>

በጥንቃቄ ልናየው የሚገባ ጉዳይ !! (ሀብታሙ አያሌው)

በጥንቃቄ ልናየው የሚገባ ጉዳይ !!
ሀብታሙ አያሌው
ለአገር መረጋጋት ለህዝብ  ደህንነትና ሰላም ቅድሚያ መስጠት ይገባል!! ነገር ግን  የባህርዳሩም ሆነ የአዲስ አበባው ግድያ…
              1.በጥልቀት ልናይ ልንመረምረው ይገባል
              2.ስክነትና ጥንቃቄ ይፈልጋል !!
              3.መናበብ መረጃ መለዋወጥ ይፈልጋል
              4. ከፍረጃ መቆጠብ ይጠይቃል 
* በኢታማዦር ሹሙ በሰዓረ መኮንን እና በጀነራል ብርሃኑ  ጁላ  በኩል የነበረው የቆየ ፍጥጫ…
* ከወራት በፊት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የመከላከያ ቁመና ያለው ኃይል በይፋ አደራጅቶ ሲያስመርቅ በጭብጨባ ተስተናግዶ  –  በቅርቡ ጀነራል አሳምነው በአማራ ክልል ልዩ ኃይሉን ማደራጀቱ ድንጋጤ መፍጠሩ …
* የፌደራል መንግስት ነጥሎ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን ብቻ  እንደ ስጋት ማየቱ – ከጀነራል አሳምነው ጋር ፍጥጫ ውስጥ መቆየቱ…
* ከሳምንታት በፊት ኦነግ ወሎ ሰሜን ኦሮሚያ ነው የሚል ይፋዊ የአቋም መግለጫ መስጠቱ…
* በወልቃይት እና በራያ ማንነት ተኮሩ ግፍ ከሳምንት በፊት እንደ አዲስ  መጀመሩ…
* ከሳምንታት በፊት የፌደራል መንግስት ያለክልሉ ፍቃድ  ኦፕሬሽን አለኝ ብሎ በሚስጥር ወደ ክልሉ መግባቱና የጀነራል አሳምነው ተቃውሞ…
* የባህርዳሩ ግርግር እንዴት ተነሳ?  የመግደል እቅድ የማን ነበረ ?  ማን ወደማን ተኮሰ ?
* አማራ ክልል በቀናት ውስጥ በሞትም  በእስርም  እነማንን  አጣ ?
* ይህ አጋጣሚ ለነማን ሰርግና ምላሽ ሆነ ?
* የፌደራል መንግስቱ ያሰማራው ኃይል ለመያዝ እየወሰድኩ ነው በሚለው እርምጃ እነማን እየተገደሉ ነው ?
* በቅርቡ ኦነግን ከኦዴፓ ጋር አንድ አደርጋለሁ ብሎ ሲተጋ የነበረው የመከላከያ ስልጣንን ጠቅልሎ የያዘው ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በርግጥ በዚህ ጉዳይ   ገለልተኛ አመራር ይሰጣል ?
          ብዙ ጥንቃቄና ክትትል የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉና ከስሜት ባሻገር እንሁን !!
Filed in: Amharic