>

የአክራሪዎችና የጽንፈኞች ቀላሏ ታርጌት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን!!! (ዶችቬሌ)

የአክራሪዎችና የጽንፈኞች ቀላሏ ታርጌት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን!!!
ዶችቬሌ
 
በሀገረ ሠላም ሦስት አብያተ ክርስትያናት ተቃጥለዋል፤
 * ዶያ ሚካኤል በእሳቱ በመጋየቱ ፅላቱ ወደሌላ ቦታ ተወስዶአል
* ለአብያተ ክርስትያናቱ እና ምዕመናን ድጋፍ የሚያደርግ ኮሚቴ ተቋቁሞአል» 
የሲዳማ ሃገረ ስብከት
በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በሀገረ ሠላም የሚገኙ ሦስት አብያተ-ክርስትያናት የቃጠሎ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሲዳማ፣ የጌዶ፣ አማሮ እና ቡርጂ ሃገረ ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ። ምክትል ስራ አስኪያጁ መጋቢ ሐይማኖት ቀሲስ ነፃነት አክሎግ ለዶይቼ ዌሌ ዛሬ እንደተናገሩት፤ በሲዳማ ሀገረ ሠላም አካባቢ የሚገኙት ዶያ ሚካኤል፣ ገሳባ ገብረክርስቶስ እና ጭሮኔ አማኑኤል የተባሉት ሦስት አብያተ ክርስትያናት ላይ ቃጠሎ ደርሷል።
.
በተለይ ዶያ ሚካኤል ቤተ-ክርስትያን በደረሰበት ቃጠሎዉ መዉደሙን እና ፅላቱ ወደሌላ ቦታ እንዲሄድ መደረጉን መጋቢ ሐይማኖት ነፃነት ተናግረዋል። በተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ለመከላከል ምዕመናን ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸዉን የገለፁት ምክትል ስራ አስኪያጁ፤ በርካታ ዲያቆናት አካባቢዉን ሸሽተዉ በኦሮምሚያ ክልል ሮቤ ወረዳ በሚገኝ ቤተ-ክርስትያን መጠለላቸዉን አረጋግጠዋል።
.
በቃጠሎ የወደመዉ የዶያ ሚካኤል ቤተ-ክርስትያን አስተዳዳሪ፤ ሁኔታዉን ለማስረዳት አዋሳ ወደሚገኘዉ ሃገረስብከት መሄዳቸዉም መረጃዉ ደርሶናል ብለዋል። “ቀደም ሲል የዶያ ሚካኤል አስተዳዳሪ መታገታቸዉ መረጃ ደርሶ ነበር ግን ዛሬ መለቀቃቸዉን እንዲሁ ሰምተናል” ሲሉ መጋቢ ሐይማኖት ነፃነት ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
.
በሲዳማ በሌሎች የገጠር ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በምዕመናን ጥረት ከአደጋ እና ከቃጠሎ የተረፉ መኖራቸዉንም አክለዋል። “አብያተ ክርስትያናቱ እንዳይቃጠሉ ሲከላከሉ ከነበሩ ምዕመናን መካከልም የሞቱ እንዳሉ ሰምተናል” ያሉት የሀገረ ስብከቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ “ይሁንና ይህን መረጃ በእርግጠኝነት ለማጣራት ቦታዉ ላይ መሄድ ይጠበቅብናል” ብለዋል።
.
“ወደ አካባቢዉ ለመሄድ የአካባቢዉ ፀጥታ አልፈቀደልንም ነበር። በአሁኑ ሰዓት ግን የመረጋጋቱ ሁኔታ በመሻሻሉ፤ በደቡብ ክልል የሰባት ቤተ-እምነቶች ጥምረት፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ነገ ስፍራዉ ላይ ተገኝቶ ሁኔታዉ ለማጣራት ቀጠሮ መያዙን መረጃ ደርሶኛል” ሲሉ ከቃጠሎው በኋላ እየተደረገ ያለውን ጥረት አስረድተዋል። ዛሬ በይርጋለም እንደሚገኙ የነገሩን የሃይማኖት አባት ሲዳማ ዛሬ ከሌሎቹ ቀናቶች ሁሉ በተሻሻለ የፀጥታ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ከተለያዩ አካባቢዎች በደረሰኝ የስልክ ጥሪ ማረጋገጥ ችያለሁ ብለዋል።
.
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእነማን? ለምን አላማ የጥቃት ሰለባ ሆነች!!!
በኢትዮ 360 የቀረበ ውይይት
Filed in: Amharic