>

ብርጋድየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ተገደሉ!!! (ቢ.ቢ.ሲ አማርኛ)

ብርጋድየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ተገደሉ!!!

ቢ.ቢ.ሲ አማርኛ

በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደም አረፉ!!!

ቅዳሜ ዕለት ባህር ዳር ውስጥ ተሞክሯል የተባለውን “መፈንቅለ መንግሥት” መርተዋል ተብለው ሰማቸው የተጠቀሰው የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋድየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ መገደላቸው ተዘገበ።

ብሔራዊው ቴሌቪዥን እንደገለጸው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባህር ዳር ዙሪያ በሚገኝ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን አሳውቋል።

• የሥራ ኃላፊነታቸውን “ከባድና የሚያስጨንቅ… ነው” ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ?

የኢቲቪ ዘገባ ጄነራሉ በምን ሁኔታ በጸጥታ ኃይሎች እንደተመቱ የገለጸው ነገር የለም። ዜናው እንዲሁ በጥቅል መመታታቸውንና ህይወታቸው ማለፉን ብቻ ነው የገለጸው።

ስለብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ በጥቂቱ

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተወለደው ያደጉት ወሎ ላስታውስጥ ነው። አሳምነው ወደ ትግል በመግባት የወቅቱን ኢህዴን በኋላ ብአዴን የተባለውን የአማራ ድርጅትን ከመቀላቀላቸው በፊት በደሴ ከተማ በሚገኘው የመምህራን ኮሌጅው ስጥ መምህር ሆነው አገልግለዋል።

ወታደራዊው መንግሥት በአማጺያኑ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በትውልድ አካባቢያቸው አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ነበር።

• ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው

በማስከተልም ወደ መከላከያ ሠራዊቱ ገብተው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ነበር። ወደ አሜሪካ በመሄድ ወታደራዊ ትምህርት የተከታተሉት አሳምነው ከጦርነቱ በኋላ የጄኔራልነት ማዕረግ አግኝተው በሠራዊነቱ ውስጥ በኃላፊነት ሲያገለግሎ ቆይተዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የመከላከያ ሠራዊቱን ኮሌጅ በበላይነት በመምራትና በማስተማር እንዳገለገሉ ይነገርላቸዋል። ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው በ2001 ዓ.ም ከሌሎች ወታደራዊ መኮንኖች ጋር መፈንቅለመንግሥትለማድረግ በማሴር ታስረው ነበር።

ጄኔራሉ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ስለተባሉ ማዕረጋቸው ተገፎ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ለዘጠኝ ዓመታት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከእስር ተፈትተው ለሃገራቸው የከፈሉት መስዋዕትነትን እውቅና በመስጠ ትማዕረጋቸው እንዲመለስና የሚያገኙት ጥቅም እንዲከበርላቸው አድርገዋል።

የአማራ ክልልም ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለአጭር ጊዜ በቆዩበት የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ሰጥቷቸው ነበር።

• በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደ አረፉ

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተሞከረውና የክልሉን ፕሬዝዳንትና የሃገሪቱን ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹምንና የሌሎች ሁለት ከፍትኛ ባለስልጣናትን ህይወት ከቀጠፈው የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ጀርባ እንዳሉ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስታውቋል።

የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ኃላፊነቱን የተረከቡት አቶ ላቀ አያሌው ለክልሉ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ጄኔራሉንና ሌሎች የድርጊቱ ተሳታፊዎችን ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎች እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።

Filed in: Amharic