>

ሰው በላው የሊቢያ መንገድ (አሸናፊ በሪሁን)

ሰው በላው የሊቢያ መንገድ

(አሸናፊ በሪሁን ከ seefar )

 

ከአፍሪካ ቀንድ ወደ አውሮፓ የሚደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ከስደተኞች መነሻ አገራት ጀምሮ እስከ አውሮፓ ያለው ሰንሰለት ጠመዝማዛና ውስብስብ ነው፡፡ ወደ አውሮጳ የሚደረገው ይህ ጉዞ አስፈሪ እና አደጋ የተሞላበትን ቢሆንም ዛሬም ብዙዎች ነብሳቸውን አስይዘው ይሄዱበታል።

አህመድ ሳልህ (ስሙ የተቀየረ ) ከ2 ዓመት በፊት ነበር አውሮፓ ለመግባት ተስፋ ሰንቆ ከኢትዮጵያ የወጣው። ከዛ ሞትን ከሚያስመኝው አሰቃቂ የጉዞ ገጠመኞ በኋላ አሁን ወደ ሀገሯ ተመልሶል፡፡ አህመድ በተሰበረ ስሜት ታሪኩን ሲያወራ የፊቱ ገፅታ ይቀየራል፡ እንባ ይቀድመዋል፡፡ አሕመድ የመጀመሪያ ጉዞውን ከአዲስ አባባ በመነሳት ወደ ሱዳን ነው ነበር ያደረገው። በሱዳን ለጥቂት ጊዜ ከቆየው በኋላ ከሌሎች ስደተኞች ጋር በመሆን ለሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በነብስ ወከፍ 600 ዶላር በመክፈል ጉዞውን ወደ ሊቢያ ጀመረ። የሊቢያ ጉዞው የተጀመረ በጭነት መኪና ነበር። የአካባቢው ሙቀት፣ የውሃ ጥማት እና ረሃቡ እንዲሁም ዕርስ በርሳቸውን ተደራርበን መጫናቸውን የሚያስታውሰው አህመድ ጉዞው አድካሚ ብቻ ሳይሆን ተስፋ አስቆራጭ ነበር ይላል። ይህ አስከፊ የበረሃ ላይ ጉዞ ለሳምንታት ቀጠለ። በረጅም ቀናት ጉዞም በኋላ ግብፅን እና ሊቢያን የሚያዋስን ቦታ ላይ ደረሡ። ይህ ቦታ ህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪች ስደተኞችን የሚቀባበሉበት አንዱ ስፍራ ነው። ቦታው ላይ የደረሡት ግን እጅግ ተጎሳቁለው እና ተዳክመው ነበር።

ብዙም ሳይቆይ ያላሰቡት ነገር ገጠማቸው። መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች በድንገት መጥተው የነበራቸውን ገንዘብ እና ያደረጎቸውን ጌጣ ጌጦችን እና ዕቃዎቻቸውን ሙጥጥ አድርገው ዘርፈዋቸው ሄዱ። ወደ ስፍራው የወሰዱዋቸው ሰዎችም ለሊቢያ ደላሎች አሳልፈው ሰጥዋቸው ፡፡ አዘዋዋሪዎች አረብኛ እና ሌሎች የማላውቃቸውን ቋንቋዎች ስለሚናገሩ ከማን ጋራ ምን እንደሞዶሉቱባቸው እነ አህመድ አያውቁም ፡፡ አሁንም አሰልቺ እና ተስፋ አስቆራጭ የሆነ የሁለት ቀን ጉዞ ካደረጉ በኋላ ሊቢያ አቅራቢያ ወደሚገኝ አንድ ካምፕ ውስጥ አስገድደው አንዲገቡ አደረጉዋቸው ። ከቀናት በኋላ አዘዋዋሪዎች አንድ መኪና አመጡና “4000 ዶላር መክፈል የምትችሉ እዚህ መኪና ውስጥ ግቡ የማትችሉ ግን እዚሁ ቁጭ በሉ” ሲሉ አዘዙዋቸው ። ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የተላከላቸው የተወሰኑ ሰዎች የተጠየቁትን ከፍለው መሄድ ቻሉ።እህመድ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ግን በጊዜው ምንም ገንዘብ ስላልነበራቸው ለተጨማሪ ቀናት እዛ በርሃ ላይ ለመቆየት ተገደዱ። ለአንድ ወር ያህል የተለያዩ ስቃዮችን አንደደረሱበት የሚናገርው አህመድ ከመሃከላችን ጥቂቶቻችን ቤተሰቦቻችን በስልክ አግኝተን ብር እንዲልኩልን አድርገን እና ከፍለን ከዛ ቦታ መውጣት ቻልን። ቦታውን ለቀን ብዙም ሳንጓዝ ሌሎች ሰዎች መጥተው አፍነውን ወደ ሌላ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ወሰዱን። አሁንም ገንዘብ አምጡ እና እንውሳዳችው ተባልን ሆኖም ግን በካምፑ ውስጥ መቆየት እጅግ አስጨናቂ ስለነበር የጠየቁትት ገንዘብ እንዳለኝ በማስመሰል ተስማምቼ ተሳፈርኩ።

እኔ ብቻ ሳልሆን ሌሎች በርካታ ስደተኞች ገንዘብ ያላቸው በማስመሰል መኪናው ላይ ወጡ። ወዴት እንደሚወስዱን እንኳን እርግጠኛ ሳንሆን ከሶስት ቀናት ጉዞ በኋላ ከአንድ ስፍራ ደረስን። እዚህ ስፍራ ስንደርስ የነበረኝ አማራጭ ገነዘብ መክፈል አለያም ደግሞ ማምለጥ ነው፡፡ ገንዘብ ፈፅሞ ስላልነበረኝ ህይወቴን ለማትረፍ ያለኝ አማራጭ ማምለጥ ነበር፡፡ ያን ቀን ማታ በጣም ተዳክመን ስለነበር ማምሻውን ከሁለት ኢትዮጵያውያን ጎደኞቸ ጋራ ተማክረን በለሊት አመለጥን ፡፡ ከቀናት ጉዞ በኋላም አህመድ እና ጎደኞቹ ተሳክቶላቸው ሱዳን ለመድረስ በቁ ፡፡ ሱዳን ሲደርሱም ዕዛ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጋራ ተጠግተው ከቆዩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ በቅተዋል ፡፡ አህመድ እንደ ዕድል ሆኖ በህይወት ተርፎል። የእርሱ ዓይነት ህልም የነበራቸው ሌሎች በርካታ ስደተኞች ግን እንደወጡ ቀርተዋል። በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመግባት በሚደረገው ጉዞ በሱዳንና በሊቢያ መካከል በሕገወጥ ሚሊሻዎች፣ ሽፍቶችና ዘራፊዎች በመንገድ ላይ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና በውኃ ጥም ሕይወታቸው የሚያልፈው ስደተኞች ብዙ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያንም ከአገር ውስጥ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ ድንበሮች የሚሻገር ትስስር ያለው የዚሁ ወንጀል ሰለባ በመሆናቸው ለከፋ ስቃይ፣ ፣ ለሞት፣ ለበረሃ ሲሳይ፣ ለአውሬና ለባህር ቀለብ መሆናቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ወደ አውሮፓ የሚወስደው መንገድ በተለይ ለሕፃናትና ሴቶች በጣም አደገኛ ነው፡፡ ብዙዎች በጉዞው ላይ ለድብደባ፣ ለተገድዶ ለመደፈር፣ ለባርነትና ሌሎች ጥቃቶች ይዳረጋሉ፡፡ ብዙዎች ሴት ስደተኞችም የሊቢያውን ምድረ በዳ ከመሻገራቸው በፊት በሱዳን የፅንስ መከላከያ መርፌ ይወጋሉ፤ ምክንያቱም በዚህ ጉዞ የመደፈር አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጋረጠባቸው ስለሚያውቁ ነው፡፡በሊቢያ ጥናት ከተደረገላቸው ግማሽ የሚሆኑት ህገ ወጥ ሴቶችና ህፃናት ስደተኞች በጉዛአቸው ወሲባዊ ጥቃትና ስቃይ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ስደተኞች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ አውሪፓ ለመድረስ 5400 የአሜሪካን ዶላር ያህል ያወጣሉ። ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለመድረስ 1600 የአሜሪካን ዶላር ከሱዳን ወደ ሊቢያ ለመደረስ 1600 የአሜሪካን ዶላር በስተመጨረሻም ሜዲትሪያንያን ለመደረስ እሰከ 2200 የአሜሪካን ዶላር ይከፍላሉ፡፡ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አንድን ስደተኛ ወደ አውሮፓ ድንበሮች ለማድረስ በርካታ ገንዘብ ያስከፍላሉ፡፡ አውሮፓ ለመድረስ በጣም ቀላል ነው እያሉ ስደተኞችን ማታለል የተለመደ ሥራቸው ነው፡፡ ከዚሁም ሌላ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ከስደተኛው ጋር መጀመርያ ላይ ያደረጉትን ስምምነት ብዙውን ጊዜ ያፈርሳሉ ፡፡ ሰደተኞቸም ድንገት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ፡፡ ስደተኞችን እንደመያዣነት በመጠቀም ወዳጅ ዘመዶቻቸው የማስለቀቅያ ብር እንዲልኩላቸው ያስገድዳሉ፡፡ አንዳንድ ስደተኞች ደግሞ ደላሎች በየጊዜው የሚቆልሉትን ዕዳ ለመከፈል እና ለሚቀጥለው ጉዟቸው ገንዘብ ለማጠራቀም በማሰብ ለባርነት ይዳረጋሉ፡፡ስደተኞች ለህገወጥ አዘዋዋሪዎቻቸው የሚከፈል ገንዘብ ካጡ የሰውነታቸውን አካላት በልተው ለሚወስዱ የተደራጁ የወንጀለኞች ቡድኖች አሳልፈው ይሸጡዋቸዋል ፡፡

በዓለም ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 130 ያህል አገሮች ለድንበር ተሻጋሪ ከፍተኛ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጋላጭ መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለጥቂቶች በአጭር መበልፀጊያ፣ ለብዙዎች ግን ከስቃይም በላይ ሕይወት መገበሪያ ሆኗል፡፡ ይህ ድርጊት የዕፅ ዝውውርና ንግድን በማለፍ፣ የጦር መሣሪያ ንግድን በመከተል በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ከፍተኛ የወንጀል ሀብት ማካበቻ ዘርፍ ሆኗል፡፡ በተደራጁ ወንበዴ ደላሎች አማካይነት የሚፈጸም አደገኛ ወንጀል ነው፡፡ ከሱዳን ሊቢያ አውሮፓ ለመግባት በሚደረገው ይህን የሰው ህይወት የሚበላው ጉዞ ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ግን ዛሬም ይህን እየሰሙ ብዞዎች ይጎዙበታል ፡፡ እኛም የዚህ አደገኛ ጉዞ ሰለባ ላለመሆን ህጋዊ መንገድን ብንከተል ይሻላል እላለው

Filed in: Amharic