>

መፈንቅለ መንግሥትስ እናውቃለን!  (አቻምየለህ ታምሩ)

መፈንቅለ መንግሥትስ እናውቃለን! 

አቻምየለህ ታምሩ

 «በየ መንደሩ መፈንቅለ መንግሥት አይደረግም!!!»   ጄኔራል አሳምነው ጽጌ

በኢትዮጵያ የተከሰተ እውነተኛ መፈንቅለ መንግሥት  እናውቃለን። በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ የተከሰተው እውነተኛ መፈንቅለ መንግሥት ከ58 ዓመታት በፊት በ1953 በታሣሡ ግርግር ወቅት የተሞከረው የመንግሥት  የፍንቀላ ነው።

የ1953 ዓ·ም· መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች ብሔራዊውን የመንግሥት ሬዲዮ ጣቢያ ከተቆጣጠሩ በኋላ የንጉሡን መንግሥት ገልብጠው የራሳቸውን መንግሥት ማቋቋማቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ አደረጉ። የንጉሠ ነገሥቱን ልጅ በሬዲዮ አቅርበው ግልበጣውን እንደተቀበሉና  የኢትዮጵያ ሕዝብ መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎችን እንዲቀበል ጥሪ እንዲያቀርቡ አደረጉ።

መፈንቅለ መንግሥት እንዲህ ነው። ዐቢይ አሕመድ መፈንቅለ መንግሥት አድርጎብኛል  ብሎ የሚወነጅለው ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ግን እንኳን እንደ ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ የሬዲዮ ጣቢያ ተቆጣጥሮ መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን በሬዲዮ ሊያውጅ  በአዲስ ፎርቹን ጋዜጠኛ «መፈንቅለ መንግሥት አድርገሀል ወይ?» ተብሎ ሲጠየቅ «በየ መንደሩ መፈንቅለ መንግሥት አይደረግም»  ብሎ መልስ የሰጠውን ነው።

መፈንቅለ መንግሥት ከታች እንደታተመው አይነት  የመንግሥቱ ንዋይ የግልበጣ አዋጅ የሚታወጅበትና አልጋወራሽ አስፋወሰን ኃይለ ሥላሴም ሕዝቡ ፈንቃዮችን ሕዝቡ እንዲቀበል በሬዲዮ ያሰሙት አይነት የፈንቃዮች መንግሥት ዲስኩር የሚሰማበት ድርጊትነው። ከዚህ ውጭ የአዲስ አበባ መደራጀትና የአማራ መጠናከር ያሰጋው የአፓርታይዱ አገዛዝ ትራጄዲ ሁሉ መፈንቅለ መንግሥት ሊሆን አይችልም።

መፈንቅለ መንግሥት እንዲህ በፈንቃዮች  አንደበት በሬዲዮና በልዩ ልዩ አውታሮች በቀጥታ ለሕዝብ የሚታወጅ ስዒረ መንግሥት ነው።

[ድምፁ ከክምችት ላይበራሪያችን ለ – ወዳጆቻችን  የተጫነ ነው]

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2421703321184936&id=100000358765743

Filed in: Amharic