>

ለህዝብ የቆመ ፓርላማ ቢኖረን የጃዋርን አሸባሪነት አውጆ ሃገር ቤት እንዳይገባ መከልከል በቻለ!!!  (መስከረም አበራ)

ለህዝብ የቆመ ፓርላማ ቢኖረን የጃዋርን አሸባሪነት አውጆ ሃገር ቤት እንዳይገባ መከልከል በቻለ!!! 
መስከረም አበራ
ጠ/ሚ አብይ በአሳዛኝ ሁኔታ ጃwar መሃመድ ኢትዮጵያን ለማውደም ከሚያደርገው ሩጫ ሊያስቆሙ አለመቻሉ ያፈጠጠ ሃቅ ነው። አብይ ይህን ለማድረግ ፍላጎቱ ቢኖረው ኖሮ ህጋዊ ስልጣኑም አቅሙም በእጁ ነበር፤ሆኖም አብይ ጃዋር የዘር ግጭትን እየለኮሰ እንዲያቀጣጥል ፈቅዶ ትቶታል።
በተለይ የሲዳማ ህዝብ በጉልበትም ቢሆን ክልልነቱን እንዲያውጅ ጥሪ ያቀረበበት ቪዲዮ ለዚህ ተግባሩ ተጠቃሽ ነው። እናም ይህን ጥሪ ተከትሎ ኤጄቶ የተባለው ቡድን ለጃዋር ጥሪ በሰጠው እጅግ አመፀኛ ምላሽ አሁን ላይ ኢትዮጵያዊያን ውድ ህይወታቸውን እየከፈሉ ነው።
አብይ አህመድ ለእነዚህን ንፁሃን ኢትዮጵያዊያንየህይወት እና ንብረት ዋስትና መስጠት ስላልፈለገ ፓርላማው በአስቸኳይ ተሰብስስቦ ስልጣኑ የሚፈቅድለትን ሃይል ሁሉ ተጠቅሞ የእነዚህን ንፁሃን ዜጎች ህይወት እና ንብረት ለመታደግ የሚያስችል አንዳች ውሳኔ መስጠት አለበት።
ፓርላማው ሊወስን የሚችለው እና የሚገባው አንድ ነገር ቢኖር ጃዋር የመሃመድን አሸባሪነት አውጆ ሃገር ቤት እንዳይገባ መከልከል ብሎም በአለበት ምድር ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርብ መወሰን ነው።
 አብይ ጃዋር ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጭ ብሎ ኢትዮጵያ የምትፈርስበትን ስራ እንዳይሰራ የሚፈልግ ቢሆን ነገሩ የሚጠይቀው ቀላል ነገር  ለአሜሪካ ባለስልጣናት አንድ የስልክ ጥሪ አድርጎ ጃዋር በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ እያደረገ ካለው እኩይ ስራው እንዲቆጠብ እንዲያስጠነቅቁት መንገር ብቻ ነበር። አብይ ይህን ማድረግ ስለማይፈልግ ጃዋር በግልፅ በአደባባይ ኤጄቶ የተባለውን ቡድን ለዘር ፍጅት ያበቃውን የቪዲዮ ንግግር እስከማድረግ ደረሰ።ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተደረገው አሰቃቂ ድርጊት የዚሁ ቪዲዮ ውጤት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝቡን ደህንነት ማስጠበቅ ካልቻለ እና ፓርላማውም በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ሳያደርግ ዝም ብሎ የሚያይ ከሆነ እንዴት ብለን ነው በኢትዮጵያ ትርጉም ባለው መንገድ የሚንቀሳቀስ መንግስት አለ  ማለት የምንችለው?
Tedla G.Yohanes በፈረንጅ አፍ  እንደፃፈው እኔ እንደተረጎምኩት

https://youtu.be/05WT_kgE8qQ

Filed in: Amharic