>
5:13 pm - Tuesday April 19, 6591

"ወንዝ አያሻግርም" የተባለው አማርኛ ከኢትዮጵያ በ15,960 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው ቶንጋ ምድር ላይ ደምቆ ዋለ!!! (ታዬ ቦጋለ አረጋ)

ወንዝ አያሻግርም” የተባለው አማርኛ ከኢትዮጵያ በ15,960 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው ቶንጋ ምድር ላይ ደምቆ ዋለ!!!
ታዬ ቦጋለ አረጋ
የሀይማኖት ሊቃውንት የሰው ልጆች ቋንቋ አንድ እንደነበረና በኃጢአት ምክንያት ባቢሎን ላይ መቀላቀሉን ያስተምሩናል። የቋንቋ ሊቃውንት ደግሞ – ቋንቋ ዋነኛው ጥቅሙ መግባቢያነት እንደሆነ ይገልፁልናል። በዚህ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ። እንስሳት በደመነፍስ በመጠኑ ከመናበብ ባለፈ – መች በጠረጴዛ ዙሪያ  መወያየት ይችላሉ?!
*
ብሪታንያ በ19ኛው ክፍለዘመን ማብቂያ ሩብ የሚሆነውን የመሬት ክፍል በቅኝ ግዛት መዳፏ ስር አስገብታ – “The sun never sets on the British empire” በሚል እብሪት ተስፋፍታ ዛሬ የቋንቋው ተናጋሪዎች ብዛት ከቻይናው መንደሪን ቋንቋ ለጥቆ ሁለተኛ ቢሆንም – የዓለማችን Lingua franca በመሆን እያገለገለ ይገኛል።
(በቅኝ ግዛት ቀንበር ይማቅቁ የነበሩ ሀገሮችም ሆኑ መላው ዓለም እርስበርስ ይተሳሰርበት ዘንድ ብልህ ውሳኔ ወስኗል። የአፍሪካ ህብረትም እንግሊዝኛን ከመነጋገሪያ የሥራ ቋንቋዎቹ አንዱ አድርጎ – አብዛኛው ጆሮው ላይ ‘ማሺን’ ሳይደቅን ይገለገልበታል።)
“የዓለማቀፉ የጤና ተቋም ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም  በሃገረ ቶንጋ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በተጓዙበት ወቅት –  የሃገሪቱ ህፃናት ተማሪዎች በወል በምንደምቅበትና በሠፊ የፍቅር መስተጋብር የእኛ የወል በሆነው ቋንቋ አማርኛ፦
 “እንኳን ደህና መጡ” የሚል ፅሁፍ ይዘው ተቀብለዋቸዋል።
*
ዶክተር ቴዎድሮስም በአፀፋው የሚከተለውን ብለዋል፦
“ሃገረ ቶንጋ ከሀገራችን በ15,960 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በፓስፊክ ውቅያኖስ ትገኛለች። ይሁንና ተማሪዎቹ ስለ ሃገራችን ብዙ ነገር አውቀው ነበር የጠበቁኝ። ያልጠበቅኩትና ያስደሰተኝ ነገር – ኢትዮጵያ ሃገራችን በቶንጋ። “
*
ወደ ዋናው መልዕክቴ ልመለስ፦ ዓለም እንዲህ ርቃና ረቅቃ በሌሎች ቋንቋዎች ፍቅርን ስትለዋወጥ እኛ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ትንቢት መፈፀሚያ እንዳንሆን፦
“የመጣነው ጉዞ ያሳዝናል
አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል”
አስብና ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ሀገር የዱኣ የምህላ የጸሎት የስግደት  የአብሮነት ምድር እንደሆነችና – የመላውን ኢትዮጵያዊ የልቡና ውቅር ተዟዙሬ ስላየሁ – ሀገሬ እምዬ እናቴ – ሊያፈርሷት የሚተጉ እንደ አቦሸማኔ ሲወረወሩ = እንደ ንሥር የሚታደሱና Frog Perspective ሳይሆን (Normal, Bird, Side and Frog Perspective) አጣምረው የሚንተገተጉ ልጆች ስላሏት – አንድነቷ ተጠብቆ እንደሚኖር ፅኑ እምነቴ ነው።
Filed in: Amharic