>

እስራቱም በፈረቃ ሆነ እንዴ ?  (ህብር ራድዮ)

እስራቱም በፈረቃ ሆነ እንዴ ? 
ህብር ራድዮ
በአገራችን ኢትዬጵያ ውስጥ የምናያቸው ዙሪያ ገብ ጉዳዬች ብዙዎችን ግራ እያጋቡ እና ወይቸው ጉድ  እያስኙ ይገኛሉ።
በባለፈው ቅዳሜ በባሕር ዳር እና በአ/አ ከተሞች ላይ የከፍተኛ የስቪል እና የወታደራዊ ባለስልጣናት ግድያን ተከትሎ ከ200 በላይ ተጠርጣሪዎች  በቁጠጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
በሁለቱ ከተሞች ውስጥ የተፈጸመውን የግድያውን እና የጥቃቱን እርምጃ  በቅድሚያ ካወገዙት እና በአገሪቱ ውስጥ ሁለገብ የመደማመጥ እና የመስከን መንፈስ እንዲስርጽ  ጥሪ ካቀረቡት መካከከል ግንባር ቀደም የሆነው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የህዝብ ግንኙነት የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ለተለያዩ  የአገር ውስጥ እና የውጪ መገናኛ ብዙሃናት በሰጡት መግለጫ “ለሰላም እና ደህንነት  እንዲሁም መረጋጋት ስጋት ናችሁ ከሚል ውንጀላ እንስቶ ግጭትን በገንዘብ ትረዳላችሁ የተባሉ፣የገዢው የ አማራ ዲሞክራሲ ፓርቲ (አዴፓ )እባል ሆነው ሳለ የአብን አባል ናችሁ ተብለው የታሰሩ ይግኙበታል።” ብለዋል።
ዘግይቶ በደረሰን ዘገባ  የአብን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ክርስቲያን ከተወሰኑ የፓርቲው ሀላፊዎች ጋር በአማራ ክልል ውስጥ በዓለታዊ የድርጅታዊ ስራ ላይ ሳሉ መታሰራቸው ፓርቲው አስታውቋል። አቶ ክርስቲያን ለምን እንደታሰሩ  እና ምን ያህል ጊዜ በቁጥጥር ስር እንደሚሆኑ በውል አልተገለጸም።
በአገሪቱ ውስጥ ሰላምን ማስፈን፣የጸጥታን መታወክን ማስታገስ፣ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር ማዋልን ብዙዎች ቢስማሙበትም  አቶ ክርስትያን ከመታሰራቸው ቀደም ሲል ከዜና አገልግሎት ሮይተርስ ጋር ባደረጉት  ቃለምልልስ ላይ ,”የሰሞኑ  ጥርጣሬ፣ማዋከብ እና እስራት  ዘርን  እና ማንነትን ማእከል ያደረገ ይመስላል።” ብለው ነበር።
ይህም አባባላቸው በዘመነ ደርግ”ገንጣይ አስገንጣዬችን እረዳችሁ፣የእነርሱን ራዲዬ ጣቢያ አዳምጣችኋል…ወዘተ”ተብለው ለእስራት እና ለከፋ እንግልት  የተዳረጉ ወገኖቻችን አሳዛኝ ገጠመኞችለብዙዎቻችን ይቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።
 በደርግ እግር የተተካው ሕዋት/ኢህአዲግም  እንዲሁ “ለ ሽፍቶች መረጃ፣  ስንቅ እና ትጥቅ አቀብላችኋል ።” በማለት አፋን ኦሮሞ  የእስር ቤቶች የስራ ቋንቋ እስኪ መስል ድረስ በ10ሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ማሰቃየቱ የሌላ ብሔር ተወላጅ የሆኑ የፓለቲካ እስረኞች ሳይቀሩ ድርጊቱን በምሬት  ማጋለጣቸው የአደባባይ ምስጢር ነው።
ዛሬም ቢሆን የነጠሩ እና የተጨበጡ  መረጃዎች እና ማስረጃዎች በቅድሚያ ሳይሰበሰቡ” ጊዜው የእኛ ብቻ ነው”የሚሉ ወገኖች  አማሮችን፣ ገዢው የአማራ ዲሞክራሲ ፓርቲ(አዴፒ)ደጋፊዎችን ሳይቀር በስመ አማራ ከባሕር ዳር እስከ አ/አ፣ከድሬደዋ እስከ ወለጋ፣ከከፍተኛ ምሁራን እና የፓርቲ አመራሮች እስከ ተራ ዜጋ እና አባል የማሳደዱ፣የማዋከቡ እነዚያ በአንድ ሰሞን ወደ ሙዚየምነት ይቀየራሉ ወደ ተባሉት  የማጎሪያ ቤቶች እና ድብቅ እስር ቤቶች  በገፍ ማጋዙ  “እድራቱም  በፈረቃ ሆነ እንዴ?”፣ቀጣዩስ ባለጊዜ እና ባለፈረቃ ማን ይሆን ?” የሚል ጥያቄ  ማስነሳት አይቀሬ ነው።
Filed in: Amharic