>

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦበታል!!! (አምንስቲ ኢንተርናሽናል)

አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ !!
በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦበታል!!!
ዶቼ ቬሌ
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዓመት በመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ላይ ያደረገው ከፍተኛ መሻሻል የኋሊት የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦበታል ሲል የዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አሳሰበ።
ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ባሰራጨዉ ዘገባ እንዳለዉ መንግሥት ሰሞኑን ጋዜጠኞችን ማሰሩና የሐገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር ወታደራዊ ሚስጥር አወጡ ያላቸዉን ጋዜጠኞች እንደሚከስ ማስታወቁ ለፕረስ ነፃነት አደገኛ ነዉ። በምስራቅ አፍሪቃ የአምስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ተጠሪ ጆአን ንያንዩኪ እስሩና የመክሰስ ዛቻዉ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ የታየዉን የፕሬስ ነፃነት የሚደፈጥጥ፣ ሃገሪቱንም ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የሚያመራት እንደሆነ አመልክተዋል።
የድርጅቱ ዋና ተጠሪ የታሰሩ ጋዜጠኞች ሁሉ መፈታት አለባቸዉ ፤ የተመሰረተባቸዉ ክስም ዉድቅ መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል። አምንስቲ እንዳለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት መፈንቅለ መንግሥት ካለዉ የባለስልጣናት ግድያ በኋላ ሶስት ጋዜጠኞች ታስረዋል። ከሶስቱ ሁለቱ በአሸባሪነት ተከስሰዋል።
Filed in: Amharic