>

የአዋሳ ጉዳይ የሚመለከተው የአዋሳ ከተማ ነዋሪው ብቻ ነው !!! (ግርማ ካሳ)

የአዋሳ ጉዳይ የሚመለከተው የአዋሳ ከተማ ነዋሪው ብቻ ነው !!!
ግርማ ካሳ
ኢጄቶ በአሁኑ ወቅት  ከሲዳማ ፖሊሶች ጋር በማበር የአዋሳን ከተማ እያሸበረ ነው። አዋሳን በተመለከተ ብዙዎች የማያወቁት ሃቆች አሉ።
1. አዋሳ ወይንም ሃዋሳ ከተማ ከጥቂት አመታት በፊት ባዶ ነበረች። በዚያ አካባቢ የሚኖሩ ኦሮሞዎችና ሲዳማዎች ከብቶች ያሰማሩባት የነበረች ። የቀድሞ የሲዳሞ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ የነበረችውም የይርጋለም ከተማ ነበረች። (ያኔ አዋሳ/ሃዋሳ አልነበረችምና)።
2. አዋሳ የተቆረቆረችው፣ አዎን ከባዶነት ወደ ከተማነት፣ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1960 በራስ መንገሻ ስዩም ነው። በ1961 ወደ 404 ጡረታ የወጡ ወታደሮች ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሁን አዋሳ በሚባለው ቦታ መሬት ተሰጥቷቸው በዚያ መኖር ጀመሩ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከተማ መሆን ጀመረች። ከ1960 እስከ 1968 በሲዳሞ አውራጃ የያቤላ ወረዳ ዋና ከተማ ሆና አገለገለች። በ1968 የሲዳሞ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ከይርጋለም ወደ አዋሳ ዞረ።
3. በደርግ ጊዜ የሲዳሞ ክፍለ ሃገር የሚለው ወደ ሲዳማ ክፍለ ሃገርነት ስሙ ተቀየረ። አዋሳም ዋና ከተማ መሆኗ ቀጠለ።
4. በ2002 ዓ.ም አዋሳ ከተማ ሕብረ ብሄራዊ በመሆኗ እንደ ድሬዳዋ ራሷን የቻለች የቻርተር ከተማ ለማድረግ ታስበ። ከዚያም የተነሳ በተነሳው ተቃዉሞ ከ70 በላይ የሲዳማ ወጣቶች ተገደሉ። የሎቄ እልቂት ተብሎ የሚታወቀው።
5፣ በ2007 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ አዋሳ ከተማ በዙሪያዋ ያሉ ቀበሌዎች ጨምሮ ወደ 358808 ነዋሪዎች ነበሯት። ከነዚህም ወደ 61% በመቶ የሚሆኑ ዋና ከተማ ላይ የሚኖሩ ናቸው። በአጠቃላይ ከዋና ከተማ ወጣ ያሉ ቀበሌዎችን ጨምሮ በአዋሳ ከሚኖረው ህዝብ 65% ሲዳማ አልነበረም። 66% የአፍ መፍቻው ቋንቋ ሲዳምኛ አልነበረም።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ ላለፉት 12 አመታት አዋሳ በጣም በማደጓ ይሄ ቁጥር ቁጥሩ የበለጣ የሚያድግ ነው። ምን አልባት ወደ 75%።
6. ኢጂቶዎች የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ በማንሳት በአዋሳ በሌሎች ማህበረሰባት ላይ የተለያዩ የሽብር ተግባራቶች መፈጸም ጀመሩ። በስፋት ከአንድ አመት በፊት እንደተዘገበው፣ በርካታ የወልያታ የአዋሳ ነዋሪዎች ላይ ትልቅ እልቂት ፈጸሙ። አሰቃቂ እልቁት። ከኦሮሞ ጽንፈኞች ጋር በማበርም ፣ የራሳቸው የሲዳማዎች ብቻ የሆነች ክልል በመመስረት በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተገነባችህዉን አዋሳ የነርሱ ብቻ ንብረት ለማድረግ ቋመጡ።
አዋሳን የመሰረታት፣ አዋሳ የምትባል ትልቅ ከተማ እንድትኖር ያደረው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው እንጂ ሲዳማዎች ብቻ አይደሉም። ስለዚህ የሲዳማዎች ብች የሆነች አዋሳ ልትኖር አይገባም። አዋሳ ከተማ ራሷን የቻለች ፌዴራል መስተዳደር ነው መሆን ያለባት። የአዋሳ ከተማ ህዝብ እርሱን በማይወክሉ ሰዎች እድሉ ሊወሰንለት አይገባም፣።
Filed in: Amharic