>

"...የእኛ ቆብ መድፋት ከንቱ ነው! የጌታን  አደራ በልተናል!!! (ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት)

“…የእኛ ቆብ መድፋት ከንቱ ነው! የጌታን  አደራ በልተናል!!!
ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት
 
* ለእምነታችን እና ለሀገራችን ዋጋ እንከፍላለን ህዝበ ክርስቲያኑና ሀገር ወዳድ የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮችም ለሚወሰደው ርምጃ ከጎናቸው!!!
ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ በቤተክርስቲያኗ ውድመትና ሀገሪቷ ያለችበት አቸጋሪ ሁኔታ በመጥቀስ “ለፓለቲካ ሲባል ቤተክርስቲያኗን ክደናል፤ህዝበ ክርስቲያኑን አስከፍተናል የአባቶቻችን፣ አደራ በልተናል….የሚሉና መሰል መረር ያሉሉ ቃላትን በመጠቀም ስሜታቸውን ገልጸዋል።
ከውጭ ከመጡ አባቶችም ” እኛ ከውጭ የመጣነው የቤተክርስቲያኗን እና የሀገሪቱን መከራ ለመመልከት አይደለም፣ በዶ/ር ዓብይ አስተዳደር ተስፋችን ተሟጧል ፣ የሚሉ የምሬት ድምጾች በስብሰባው ላይ በከፍተኛ እልህ እና ቁጭት ተደምጧል።
“ለእምነታችን እና ለሀገራችን የምንከፍለውን ዋጋ እንከፍላለን” በማለት ህዝበ ክርስቲያኑና ሀገር ወዳድ የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ለሚወሰደው ርምጃ ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።
“ቅድስት  ቤተክርስቲያን ለምዕመኖቿ  በችግራቸው  የማትደርስ ከሆነ የእኛ ቆብ መድፋት ከንቱ ነው። የጌታን  አደራ በልተናል” እያሉ ነው ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳቱ።
ከአመታዊው የቤተክርስትያኗ አጠቃላይ ጉባኤ በፊት  አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሊጠራ  እንደሚችልም ተጠቁሟል።
ለዘመናት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ነፃነት እና ህልውና በሰማዕትነት ያሸበረቀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተወህዶ ቤተክርስቲያን በቆረጡ ሊቃነ ጳጳሳት ለኢትዮጵያ ዳግም ትንሳኤ ከፊት ልትሰለፍ ነው።
በተያያዘም አበው ካህናት እና የቤተክርስቲያኒቷ ሊቃውንት ለመንግስት ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል!!!
 
ጥብቅ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን  
 
እያረደኝ በደሜ የሚሰብከው መንግስት 
-ቅድስት ቤተክርስቲያን ን እንዳቃጠለ አንጾ ያስረክበን
-ይቅርታ ልንጠየቅ፣ ከለላ ሊሰጠን፣ ካሳም ሊከፈለን 
 
እምቢ ካለ ባልጠበቀው ሰአት ለሚፈነዳው አደጋ ይዘጋጅ።
 
ልመና አይደለም ማስጠንቀቂያ ነው!!! 
 
////
 
Filed in: Amharic