>

ወሎንም ሰላሟን ሊያደፈርሱ?!? (ኣብርሃ በላይ)

ወሎንም ሰላሟን ሊያደፈርሱ?!?
ኣብርሃ በላይ
ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ ወሎ ኦሮሞ ነው ሲል “ኧረ! ለካ እብዶች ናቸው ስልጣን የጨበጡት!” ነበር ያልኩት። ወሎ የአማራው፣ የኦሮሞው፣ የአገው፣ የአፋር፣ የትግሬው፣ የሁሉም የፍቅር፣ የሰላም፣ የአብሮ መኖርነት ተምሳሌት ሆና ኑራለች። ወሎ ትንሽዋ ኢትዮጵያ ሆና ኑራለች። (Wollo, like Addis Ababa, has been the microcosm of Ethiopia):: ታድያ ደፋሮች መጡና ወሎ የአንድ ዘር ካምፕ መሆንዋን በድፍረት ነገሩን። መቸም ህዝቅኤል አብይ አህመድን ተማምኖ ነው እንጂ እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ ለድንፋታው “ሙሉ ኃላፊነት እንወስዳለን” ባላለ ነበር። “ባለቤትዋን የተማመነች በግ ላትዋን ውጭ ታሳድራለች” ተብሎ የለ! ወዲህም ተባለ ወድያ፣ የኢትዮጵያ አንድነት፣ የህዝባችን አብሮ መኖርነት የሚፈልግ ዜጋ ሁሉ እነዚህ አገር ሊያፈራርሱ ዘር የማጥራት (ethnic cleansing) ዘመቻ የተያያዙትን ሰዎች መታገል ያስፈልጋል። ዝምታ ማለት ግፉበት ማለት ነው።
በታሪክ ታላቅ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ተብለው የሚታወቁት አብርሃም ሊንከን እንዲህ ብለው ነበር – “All it takes for evil to triumph is for good men to do nothing.” እኩይ ፍጡር የሚያሸንፈው ደጋግ ሰዎች አይተው እንዳላዩ ሲሆኑ ነው”)። ኢትዮጵያ የተደቀነባት አደጋ ግልጽ ነው – ዘገምተኞች ካልሆን! በኢትዮጵያችን እኩይ አስተሳሰብ ማምከን አለብን።
Filed in: Amharic