>

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 57 ሰዎች ተገደሉ!!! (ዶቼቬሌ)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 57 ሰዎች ተገደሉ!!!
ዶቼቬሌ
የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከመካከላቸው በተኙበት በእሳት ተቃጥለው የሞቱም ይገኙበታል። የተቀሩት ደግሞ በጥይት ተመተው መገደላቸውን  17 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ገልጸዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ባንጂ በተባለ ስፍራ የታጠቁ ኃይሎች ባለፈው እሁድ አደረሱት በተባለ ጥቃት የ57 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ጃራ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከመካከላቸው በተኙበት በእሳት ተቃጥለው የሞቱም ይገኙበታል።የተቀሩት ደግሞ በጥይት ተመተው መገደላቸውን  17 ሰዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። 44 ቤቶችም መቃጠላቸውን ተናግረዋል። የአሶሳው ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ዘገባ አለው።

https://m.dw.com/am/%E1%89%A0%E1%89%A4%E1%8A%92%E1%88%BB%E1%8A%95%E1%8C%89%E1%88%8D%E1%8B%8B-%E1%8B%B3%E1%8A%95%E1%8C%89%E1%88%AD-57-%E1%88%B0%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%8B%B0%E1%88%89/a-49361907?maca=amh-Facebook-dw

Filed in: Amharic