ፣ የፌድራል መዋቅሩን እንደፈለገ ሲያበላሸው የነበረው ትህነግ ለህገ መንግስትና ለፌድራሊዝም ጠበቃ ሆኖ ባለፈው 27 ዓመት ሁሉም ነገር ጥሩ እንደነበርና አሁን ባለፈው 1 ዓመት ብቻ እንደተበላሸ ያለ ሀፍረት ሲደሰኩር እየሰማን ዝም ማለታችን አስነዋሪ ነው። ዝምታው በተለይ አስነዋሪ የሚሆነው በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ዘረኛ፣ ሙሰኛ፣ ሞራለ ቢስ የአድዋው ዶ/ር መንበረ ጸሀይ ታደሰ ህገ መንግስቱ የረቀቀበት መንገድ ቅቡልነት ያለው ሲል ሰውየውን የምታውቁ የህግ ባለሙያወች ዝም ማለታችሁ ነው።
.
ዶ/ር መንበረ ጸሀይ ታደሰ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል በነበረ ጊዜም ሆነ የህግና የፍትህ ጥናት መስሪያ ቤት ኃላፊ በነበረ ጊዜ ሲሰራውና ሲያደርገው የነበረው ሳያሳፍረው አሁን በመድረክ መጥቶ የተበላሸውን አሮጌውን ጨካኝና ገዳይ ሥርዓቱን ለመመለስ ሲቀባጥር ልክ ልኩን መንገር ሲገባን ዝም ማለታችን አሳዛኝ ነው። በተለይ ደግሞ አሳዛኝ የሚሆነው የዚህን ሰው ሙስና፣ ወንጀል እያወቃችሁ የእሱ የዘረኝነት በትር ላረፈባችሁ የህግ ባለሙያወችና ዳኞች ነው።
.
መንበረ ጸሀይ ታደሰ ልጁ የምትሆን ሉዋም አሰፋ የምትባል ሴትን (ምኑ እንደሆነች ፈጣሪ ይወቅ 😜) ከጠቅላይ ፍርድቤት ተሿሚነት ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በውሽምነት ይዞ ውጭ ሀገር ድረስ እንድትማር በማድረግ እሱ መስሪያ ቤት ሲቀያይር አብሯት የሚዞር አሁንም በእሷ ስም ጥብቅና ፈቃድ አውጥቶ ብር የሚሰበስብ ሞራል የለሽ ሰው ነው። ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ተነስቶ ወደ ህግና ፍትህ ጥናት መስሪያ ቤት ሲመደብ ይቺኑ ሉዋም የምትባል ጸሀፊውን አብሮ አዛውሮ ክፍያዋን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ መደብ ዝቅ ስለሚል በፕሮጀክት መደብ ተመድባ ከፍ ያለ ክፍያና መኪና ጥቅማ ጥቅም እንድታገኝ ሲያደርግ ነበር።
.
የጠሚ ዓቢይ መምጣትን ተከትሎ ከስልጣን ሲነሳ ይቺኑ ሉዋምን ከመስሪያ ቤቱ እንድትለቅ አድርጎ የጥብቅና ፍቃድ እንድታወጣ በማድረግ እሱ ራሱ ፈቃዱን እየነገደበት ይገኛል። እሱ ራሱ ፈቃድ ማውጣት እየቻለ በእሷ እንዲወጣ ያደረገው መንግስት ለጡረተኞቹ የሚሰጠው እጅግ ከፍተኛ ጥቅማጥቅምና ቤት እንዳይቀርበት ነው። መንበረጸሀይ ለዳኞችና ለአቃቢያን ሕግ ስልጠና የሚያገለግል ግንባታ በካናዳ መንግስት ድጋፍ ሲሰራ የሚሰራው ስልጠና ተቋም የዳይሬክተሩ ቢሮ ለሚሆን ቢውልዲንግ ማሰሪያ የሚሆነውን ገንዘብ ቅርጥፍ አድርጎ የበላ ሙሰኛ ነው።
.
የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞችን ጣልቃ እየገባ እንደፈለገ ሲያወጣና ሲያወርድ፣ ከመለስ ዜናዊ ጋር እየተነጋገረ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሲያባርር፣ ጣልቃ ሲገባና ፍርድ ቤቱን መጫወቻ ሲያደርግ የነበረ፣ ዳኞችን ሲያሸማቅቅ የነበረ በተለይ እንደ ዓሊ መሀመድ ዓይነት ምርጥ ዳኞችን ቁም ስቅላቸውን መከራ ሲያበላቸው የኖረ ሰው ነው። በዚህና መሰል ሌሎች ምክንያቶች የቀድሞው የፍትህ ሚንስቴር የብአዴኑ ብርሃን ኃይሉ በመሞገቱ ምክንያት ከስልጣኑ ተነስቷል።
.
እንዲህ ዓይነት አስቀያሚ ሪከርድ ያለው ግለሰብ ስለ ህገ መንግስትና ህግ ሲያወራ ቢያንስ እንኳን የግፉ ሰለባ የሆናችሁ ዳኞችና የህግ ባለሙያወች ዝም ማለታችሁ እጅግ አሳዛኝ ነው። የድሮው ዝምታ በአንባገነን መዳፍ ስር እየተዳደርን ስለነበር ግዴለም ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ሰው ሞራል ኖሮት ወደ መድረክ ወጥቶ ህግና ህገ መንግስት ሲል ዝም ማለታችሁና ህሊናችሁ መቻሉ አስገራሚም አሳዛኝም ነው።
Filed in: Amharic