>

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ፍጥነት የማይታመኑበት ደረጃ መድረሳቸው በራሱ አስገራሚ ነው!!! (ህብር ራድዮ)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ፍጥነት የማይታመኑበት ደረጃ መድረሳቸው በራሱ አስገራሚ ነው!!!
ህብር ራድዮ
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መግለጫ ብዙ ጉዳዮችንም ባይሆን መጪው ጊዜን ያመላክታል። ክህደት እና ማን አለብኝነት ተስተውሎበታል ብለው የሚከራከሩ የመኖራቸውን ያህል ቃላቸውን ተገቢ አድርገው የቆጠሩ ደገፊዎችም አሉዋቸው። ያው ትላንት የሚያለቅስ ሕዝብ እና የሚዘፍን ካድሬ ማየት ብርቅ አልነበረም። የዚህ ድምር ውጤት ደግሞ ሰውዬው የኖረውን ኢህአዴግ በግብር ለመድገም የቆረጡ መሆኑን ያሳያል።ለዚህ አባባል ራሳቸውን የበለጠ የገለጡበትን የትላንቱን መግለጫቸውን በመጠኑ  እንቃኘው።
 ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደወትሮው በቃላት ለመደለል አለመሞከራቸው በቅርቡ ስልጣን አጠናክሬያለሁ የሚል ስሜት የፈጠረው የተለመደ የአምባገነኖች ማምለጫ ስለሆነ ብዙ አያስገርምም።
አቶ መለስ ስለ ጋዜጠኞች ፣የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እና አመራር ምን ሲናገሩ እንደኖሩ ለሚያስታውስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋዜጠኝነት ወንጀል ለመሥራት መደበቂያ አይደለም፣መፈንቅለ መንግሥቱን በቀላሉ አትዩት እና ሌሎችም ጄኔራሎች ሊገደሉ ነበር የሚለው ንግግር ብዙ ያስታውሳል።ስልክ አዳምጠናል የምትለዋ ንግግር ያው እመኑን በማስረጃ ነው ያሰርነው አይነት ማምለጫ ነውና
አሁን ማን ይሙት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ሆነ እነ ስንታየሁ ሸኮል(የሳቸውን የሰኔ 16/2010 የመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ በዋናነት ካስተባበሩት አንዱ እና ከጀርባቸው ተቀምጦ ከዚያ የመግደል ሙከራ ያመለጠ) የባልደራሱ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ መፈንቅለ መንግሥት አድርገዋል፣ባለሥልጣናት ችለዋል ብለው እነሱን እና ተቀናቃኞቻቸውን የሚያሳድዱበትን ያሳምናል ብለው ነው?
አቶ ሀይለማሪያም አስተዳደራቸው ስላሰራቸው ጋዜጠኞች ተጠይቆ የታሰረ ጋዜጠኛ የለም ያሉትን ያስታወሰን የዶ/ር አብይ መግለጫ ጋዜጠኝነት ወንጀል ሰርቶ መደበቂያ አይሆንም ማለት ከዚህ የተለየ አይደለም።
አቅፌ አስረክባችሁዋለሁ ያሉት የአብን መሪዎች ጭምር ባሉበት መድረክ ሲሆን በዋናነት የአብን መሪዎች እና አባላትን ጨምሮ የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት እየታሰሩ ነው።ኦፌኮ እና በኦነግ ስም የተጠረጠሩ ይገኙበታል።በእርግጥ እነዚህ እስረኞች ወደ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።በወታደራዊ ካምፕ አሉ ተብለዋል።ለምን ፍርድ ቤት አልቀረቡም ? ድርጅቶቻቸው ፍርድ ቤት ይቅረቡ ብለው ለምን መግለጫ አይሰጡም?  በአብን ላይ የሚወሰደው እርምጃ በአንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ እንዳይመስል የተሀድሶ ስልጠና ላይ ናቸው የሚሉ አሉ። ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይገባል።ክሳቸው በግልጽ ችሎት ሊታይ ይገባል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእስረኞችን እያያዝ እና የሰብዓዊ መብት ጥበቃውን አስመልክቶ ቃላችንን አላጠፍንም ለማለት ሞክረዋል።እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው የሰጡት ምስክርነት ጨለማ ቤት እና ቀዝቃዛ ክፍል መታሰራቸውን ገልጸዋል።ስለዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለመደ የኢህአዴግ መሪዎችን ቅጥፈት ደገሙት ከማሰኘት የዘለለ ጥቅም የለውም።በዚህ ፍጥነት የማይታመኑበት ደረጃ መድረሳቸው በራሱ አስገራሚ ነው።
የጥፍር አለመንቀልን የአስተዳደራቸው የተሻለ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው የሰሞኑን ሕገ ወጥ እስር ሕጋዊ አያደርገውም።ሳናጣራ አናስርም ያሉትን ቃል አጥፈው ከየመንገዱ ጎትተው ያስገቡዋቸውን ጋዜጠኞች እና የአብን መሪዎች አንዳንዶቹን በብርሃን ፍጥነት በኦሮሚያ ክልል ፍርድ ያሉትን ሲወስኑባቸው የቀሩትን ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ስለ ባልደራስ ፣ስለ አብን ማን ይረዳዋል እንጂ እሳቸው ቢቀላሉ አትዩት ስላሉት መፈንቅለ መንግሥት ምርመራ ብሎ ነገር እንዳልነበር አጋልጠዋል።
በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ መሪዎችን፣መንግስታቸውን የተቹ የአሥራት ቲቪ ጋዜጠኞችን አስረው ስለ ቀጣዩ ምርጫ በጊዜው መደረግ ይናገራሉ።አክሱም እያሉ በቅርቡ ምርጫ የማይደረግባቸውም አገሮች አሉ ያሉትን የረሱት ይመስላል። ምርጫ ላይደረግም ይችላል ብለህ ሰላማዊ የውድድር ሜዳ በማሰርብእና በማሳደድ እየተዘጋ፣ተቃዋሚዎች፣ጋዜጠኞች እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንኳን እየታፈኑ የቆዩት የባልደራስ አባላት እና አመራሮች እስር በእርግጥ ቀጣዩን ምርጫ ከተደረገ የ2007ቱ የኢህአዴግ እሱና ተለጣፊዎቹ የሮጡበትን ምርጫ ለመድገም ይመስላል። ምርጫ በጊዜው የመደረግ ችግር ነው ወይስ ምርጫው ተአማኒ እና ነጻ የመሆን ችግር ነው እስከዛሬ የነበረው የአገሪቱ ችግር? አውቆ የተኛን ካልሆነ የሕዝቡ ጥያቄ ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ ጋር ይያያዛል።
ዛሬም ድረስ ብዙዎች የሚያለቅሱበት እና የሕወሓት እንደ ልቡ የሰብዓዊ መብት የሚጥስበት የራያ እና የወልቃይት የማንነት ጉዳይን በወሰን እና የማንነት ጉዳይ ብለው ባቁዋቁዋሙት መ/ቤት ህንጻ ግንባታ እና  ስብሰባ ጋር ለማያያዝ ሞክረው አልፈዋል። የተጠየቁት ስለ ህንጻ አለመሆኑ ቢገባቸውም በተለመደው ስልት ለማለፍ ሞክረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ሚዲያው ላይ የቀረበውን ጥያቄ አፈናው አስፈላጊ ከሆነ እስከ ወዲያ ኛው እንጠረቅመዋለን አይነት ምላሽ ሰጥተዋል።ይህ እንግዲህ ስልጣን በያዙ ማግስት የማህበራዊ ሚዲያውን ልንዘጋው አይገባም፣የዓለም ሕዝብ ቁጥር እና የፌስ ቡክ ተጠቃሚን እያነጻጸሩ የሰጡትን ገለጻ ለሰማ ምነው እንዲህ በአጭር ጊዜ ሹዋሹዋ ሰሩን ሲሉ የነበሩ ተክደናል ያሉትን ወገኖች ሀሳብ መግለጫቸው ከሰሞኑ የተግባር እርምጃ በተጨማሪ የበለጠ አረጋግጦዋል።
ጥያቄው በዚህ መንገድ ኢህአዴግም ሆኑ እሳቸው አፈና በማጠናከር ብዙ ርቀት ይሄዳሉ!? አስተያየት ስጡበት።
Filed in: Amharic