>
5:13 pm - Friday April 19, 9585

አፓርታይድ እስከመቼ? (አብርሃ በላይ)

አፓርታይድ እስከመቼ?
አብርሃ በላይ
*  “ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያሉ በባዶ ሜዳ መጮህ የሚሰጠው ትርጉም ቢኖር – “የማይነገረው ፕሮጀክታችን እስክንተገብር ድረስ፣ እባካችሁ ትንሽ ታገሱን!” ከማለት ውጪ ሌላ ሊሆን አይችልም!!!
የኢትዮጵያ አፓርታይድ ከደቡብ አፍሪቃው አፓርታይድ እጅግ አስፈሪና አገር አፍራሽ፣ ህዝብ አጫራሽ የፖለቲካ ካንሰር ነው። የደቡብ አፍሪቃው አፓርታይድ ከ95% በላይ የሆነውን ጥቁር ህዝብ ህብረቱን አጠናክሮ አንድ ላይ እንዲቆምና አናሳው የነጮች (3%) አገዛዝ እንዲወገድ ረድቷል።
የኢትዮጵያው ግን በነጭና በጥቁር ህዝብ የምንለው አይደለም። የእርስ በርስ እልቂትን የሚጋብዝ በታኝ አፓርታይድ ነው። እየሆነ ያለውም ይኸው ነው።
አሁን ጊዜው የዶ/ር አብይ መንግስት ነው። ይህ መንግስት ዘወትር እንደሚምለው ለኢትዮጵያ ትንሳኤ የቆመ ከሆነ፦
1) አደገኛውን አፓርታይድ በአዋጅ ያስወግድ!
 2) ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ ኃይሎችን ማዋከብ፤ በተለይ የባልደራስ እና የአብን አመራርና አባላትን ማሰር፣ ማሳደድ ያቁም፤ የታሰሩትም ይፍታ!
 3) የአፓርታይድ ተጠቃሚዎች እና ጠበቆች የሆኑት የኦዴፓ እና የትህነግ ድርጅት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በእነ መምህር ታዬ ቦጋለ አይነት ታላላቅ የታሪክ ምሁራንና የሀገር አንድነት ጠበቆች በቂ ትምህርት እንዲያገኙ በየደረጃው የሚሰጡ ብሄራዊ ሴሚናሮችን ያዘጋጅ። የኢትዮጵያ ህዝብም ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ የመንግስት ደጀን ሆኖ እንደሚቆም አያጠራጥርም።
ይህን ሳያደርጉ፣ “ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያሉ በባዶ ሜዳ መጮህ የሚሰጠው ትርጉም ቢኖር – “የማይነገረው ፕሮጀክታችን እስክንተገብር ድረስ፣ እባካችሁ ትንሽ ታገሱን!” ከማለት ውጪ ሌላ ሊሆን አይችልም።
Filed in: Amharic