>

ዶር ዳኛችው ፈላስፋ ወይስ ዳኛ? (ሀይለገብርኤል አያሌው)


ዶር ዳኛችው ፈላስፋ ወይስ ዳኛ?
ሀይለገብርኤል አያሌው
* ጀነራል አሳምነው ላይ ፍርድ ለመስጠት ምን መረጃ አለዎት?
ዶር ዳኛቸው በአደባባይ ምሁርነታቸው ይታወቃሉ::ስለ ሞራልና ፍልስፍና ገለጻ ሲያደርጉ የማይደመም ስለ ፖለቲካችን በድፍረት ሲናገሩ የማይደሰት አልነበረም:: ዶር በሕዝብ ዘንድ የተከበሩ  መልካም ሰው በመሆናችው ብዙዎቻችን እሳቸውን ለማድመጥ እንምርጣለን:: ይህ መከበርና መወደድ ስለ መልካም ስብዕናቸውና አድራጎታቸው እንጂ ከሌላ አንጻር አይደለም:: እንዲያውም የእህታቸው የወሮ ገነት ዘውዴ(ዮዲት ጉዲት) ተቃራኒ መሆናቸው ለህሊና ማደራችው የበለጠ ተወዳጅ ያደረጋቸውም ይመስለኛል::
 
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ዶር ዳኛቸው የመርህ አጥር እየጣሱ የእውነትን መንገድ እየሳቱ ባልተገባ መስመር ሲራመዱ አስተውለናል:: በሂደትም የቀድሞ ስብዕናቸው ሚዛን ደፍቶ ወደ መስመራቸው ይመልሳቸዋል ብዬ በግሌ ጠቢቄያለሁ:: እንዳለመታደል የሚኒሊክ ቤተ መንግስት አልጋ የተጠጋው ሁሉ መክሊቱን እየጣለ በኑፋቄ መንፈስ እየተመራ ሲቃዥ ማየት ተለምዷል::
 
እንኳን ከአራት ኪሎ ጆሊ ባር ቤተመንግስት የታደሙት ዶር ዳኛቸው ከሃሬና ኤርትራ አሮጌ ብረት አንግተው የገቡት አርበኞች ትጥቅ ብቻ ሳይሆን ሱሪያቸውን እንደፈቱ አይተናል:: የሰሞኑ የዶክተር ዳኛቸው ሞራል የለሽ ፍርደገምድል የአደባባይ ትንተና የሚያሳፍር የሚያሸማቅና የሕግ ልዕልናን የጣሰ ጭልጥ ያለ አድርባይነት ነው::
 
ዶር ዳኛቸው በአማራ ክልል በባሕር ዳር  በመስተዳድሩ መሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት አስመልክቶ ያደረጉት ገለጻ ሕግ ቢኖር የሚያስጠይቅም በሆነም ነበር:: ግለሰቡ የምርመራ ውጤቱ ተጣርቶ በግልጽ ወንጀለኛው ባልተገለጸበት ሁኔታ የመንግስትን የአንድ ወገን ፕሮፓጋንዳ ይዘው ጀነራል አሳምነው ላይ የሰነዘሩት ውንጀላ አስነዋሪ ነው:: 
 
የአማራው ሕዝብ የክልሉ የጸጥታ አካላትና የሟች ቤተሰቦች ግድያውና ምክንያቱ በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ እውነታው እንዲገለጽላቸው እየጠየቁ ባለበት ወቅት የመንግስትን ተረት ይዞ ይህን ያህል መረን የለቀቀ አስተይየት መስጠት ከአንድ ምሁር አይጠበቅም:: በባሕር ዳር የተፈጸመው እልቂት የአማራ ሕዝብ አንገት ለማስደፉት ከአራት ኪሎ የተቀናበረ ሴራ ለመሆኑ የሚጠቁሙ በበዙበት በዚህ ወቅት አደጋውን አስመልክቶ በነጻና ገለልተኛ አካል እስካልተገለጸ ድረስ ማንም ማንንም መወንጀል አይችልም:: 
 
ለሃቅ ለሕግ ልዕልና ለፍትህ የቆመ እረጅም ዘመን አሜሪካ የኖረ ምሁር ቀርቶ ቡታጅራ የኖረ ራፖር ጸሃፊ አይስተውም:: ከምሁራን የሚጠበቀው ይህንን የሕዝብ ጥያቄ በማስተጋባት እውነት እንዲረጋገጥ ድጋፍ ይሰጣል እንጂ ስሜቱን በዘፈቀደ አይገልጽም::  
 
ይህ ደግሞ ሞራልም ሕግም ፍልስፍናም አይደግፈውም!!!!
የሞቱት ሁሉም ጀግኖቻችን ናቸው!!
Filed in: Amharic