>
5:13 pm - Thursday April 20, 4254

ወለጋም ተራበ፤ ህፃናትም በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው !!! (ዘመድኩን በቀለ)

ወለጋም ተራበ፤ ህፃናትም በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው !!!
ዘመድኩን በቀለ
እዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ትኩሳት
       ወገኔ አለቀ በረሃብ እሳት
                 *★★★*
•••
ብዙ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በዚያ በ1977 ቱ የረሃብ ዘመን ከወሎ ተነስተው ወለጋ እንዲሰፍሩ ነበር የተደረገው። ወለጋ የምዕራብ ኢትዮጵያ ፈርጥ ነው። ወለጋ ለም ነው። ወለቃ የወርቅ ሀገር፣ የበቆሎ የቡና ሀገር ነው። ወለጋ በበረከት በመትረፍረፍ ነበር የሚታወቀው።
•••
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን “ ሁሉ ነገር ኬኛ ባዮች እንደ እንጉዳይ ፈልተው “ የወለጋን ስም አጠለሹት። ወሎዬዎች ከሀገራችን ይውጡ፣ መሬታችንን ይልቀቁ፣ በማለት በወገኖቻቸው ላይ ግፍ ሲሠሩ ታዩ። ይሄ የወለጋ ደንቡም ባህሉም አይደለም። አልነበረምም። ወሎዬዎችን ከኦሮሚያ ውጡ እያሉ ወሎን ኬኛ ማለትም ደግሞ የሌለ የባሰ ነውር ነገር ነበር። ብዙዎችም በዚህ አዝነዋል።
•••
በወለጋ አንድ ህንዳዊና አንድ ጃፓናዊን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን በጥይት ተመተው፣ በእሳትም ከነ መኪናቸው የተቃጠሉትም በዚሁ ባሳለፍነው ዓመት በወለጋ ነበር። የአልሸባብ፣ የአይኤስአይኤስ ጠባይና ባህል በወለጋ የታየውም በዚሁበወለጋ ነበር። ምላሳቸው ተቆርጦ፣ በጥይት ተደብድበው በአደባባይ የተረሸኑት የኦህዴድ የደኅንነት ኃላፊም የተገደሉት በዚሁ በወለጋ ነበር። በእውነት ይሄ ታላቅ ቁጣን በምድሪቱ ላይ የሚጠራ ጭምር ነበር።
•••
የህወሓቱ አግአዚ ከመሞቱ በፊት ልጅን ገድሎ እናትን በልጇ አስከሬን ላይ ያስቀመጠውም በዚሁ በወለጋ ነበር። የደም መሬት፣ የግፈኞች መፈንጪያም ሆና ነበር ወለጋ።
•••
ከ18 በላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተዘረፈውም በዚሁ በወለጋ ነበር። የዐማራ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች የለፉ፣ የደከሙባቸው የደረሱ ማሳዎቻቸውም በእሳት የተቃጠሉት፣ ጎተራዎቻቸውም የነደዱት በእዚሁ በወለጋ ነበር።
•••
ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ እንኳ “ወለጋ ሄጄ ብገደል የኦሮሞ አንድነት ይላላል፣ ሌላ ክልል ሄጄ ብገደል ግን የኦሮሞ አንድነት ይጠነክራል፣” ብለውም ኢትዮጵያን እየመሩ እንደ ኦሮሞ በማሰብ ራሳቸው ላይ ሟርት ያሟረቱት በዚሁ በወለጋ ያለው ሁኔታ አስፈርቷቸው እንደነበር ይታወሳል።
•••
ወለጋ ራሱን የቻለ ክልል እንዲሆን የሚታገሉ እንደነ ጃል መሮ ያሉ ታጋዮችም ከነ ሠራዊታቸው ያሉት በወለጋ ነው።  የእነ ጃዋር ጀሌዎች “ኢጆሌ ሚሺኖታ ” እያሉ በሃይማኖታቸው ምክንያት ብዙዎቹን ወለጌዎች እንደሚያገሏቸውም ይነገራል። ወደ ማዕከላዊ መንግሥት ብዙም አያቀርቧቸውም። ልማቱም፣ ፋብሪካውም ናዝሬትና ጅማ ነው ብለው የሚያኮርፉ ወለጌዎች እንዳሉም ይነገራል። እንዲያውም ወለጋ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ጎጃሜ ነውም እያሉ ሲገፏቸውም ይደመጣል።
•••
ለማንኛውም አሁን ወለጋ ተርቧል። ባሌም ረሃብ አለ ተብሏል። መጸለዩ እንዳለ ሆኖ ላለፈው በደል ንስሃ እየገባን በራብ ለሚያልቁት ወገኖቻችን በቶሎ ልንደርስላቸው ይገባል። በተለይ ህፃናት መሞት የለባቸውም። በፍጹም መሞት የለባቸውም።
•••
እነ ጃዋር መሃመድም ቢሆኑ የአሩሲ፣ የባሌና የሀረር እስላም ኦሮሞዎች ሲራቡ ብቻ አይደለም ጎ ፈንድሚ ማሰባሰብ። ክርስቲያኑ ወለጋ ኦሮሞም እንዲህ ሲራብ መንቀሳቀስ አለባቸው። OMN ም ዝም ማለት የለበትም። ከርስቲያን እስላም እየተባባላችሁ መለያየት ሳይሆን ኦሮሞ ነን ካላችሁ ወለጋንም መርዳት አለባችሁ። ይሄ ምክሬ ነው።
•••
የዐቢይ አስተዳደርም ቢሆን  ወለጋ ብሄድ ይገሉኛል ብሎ ከመንቦቅቦቅ፣ ምግብ የማይሆን ስታዲዮም ሠርቻለሁ ብሎ ሾው ከመሥራት ይልቅ ረሃብ እየገደላቸው ለሚገኙት የወለጋ ኦሮሞዎች በአስቸኳይ ሊደርሱላቸው ይገባል። ረሃብ ጊዜ አይሰጥም። በራብ ከመሞት በጦርነት መሞት ይሻላል እንዲሉ ሐዋርያት። እናም ወገን እንተባበር። እንደማመጥ።
•••
ደግሞ አንተ እኮ ኦሮሞ ስለሆንክ ነው እንዲህ ለኦሮሞ የምትጮኸው በለኝ አሉህ። ወዳጄ እኔ ጽድት ጥርት ያልኩና ህወሓት እንደሰጠችኝ እንደ መታወቂያዬ ሳይሆን እንደ ፓስፖርቴ የምኖር ኢትዮጵያዊ ነኝ።
ያ ኦቦሌሶ ዱቢን ከኑማ ጋ ።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ነሐሴ 9/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
እያሉ ነው። በረሃቡ እስከ አሁን 8 ህፃናት መሞታቸውም እየተነገረ ነው የምር 8ተኛው ሺህማ ገብቷል
Filed in: Amharic