>

መንግስት ባመነው ብቻ 53ቱ ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል !! (ሀብታሙ አያሌው)

መንግስት ባመነው ብቻ 53ቱ ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል !!
ሀብታሙ አያሌው
በኦዴፓ/ኦነግ/  የጠቅላይነት የፖለቲካ ስሌት በሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች፤ እራሱን ኤጄቶ እያለ በሚጠራ ስብስብ በኩል በተፈጸመ አሰቃቂ የጅምላ ጥቃት “ሃኪም ቤት ሳይደርሱ፣ በየአካባቢው የተቀበሩትን ሳይጨምር፣  53 ሰዎች ” መገደላቸው ፤ የሲዳማ ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዳኛው ደምሴ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል ።
ክልል የመሆን ጥያቄን በጉልበት ወይም በህግ  አስከብሩ በማለት ፤ በአደባባይ ወጣቱን ሰብስቦ መመሪያ የሰጠው የኦዴፓ/ኦነግ ኢ-መደበኛ ቃል አቀባይ  አቶ ጃዋር መሐመድ እንዲሁም የጃዋርን ተልዕኮ በመቀበል እራሱን ኤጄቶ እያለ የሚጠራውን ቡድን ፤ለ53ቱ በግፍ ሕይወታቸውን ላጡ ንጹሃን ዜጎች፤ በህግ ቀዳሚ ተጠያቂ መሆን እስካልቻሉ ስለ ፍትህ ማውራት ቀልድ እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል።
የዶ/ር አብይ አስተዳደር የአብን መታወቂያና የአባልነት ክፍያ ደረሰኝ የያዙ ንፁሃን ወጣቶችን፣  ጋዜጠኞችን  አክቲቪስቶችን  እያሰደደ በማሰርና በማሰቃየት በማንነት ተኮር የጥቃት ዘመቻው  እየፈፀመ ያለው ግፍ የስርዓቱን አደገኛ አካሄድ ለመረዳት በቂ ማሳያ ነው።
ፍትህ! ፍትህ!….  ፍትህ!!!
Filed in: Amharic