>
5:13 pm - Saturday April 19, 7879

የተረኞቹ ወህኒ ቤት (ሀብታሙ አያሌው)

የተረኞቹ ወህኒ ቤት
ሀብታሙ አያሌው
* “ጋዜጠኛ ኤልያስን ያሰረው አዲስ አበባ ፖሊስ የሽብር ወንጀል የማጣራት ሥልጣን የለውም”
    ጠበቃ ተማም  አባቡልጉ
 
ትላንት በማዕከላዊ ያንን ሁሉ ግፍ ሲፈፅም የነበረ  ኮማንደር ረታ የሚባል ኃላፊ የተረኛው ገዥ የኦዴፓ ሰው በመሆኑ ብቻ የዶክተር አብይ መንግስት ከነቤተሰቡ በቦሌ ኤርፖርት ወደ ጀርመን መሸኘቱን በጥብቅ ስንቃወም ነበር።  በዜጎች ነፍስ ሲቀልዱ ከነበሩት መካከል ሌላኛው የኦዴፓ ሰው የትላንቱ የፍትህ ሚኒስቴር (ሚንስትር ዴታ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ) ዛሬ የአቃቤ ህግ መስሪያ ቤቱ ኃላፊ ሆኖ በጠራራ ፀሐይ በፍትህ ስርአቱ እየተጫወተ ነው።
ጀነራል አሳምነው ፅጌ ህይወታቸው ከማለፉ ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን አሰልጥነው ባስመረቁ ጊዜ “የገጠመን  ፈተና ከ5መቶ ዓመታት በፊት ገጥሞን ከነበረው ፈተና የሚልቅ ነው”  ማለታቸውን ተከትሎ በኦዴፓ አመራሮች ከፍተኛ ቁጣ በተቀሰቀሰ ማግስት የኦዴፓው ሹም የፌደራሉ ዐቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ በቤኒሻንጉል እና በጎንደር  ተከስቶ የነበረውን  ግጭትን በማስታከክ  በጀነራል አሳምነው ፅጌ ላይ የዘረ ማጥፋት የሚል ክስ አደራጅተው ዘብጥያ ለማውረድ አኮብኩበው እንደነበር ከማያወላዳ ምንጭ መረጃ ተጋርቼ ነበር።
የፍትህ ስርዓቱ የተረኛ ገዢ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ መሆኑ በእጅጉ አሳዛኝ ነው።  ለነገሩ  ይሄን መሰል አስተያየት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰነዘረው የህግ ባለሙያም አይናችን እያየ ዘብጥያ ወርዷል።
ወዲህ ደሞ ሌላ የፖለቲካ ሸፍጡ ሰለባ የሆነው ወንድሜ ጓደኛዬ “ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ  በአዲስ አበባ ፖሊስ ሽንት ቤት አጠገብ ለብቻው ጨለማ ቤት በመታሰሩ  የ”ሳይነስ” ህመሙ ተቀስቅሶ እየተሰቃየ ነው”  የሚል አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል።  ተረኞች  ወደ ውድቀታቸው የሚያረጉት ጉዞ በእያንዳንዱ ቀን ስራቸው እየተገፉ እየፈጠኑ ነው።  የተረኞቹ ወህኒ ለኤልያስ እንደ ትላንቱ ነው።  ትላንትም ስቃይ ዛሬም ስቃይ… !!!
      በፍትህ ስርዓቱ ስለሚቀልዱት አሳሪዎች የህግ
      ባለሙያው እንዲህ ይላሉ …
“ጋዜጠኛ ኤልያስን ያሰረው አዲስ አበባ ፖሊስ፣ የሽብር ወንጀል የማጣራት ሥልጣን የለውም”  ጠበቃ ተማም  አባቡልጉ
Filed in: Amharic