>

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ  አገዛዝ እየሰራው ያለው ነውረኛ  ድራማ ቀጥሏል . .  (አቻምየለህ ታምሩ)

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ  አገዛዝ እየሰራው ያለው ነውረኛ  ድራማ ቀጥሏል . .
አቻምየለህ ታምሩ
እንዲህ አይነት የተጨማለቀ የነውረኛነት ጥግ በፋሽስት ወያኔ ዘመን እንኳ መደረጉትን እጠራጠራለሁ!!!
የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ  ከነትንሽነቱ የፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ አገዛዝ ታናሽ ወንድም ነው። ፋሽስት ወያኔ በሥልጣን ዘመኑ በሐሳብ የተለዩትን ግለሰቦች ሁሉ እግር በእግር እየተከታተለ ካላሳደደ፣ ካላሰቃዬና  ስብዕናቸውን ካላዋረደ ፖለቲካ የሰራና ቁሞ የሚሄድ አይመስለውም ነበር።
የፋሽስት ወያኔ አረመኔነት እግር አውጥቶ ሲሄድ ከታየባቸው ጭካኔዎች አንዱ በብርቱካን ሜዴቅሳ ላይ የሰራው ግፍ ነው።  ፋሽስት ወያኔ ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳን አስሮ ቅስሟን  ለመስበር፣ አንገቷን ለማስደፋትና  ራሷን በራሷ እንድታዋርድ ለማድረግ ያልሰራው የቴሌቭዥን ድራማ አልነበረም። ፋሽስት ወያኔ ብርቱካንን በጨለማ ቤት አስሮ በማሰቃየት  ራሷን በራሷ እንታዋርድና ጥፋተኛ ነኝ እንድትል አድርጎ ሞራሏን ለመስበር ቢሞክርም የአረመኔ ክብረ ወሰን መስበሩን ከማሳየቱ  በስትቀር  ሕዝብ በብርቱካን ላይ ባለው አመለካከት  ያደረሰው አንዳች ጉዳት አልነበረም።
የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝም ከፋሽስት ወያኔ የቀሰመውን የጭካኔና የነውረኛነት ትምህርቱን  ተጠቅሞ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ለማዋረድና ለማሳነስ የግል ጉዳዩን፣  ከሱና ከባለቤቱ በስተቀር መንግሥት ነኝ የሚለውን ክፍል ጨምሮ ማናቸውም አካል  ሊይዘው የማይገባውን የጋብቻ ሰርቲፊኬቱን በቴሌቨ ዥን አቅርቦ ተደረገ የተባለው መፈንቅለ መንግሥት ኢግዚቢት መሆኑን  ነገረን። እንዲህ አይነት የተጨማለቀ የነውረኛነት ጥግ በፋሽስት ወያኔ ዘመን እንኳ መደረጉትን እጠራጠራለሁ። የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ የጋብቻ ሰርቲፊኬትን የመፈንቅለ መንግሥት ኢግዚቢት  አድርጎ ያቀረበ  የመጀመሪያው ነውር የማያውቁ  ማጅራት መቺዎች አገዛዝ መሆን አለበት።
እነ ዐቢይ የጀኔራሉን የጋብቻ ሰርቲፊኬት በቴሌቭዥን ያሳዩን የአፓርታይድ አገዛዙ አክቲቪስቶች ላለፉት ሁለት ሳምንታት «በጋብቻ ላይ ጋብቻ ፈጽሟል» እያሉ በአሳምነው ላይ ሲቀቡት  የነበረው ጥላሸት እውነትነት መሆኑን ለማሳየት ይመስላል። ሆኖም ግን አሳምነው በአንድ ጊዜ ሁለት የትዳር ሰርቲፊኬት ቢኖረው እንኳ የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ  ለሚጋቡ ጥንዶች  የጋብቻ ሰርቲፊኬት የሚሰው ጥንዶቹ  ያላገቡት መሆናቸውን  የሚያሳይ መሸኛ ሳያቀርቡ መሆኑንና የዐቢይ ቢሮክራሲ የተሞላው የጋብቻ ሰርቲፊኬትን ያህል ትንሽ ነገር እንኳ ለማንና ምን ቅድመ ሁኔታ ላሟሉ ጥንዶች  እንደሚሰጥ በማያውቁ ሞሮኖች [morons]  መሆኑን  ብቻ ነው የሚያሳየው።
የሆነው ሆኖ ፋሽስት ወያኔ ብርቱካንን ለማዋረድ የሰራው የጭካኔ ድራማ  ብርቱካን  በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የበለጠ ጀግና ሆና እንድትታይ እንዳደረጋት ሁሉ የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝም ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ለማዋረድ እያሰራው ያለው አስነዋሪ ድራማም ዐቢይ አሕመድ የፋሽስት ወያኔ የጭካኔ አገዛዝ ወራሽና ዲቃላ መሆኑን ከማሳየቱ በስተቀር  ጀኔራል አሳምነው ጽጌን  የበለጠ ጀግና ያደርገው እንደሆን  እንጂ  የሚቀንስበት  አንዳች ነገር የለም።
Filed in: Amharic