>

ዛሬ ላይ የቤትህ ምሰሶ ሲነቃቀል ካልገባህ ነገ ግጨውን ተሻግሮ የሚመጣው የህወሀት ሚልሻ ያስተምርሀል !! (ሀብታሙ አያሌው) 

ዛሬ ላይ የቤትህ ምሰሶ ሲነቃቀል ካልገባህ ነገ ግጨውን ተሻግሮ የሚመጣው የህወሀት ሚልሻ ያስተምርሀል !!
ሀብታሙ አያሌው 
* ” መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ አደንቃለሁ። መንግስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እያደረገ ያለውን ጥረት ድጋፍ እናደርጋለን።” 
          ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል (የህውሓት ሊቀመንበር)
ይሄንን አጋጣሚ ተጠቅመው ከጎደለው በላይ ሊያጎድሉ፤  ከሞተው የሚልቅ ሊገድሉ፤  ጓዳ ድረስ ዘልቀው የበቀል ጅራፍ ሊያጮሁ…እንኳን ሴራ ኖሮ  “የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ…” ቢሆንኳን ቅሉ፤  በጀግኖቹ ሞት ሰርግና ምላሽ የሆነላቸውን እየታዘብን ነው።
የዶክተር አምባቸው አይነት ልበ ሙሉ፣ የጀነራል አሳምነው አይነት የወንዶች ቁና፤ የአቶ ምግባሩ እና የአቶ እዘዝ አይነት የህዝብ አለኝታዎች…ባንዴ መቀጠፍ  የቤቱን በር ወለል አድርጎ  የዚያን መከረኛ ህዝብ ገመና ውጭ እንዳሰጣው ተመልከት።
ከኦዴፓ እስከ ኦነግ  =  በኢትዮጵያ ስም እየማሉ ለአማራ ህዝብ ጥላቻ ካረገዙት ጉዶች እስከ ህወሓት  አጋጣሚዋን ተጠቅመው ጎንደሬው አለቀ ወሎዬው ተዋረደ ጎጃሜው ተመታ  በማለት አስከሬን እንኳን አፈር ሳይቀምስ ህዝቡ በአውራጃዊነት ተቧድኖ እንዲተላለቅ ያልሞከሩት የለም።
ማን ወንድ ደፍሮኝ ቤቴ ይገባል “ጌታቸው አሰፋን ማሰር አይታሰብም”  ስትል የነበረችው ህወሓት አጋጣሚውን ተጠቅማ ህልሟን እውን ልታደርግ “የፌደራል መንግስት ደጋፊነኝ የእስር ዘመቻው ይቀጥል”  እያለች ነው።   ዳውድ ኢብሳ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አፈናቅሎ፣ 19 ባንክ አዘርፎ አዲስ አበባ የሆቴል ወጪው እየተሸፈነለት፤ ባለሜንጫው ጃዋር መንጋ አሰማርቶ የመንግስትን አቋም እያስቀየረ … አፉ የተሸበበው መንግስት ባህርዳር ላይ ሲዘምት ትርጉሙ ካልገባህ የኸርማን ኮሆንን ቲውተር ገፅ ደግመህ አንብበው።
ያጣህው ሳያንስ አንተን በማትመልሰው ነገር እያወዛገበ እንዳታንሰራራ አድርጎ ሊቀብርህ የቤትህን ምሶሶ ሲነቃቅል ካልገባህ መቼም ሊገባህ አይችልም።  ክልሉን በአዛዥ ናዛዥነት በመከላከያ ወታደር ከብበው ስንቱን ጀግና ወጣት ልሳኑን እየዘጉ (የቀብር ስርዓቱ የተፈፀመ ሰው)  ድምፅ ለመከራከሪያ ሲሰጡህ ካላስተዋልክ ነገ ግጨውን ተሻግሮ የሚመጣው የህወሓት ሚሊሻ ያስተምርሃል።
ልብ ያለው ልብ ይበል የሆነው ሆኗል አይመለስም ያጣሃቸውን ጀግኖች ከወደድካቸው አውራጃ ላይ ተቸክለህ እርስበራስ መወዛገቡን ተወው።  አጋጣሚውን ተጠቅመህ ከቡድኖችም ሆነ ከግለሰቦች ጋር የነበረህን ቂም ለመወጣት ለክፉዎች አጀንዳ ሰለባ የሆንከውም ከራስ በላይ ህዝብ አስቀድም። በእርግጥ የጀግኖቹ ሞት ከቆጨህ ጠላት ህልማቸውን ለማምከን የሚያደርገውን ሴራ መክት።
በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል በመከላከያ ስም ምንጠራ እያደረጉ ያሉት የኦፕሬሽኑ ባለቤት ጀነራሎች ማንነት እና አሰላለፋቸውን በዝርዝር  እመለስበታለሁ !!
Filed in: Amharic