>

በሲዳማ ዞን ሕገ መንግሥቱ  እየተተገበረ እንጂ እየተጣሰ አይደለም! (አቻምየለህ ታምሩ)

በሲዳማ ዞን ሕገ መንግሥቱ  እየተተገበረ እንጂ እየተጣሰ አይደለም!
አቻምየለህ ታምሩ
በሲዳማ ዞን ውስጥ በተለይም  በአዋሳ ከተማና በዙሪያው  ከሲዳማ ውጭ በሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ላይ  እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝ  ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ፣ የንብረት ማውደም፣ የካህናት ግድያና  የቤተ ክርስቲያን  ማቃጠል  ብዙ ሰው እንደሚያስበው «ሕገ መንግሥት» የሚባለው ነገር እየተጣሰ አይደለም፤ እንዴውም እየተተገበረ እንጂ።
ሕገ መንግሥት ተብዮው የተጻፈው  «ለዘመናት ነበረ» የተባለውን «የተዛባ ግንኙነት» ወይንም «የጨቋኝና የተጨቋኝ ግንኙነት» ለማጥፋት ነው። በሕገ መንግሥቱ መሰረት የሲዳማ ዞን  ባለቤት ሲዳማ ብቻ ነው። ከሲዳማ  ውጭ ያለው መጤና ሰፋሪ ነው ተብሏል። ነዋሪው አማራ ከሆነ ደግሞ ጨቋኝ እንደሆነ ተደርጎ ተረክ ተፈጥሯል።  ቤተ ክርስቲያኗ የጭቆና መሳሪያ ተደርጋ ትምህርት መሰጠት ከጀመረ ከአራት  አስርት አመታት በላይ ሆኖታል። ይህ በሆነበት ሁኔታ በግራ ፖለቲካ ፍልስፍና ጭቆናን ማጥፋት የሚቻለው ጨቋኝን በማጥፋትና ምልክቶቹን በማውደም ብቻ ነው።
በሕገ መንግሥቱ መሰረት የሲዳማ  ሉዓላዊነትና የሲዳማ ነገድ የራሱ መልክዓ ምድር የሚኖረው ከሲዳማ ውጭ ያለው ሕዝብ ከሲዳማ የአስተዳደር ዞን ሲፀዳ ነው። ከሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ጋር ተያየዞ ሲዳማ ባልሆኑ ሰዎች ላይ እየረፈጸመ ያለው ግፍም መነሻው  በሕገ መንግሥቱ መግቢያ መሰረት ሲዳማ ሉዓላዊና  የራሱ መልክዓ ምድር ያለው ሕዝብ የሚሆነው ከሲዳማ  ውጭ ያሉትን አጽድቶ ብቻውን ሲቀር ብቻ ነው።
ስለዚህ በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ  ሕገ አራዊት  መግቢያ ላይ  «ለዘመናት ነበረ» የተባለውን «የተዛባ ግንኙነት» ወይንም «የጨቋኝና የተጨቋኝ ግንኙነት»  የራስን እድል በራስ መወሰን እሳቤ ማጥፋት የሚቻለው ሲዳማ ዞን  በሚባለው እየሆነ እንዳለው ጨቋኙንና (የ)ሲዳማ ያልሆነውን በማጥፋት እንደ ቤተ ክርስቲያን አይነት የጭቆና መሳሪያ ናቸው የተባሉትን  ደግሞ በማውደም ብቻ  ነው። በሌላ አነጋገር በሲዳማ ዞን  የምንሰማው ሁሉ ሕገ መንግሥት ተብዮው እየተተገበረ እንጅ እየተጣሰ አይደለም። ሕገ መንግሥቱ በሲዳማ ዞን  ውስጥ ከሲዳማ  ውጭ የሚያውቀው ነገድ የለውም። ዜግነትህን የገፈፈህን ሕገ መንግሥት ተብዮ የፋሽስት ወያኔና የኦነግ ደንብ  ተጣሰ ካልህ የቅሚያና የግድያ ደንበየን  አለማወቅህን ብቻ ነው የሚያሳየው።
እንኳን የፋሽስት ወያኔ ዲቃላው ዐቢይ አሕመድ ይቅርና በፋሽስት ወያኔ ዙፋን መልዓክ እንኳ ቢሰየም አገዛዙ  የተዋቀረበት  ርዕዮተ ዓለም  እስካልተቀየረ ድረስ ምን ቅን ሰው ቢሆን  ከፋሽስት ወያኔ ዘመን የተለየ ነገር እንዲያመጣ ሕገ መንግሥት ተብዮው  አይፈቅድለትም ብለን ተናግረን ነበር። ዐቢይ አሕመድ ሊያደርግ ተሚችለው ብቸኛው ነገር የትግሬን በኦሮሞ የበላይነት በብርሀን ፍጥነት  መተካት እንጂ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እንደዜጋ የሚበጅ ነገር  እንዲያመጣ  ቢፈልግ እንኳ ርዕዮተ ዓለሙ አይፈቅድለትም።
አሁንም እንደግመዋለን! የኢትዮጵያ ችግር ጸረ ሰብ፣ ጸረ ሀገርና ሕገ ወጥ የሆነው  አገዛዙ የተዋቀረበት  ርዕዮተ ዓለምና የተመሰረተበት ሕገ መንግሥት የሚሉት የፋሽስት ወያኔና የናዚ ኦነግ የቅሚያና የግድያ  ነው። ማንም ገዢ ነኝ የሚል ከአፉ  ማር ቢዘንብ እንኳ ተፈጻሚ የሚደረገው  ይህ ጸረ ሰብ፣ ጸረ ሀገርና ሕገ ወጥ ርዕዮተ ዓለም ነው የወለደው ሕገ አራዊት ነው። ጸረ ሰብ፣ ጸረ ሀገርና ሕገ ወጥ የሆነው  የወያኔ ሕገ አራዊት እስካለ ድረስ የሕግ የበላይነት፣ ንብረት የማፍራት፣ ዜጋ የመሆን፣ የሕይወት ጥበቃ፣ ወዘተ የሚባሉ መብቶች የሉህም።
ባጭሩ የጭካኔ አስተሳሰብ የወለደው  የፋሽስት ወያኔና የናዚ ኦነግ ርዕዮተ አለም የወለደው  ሕገ አራዊት ዋጋ እንዲያጣ ሆኖ እስካልተወገደ ድረስ ክልልህ  ወይም ዞንህ አይደለም በተባለው አማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ስልጤ፣ ወዘተ ላይ ዛሬ  በሲዳማ ዞን የደረሰ ያለው የፋሽስት ወያኔና የናዚ ኦነግ  ሕገ አራዊት  የወለደው ግፍና ጭካኔ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በየተራ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ መፈጸሙ የማይቀር ነው። ከአዋሳ ቀጥሎ ባለተራው  አዲስ አበባ እንደሚሆን በኔ በኩል አልጠራጠርም።
Filed in: Amharic