>
5:13 pm - Thursday April 19, 0159

ቄሮ ምን ማለት ነው? (ቅዱስ ማህሉ)

ቄሮ ምን ማለት ነው?
ቅዱስ ማህሉ
በነገራችን ላይ ቄሮ የሚለውን ቃል በፌስቡኬ ላይ መጠቀም/መጻፍ ከጀመርኩ ከትናንት ወዲያ ጀምሮ ዛሬ ገና ሶስተኛ ቀኔ ነው። እስከዛሬ የኦሮሞ ወጣቶች ሲታገሉም ሆነ ሲገደሉ ቄሮ ብየ ሳይሆን ለመብታቸው የሚታገሉ  ወጣት ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን እያልኩ ነው ስጽፍ የኖርኩት። በርግጥ ትክክልም ነበርኩ።
ምክንያቱም ወጣት የኦሮሞ ታጋዮች ሰው ዘቅዝቀው የሚሰቅሉ አይደሉም። ቄሮ ግን ሰው ዘቅዝቆ የሚሰቅል ነው።ይህን የሚያደርግ ደግሞ የዲሞክራሲ ታጋይ ሳይሆን የእንስሳ ባህሪ የተላበሰ ስብዕናው የጨነገፈ ሰው መሰል  አውሬ ነው። ቄሮ ማለት እንደሚባለው ያላገባ ኦሮሞ ማለትም አይደለም። የኦሮሞ ወጣትም ማለት አይደለም። ይህን የሚሉት ቄሮን እንደመንጋ የሚነዱት ያለቤተሰብ ሜዳ ላይ ያደጉት እረኞቹ ናቸው።
በስነምግባር እና ሰብዓዊ እሴት ሳይገሩ የቤተሰብ፣ የማህበረሰብ እና የሃገር መስተጋብር ሳይረዱ ያደጉ ገናና ደናቁርቶች ናቸው። ቄሮ አዲስ ቃል አይደለም። የአጼ ገብረመስቀል ጦር ከቄሮ ጋር ይዋጋ ነበር። ታሪክ ነው። የጋሞው ባህታዊ እና የታሪክ ጠሃፊ የሆኑት አባ ባህሪ ይህን ጥፈዋል።
የኦሮሞን ታሪክ በነቀሱበት ጥሁፋቸው ቄሮ በየደረሰበት የሰው ንብረት ሲዘርፍ፣ሲያቃጥል እና ሰው ሲያርድ እንደነበር የጣፉት ገና ጥንት ነበር። በሚኒሶታ በሚገኘው የቅዱስ ዮሃንስ ዩኒቨርስቲ የሚሰሩት ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ የአባ ባህሪይን ጥሁፍ ከግዕዝ ወደ አማርኛ እና እንግሊዝኛ መልሰው “የኦሮሞ እና የታሪክ ሰነዶች” በሚል 1997ዓ/ም አሳትመውት ነበር።
 ይህ መጥሃፍ አሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያዊያን መጽሃፍ መሸጫ ወይም ሸቀጣሸቀጥ መደብሮች ውስጥ የሚጠፋ አይመስለኝም።  ያኔ መጽሃፉን ኦህዴድ/ኦዴፓ ከአዲስ አበባ ገበያዎች ላይ እየሰበሰበ ያቃጥል እንደነበር አውቃለሁ። በመጥሃፉ ላይ አባ ባህሪ የቄሮን ትርጉም ጥፈዋል።
 “ቄሮ ማለት መዋጋት የሚችል፣ መግደለ የሚችል፣ማረድ የሚችል፣መስለብ የሚችል፣ጦር ሜዳ መዋጋት የሚችል፣ማቃጠል እና ማውደም የሚችል በማንኛውም እድሜ ላይ የሚገኝ ያላገባ ኦሮሞ ማለት ነው” ወጣት ማለት አይደለም።
 ከላይ ያሉትን ነገሮች መፈጸም የሚችል ኦሮሞ እድሜው 20 ይሆን 50 ቄሮ ነው። ያን ማድረግ የማይችል ኦሮሞ እድሜው 18 ይሁን 40 ቄሮ አይደለም። ቄሮ በአጭሩ የጥፋት፣ የውድመት፣የጦርነት፣ የእልቂት እና የሞት ነጋሪት የሚጎስም እና ያን ለማድረግም ዝግጁ የሆነ ያላገባ ኦሮሞ ማለት ነው። ቄሮ በአብይ አህመድ መንግስት እና በአክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች የሚደገፍ ቡድን ነው።ካህናትን በየስፍራው የሚያርደው እና ቤተክርስቲያናትን የሚያቃጥለው ይህ ቡድን ነው።
ወገኖቻችንን አቃጥሎ የሚሰቅለው እና የሚያፈናቅለው ይህ ቡድን ነው። በመንግስት ድጋፍ የጌዲኦን ህዝብ በርሃብ ለመጨረስ  የሚሰራው እና የሚያርደው ይህ ቡድን ነው። እባክዎ ወደ ኢትዮጵያ ዶላር ባለመላክ ይህ የጥፋት ሃይል በንጹሃን ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈጽመውን የግድያ ዘመቻ ተጨማሪ አቅም ባለመፍጠር ይተባበሩ። ዛሬውኑ ዶላር ባለመላክ ይህን ቡድን እና የሚደግፈውን መንግስት በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መደገፍ ያቁሙ!!!
Filed in: Amharic