>
5:13 pm - Friday April 19, 0565

"የፌደራል አከላለላችንንም ከዘር ሊላቀቅ ይገባል !! " (የሶ.ክ.መግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፋ ዑመር)

“የፌደራል አከላለላችንንም ከዘር ሊላቀቅ ይገባል !! “
የሶ.ክ.መግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፋ ዑመር
በሃብታሙ አያሌው
 
ወደ ባህርዳር አቅንተው ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የሶማሌ ክልላዊ መግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፋ ዑመር የሃሳባቸውን ጥራትና ከፍታ  የሚያሳይ  ሊጎበኙት የሄዱትንም  ህዝብ የሚመጥን ምርጥ ንንግር አድርገዋል !!
ሰውዬው ከጀርባ ያነገቡት የተሰወረ ጥላቻ እንደሌላቸው እስከ ዛሬ ከተናገሩት በተግባርም ከሰሩት መረዳት ይቻላል።  አንዳንዶች ለፖለቲካ ትርፍ አስልተው እንደሚያደርጉት ጉዞ ሳይሆን በክብር ተጋብዘው በሄዱበት ፕሮግራም የበለጠ የሚያስከብራቸውን ተናግረዋል !!
ፕሬዘዳንት ሙስጠፋ… “በእኔ እምነት…….!  ብለው ጀመሩ እምነት እውነታቸውን ሲያስረዱ …”በእኔ እምነት ሁሉም ዜጋ አገራዊ ዜግነቱን ተቀብሎ፣ ኢትዮጵያዊነቱን Primary identity “ተቀዳሚ ማንነት” ተቀብሎ፣ እንደ ሃገር የተገነባ Nation ሁኖ የምንነጋገርው በዘር ሳይሆን ከፍ ባለ በኢትዮጵያዊነት ደረጃ ቢሆን እና ሰዎች Association “ስብስብ” የሚፈጥሩት በዘር ሳይሆን በአመለካከት እንዲሆን መሪዎች በዘር ሳይሆን በችሎታ፣ ቢሮክራሲያችን Merit Based የአስተዳደር ዘይቤ ብንከተል የፌደራል አከላለላችንንም ከዘር ይልቅ:-
#ምሥራቅኢትዮጵያ፣ 
#ሰሜንኢትዮጵያ፣ 
#ምዕራብኢትዮጵያ፣ 
#ደቡብኢትዮጵያእና 
#ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ተተክቶ፣
#ድሬዳዋ ላይ
#አዲስአበባና ኢትዮጵያ ውስጥ ከንቲባ በዘር ሳይሆን በችሎታው አወዳድረን ከንቲባ መሆን እንዲችሉ ተደርጎ መስተካከል አለበት”
ይሄ የፕሬዘዳንት ሙስጠፋ ወርቅ ሃሳባብ  በቅርቡ “አዲስ አበባ በህግም በታሪክም የኦሮሞ ናት” የሚል የቅዥት ሃሳቡን ሲሰነዝር ለነበረው ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ለአቶ ሽመልስ እና ለድርጅታቸው ለኦዴፓ እንዲሁም ለህወሓት ካምፕ ቢደርሳቸው ጥሩ ነው።   የአማራ ክልል ህዝብም በየአቅጣጫው ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመሻገር የሚያስችለው አንድነት ፈጥሮና ተደራጅቶ ዛሬ ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ያነሱትን ያያቶቹን ሃሳብ እውን ለማድረግ የማይናወጥ አቋም ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥበት ጊዜ ይመስለኛል።
ብአዴን /አዴፓ/ ሃሞተ ኮስታራ ሆኖ የክልሉን ህዝብ ከማንኛውም አይነት የህልውና ስጋት የሚያወጣ ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መውጣት ካልቻለ ሃግ ባይ አጥቶ የሚጋልበው የኦዴፓ “የኬኛ ፖለቲካ”  ሁሉን የመጠቅለል ፖለቲካዊ ስግብግብነት  አገር ሊያሳጣ እንደሚችል መገመቱ ከባድ አይደለም።
በእጅ አዙር የኩሽ ምድር የሚል የፖለቲካ ካርታ ስታንከላውስ ለከረመችው ኦዴፓ/ኦነግ  የፕሬዝደንት ሙስጠፌ የሃሳብ ከፍታ እና ወደ ባህርዳር ማቅናት ትልቅ ትርጉም አለው።
Filed in: Amharic