>
5:13 pm - Thursday April 19, 8762

ትናንት "ኢትዮጵያዊ አይደለንም!"  ፤ ዛሬ ሰማይ ምድሩ ሁሉ የእኛ ካልሆነ...!!! (ሚካኤል ዮሀንስ)

ትናንት “ኢትዮጵያዊ አይደለንም!”  ፤ ዛሬ ሰማይ ምድሩ ሁሉ የእኛ ካልሆነ…!!!
ሚካኤል ዮሀንስ
በአሜሪካ በሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ተደርጎ በዶክተር አብይ የተሾመው ዶክተር ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኜ በጃዋር ሚዲያ በሆነው OMN ላይ ቀርቦ የሚከተለውን ብሏል።
*  አዲስ አበባ ውስጥ በየዓመቱ ከሚደረገው ግንባታ ውስጥ የኦሮሞ ድርሻ ቢያንስ ቢያንስ 40-50 በመቶ ወደ ኦሮሞ ሊሄድ የሚችልበትን ሕግና ፖሊሲ አውጥቶ ሥራ ላይ ማዋል ይገባል።
* በውጭ ንግድ እና በሃገር ውስጥ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የንግድ ፈቃድ ሲሰጥ ኦሮሞ በብዛት እንዲያገኝ የምናደርግበትን ፖሊሲ ማውጣት አለብን።
*  የአዲስ_አበባ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ወደ ኦሮሚያ መመለስ አለብን።
* በኦሮምኛ የሚሰሩ ቢዝነሶች የሉም ፣
* የኦሮሞ ቤተክርስቲያን የለም ፣
* የኦሮሞ መስጊድ የለም ብሏል።
ትናንት ኢትዮጵያዊ አይደለንም እያሉ በየሄዱበት ሀገር ኢትዮጵያዊነትን እያጣጣሉና ብሄራቸውን እንደ ዜግነት ሲናገሩ የነበሩ፣ በተለይም ኢትዮጵያዊነት አላስፈላጊና በግዴታ የተሰጣቸው እዳ አድርገው በአለማቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር ሲናገሩ የነበሩ ዛሬ በምን ሁኔታ ነው ሀገራዊ ሀላፊነት የሚሰጣቸው?
በዚህ አይነት እጅግ የጠበበ አስተሳሰብ ውስጥ ሆነው ሌላውን ኢትዮጵያዊ በቅንነት እና በታማኝነት ያገለግላሉ ተብሎስ ይታሰባል?
መንቻካና ኋላቀር የጎጥ ስሜት ውስጥ ሆነው የሚሰጣቸውን ሀገራዊ ሀላፊነት ለጠባጫሪነት እየተጠቀሙበት ነው።
ለመሆኑ በአቶ ገዱ የሚመራው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለዚህ ምላሹ ምን ይሆን?
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሕብረት
Filed in: Amharic