>

ደቡብ ግሎባል ባንክ 4.8 ሚሊየን ብር ተዘረፈ! የተዘራፊ ባንኮቻችንን ቁጥር 22 ደርሷል ( ኤልያስ መሰረት)

ደቡብ ግሎባል ባንክ 4.8 ሚሊየን ብር ተዘረፈ!
ኤልያስ መሰረት
* የለሊቱ ዝርፊያ የተዘራፊ ባንኮቻችንን ቁጥር 22 አድርሶታል!!!
 
ትላንት ለሊቱን የደቡብ ግሎባል ባንክ “ጀሞ ቅርንጫፍ” ተዘርፎ ማደሩን ከባንኩ ሰራተኛ ለመስማት ችለናል። ይህንን መረጃም ባንኩ አረጋግጦልናል። ከባንኩ ባገኘነው መረጃ መሰረትም ዝርፊያውን ፈፅመዋል ተብለው ከተጠረጠሩ የባንኩ ጥበቃዎች መካከል አንደኛው ሲይዝ የተቀሩት እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋሉም።
የተዘረፈው የብር መጠን ስንት ይሆን? ብለን ጥያቄ ያቀረብንለት የባንኩ ሰራተኛ ትላንት ከ300,000 ብር በላይ መግባቱን ነግሮን የተዘረፈውን አጠቃላይ ገንዘብ ግን አጣርቶ እንደሚነግረን ገልፆልናል። ተመሳሳይ ጥያቄ ለሚመለከትው ክፍል አቅርበን ይህን ብለውናል: “የሚያሳየው Balance 4.8 ሚሊየን ብር ነው። ከዛ ውስጥ ትንንሽ ቁጥር ያለው ገንዘብ ነው የቀረው።” ዝርፊያው ካዝና በመስበር የተፈፀመ እንደሆነ ነው የሰማነው!
በቅርቡ የኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ ለቡ ቅርንጫፍ መዘረፉም ይታወቃል።
Filed in: Amharic