>

ለኮሚሽነሩ ጓደኛዬ! ወንድሜ! (ኤርሚያስ ለገሰ) 

ለኮሚሽነሩ ጓደኛዬ! ወንድሜ!
ኤርሚያስ ለገሰ 
ወንድሜ እንደሻው(“እንደሽ!”) ትላንትና በእኔ ላይ የተፈፀመው ድራማ ዛሬ በአንተ ላይ ተገልጦ ስመለከት እጅግ በጣም አዘንኩ። በትዝታም ወደ ኃላ ሄድኩኝ። በዝዋይ ወታደራዊ ካምፕ ለአንድ አመት በነበረን የአብሮነት ኑሮ የፈጠርነው ከወንድምነት የተሻገረ መደጋገፍ ወለል ብሎ ታየኝ። ከዛም በኃላ በብዙ ጭቅጭቅና ትግል ከቀበሌ ወደ ክፍለከተማ፣ ከክፍለ ከተማ ወደ ዞን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ካድሬነት መንጭቀን እንዴት እንዳመጣንህ አሰብኩት። እርግጥ ተጋዳላይ ካሚል አህመድና ፍፁም (የዛሬው በአሜሪካ አምባሳደር) አንተን ወደ መሰላሉ ከፍታ ለማምጣት ተረባርበዋል። በወቅቱ ትምህርት ቀመስ የደኢህዴን ካድሬ እንደ ቁምጣ ያጥር ስለነበር ካሚልና ፍፁም ንቅናቄያቸውን እንደምታጠናክር በተስፋ ተሞልተው ነበር።
እንደሽ! ወደ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንድወስድህ ስትጠይቀኝ ” እኔም መውጫ ቀዳዳዬን እየፈለኩ ነው፣ አንተም ብታስብበት ጥሩ ነው!” በማለት ከነገኳቸው በጣት የሚቆጠሩ ካድሬዎች አንዱ መሆንህን ሳስበው በመጠኑ እፎይታ ተሰማኝ።ሁኔታውን ባልነግርህ ይቆጨኝ ነበር።
የሆነው ሆነ እና ከእለታት በአንዱ ቀን የኢህአዴግ ሊቀመንበሩ ዶክተር አቢይ አህመድ ፓርቲያቸው እና መንግስታቸው የፌዴራል ፓሊስን ጨምሮ የፀጥታ አካላትን የሚመሩ ሰዎች የፓርቲ አባላት ያልሆኑ ገለልተኛ ሙያተኞች እንደሚሆኑ አበሰሩ። እኛም ውሳኔው ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ሃተታ ሰጠንበት። ይሁን እንጂ ቀናቶች ሳይቆዩ የአንተ ወንድሜ የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ሹመት ይፋ ሆነ። ገረመኝ። እርግጥም ለአስርት አመታት የኢህአዴግ አባላት በየካ፣ በቦሌ ስትመለምል፣ ስታደራጅ እና ስታሰለጥን የነበርክ ካድሬ የፓርቲ አባል አይደለህም ተብሎ በጠቅላያችን ስትቀባ ማየት ገራሚ ነው። አስቂኝም ነው። እርግጥ ኑሮ ከሌለው ደኢህዴን ወደ አድርባዩ ብአዴን የነፃ ዝውውር ማድረግህን በተባራሪ ሰምቻለሁ። ይህም ሆኖ የፓሊስ ኮሚሽነርነት ሹመትህን በሰማሁ ወቅት የሆዴን በሆዴ ይዤ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልህ ምኞቴን ሰድጃለሁ። በግለሰብ ደረጃ ያለህ ቁጥብነት እና ጠንቃቃነት ከፓርቲ አባልነት ተሻግሮ ውጤታማ ሊያደርግህ እንደሚችል እምነት አደረብኝ።
የሚያሳዝነው ምኞቴ አመት ሳይሞላው የገባህበት ቅርቃር ወለል ብሎ መታየት ጀመረ። ዛሬ ህሊናህ ነገ ደግሞ ታሪክ የሚወቅስህን የቁልቁለት ጉዞ ተያያዝከው። በሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራው የባለ አደራ ምክር ቤት ( ባልደራስ) ላይ እየፈፀምክ ያለኸው ተደጋጋሚ ወንጀል ” ይሄ ትላንት የማውቀወ እንደሻው ነወይ?” ብዬ በተደጋጋሚ እንድጠይቅ አደረገኝ። ከራሴም ጋር ሙግት ገጠምኩ። የባልደራሱ ንቅናቄ አንተ አዲስአበቤውን ከባለቤት አልባነት ሊያላቅቅህ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ አንተ በተቃራኒው ቆመህ እንቅፋት መሆንህን ስመለከት አበሳጨኝ።
ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለህ በፍፁም ከኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና ጋር የማይሄድ ከሰሞኑ ግድያ ጋር በተያያዘ የሰጠኸውን መግለጫ ስመለከት በአንተ ተስፋ ቆረጥኩ። እኔ ያሳለፍኩት በአንተ ውስጥ ታየኝ። የዛሬ አስር አመት ክስተት።
 በአጭሩ እንዲህ ነበር የሆነው፣
ቀኑን ሙሉ ቢሮ ውዬ ፀሀይ ልታዘቀዝቅ በተቃረበች ሰአት የቀድሞ አለቃዬ በረከት ስምኦን ስልክ ደወለልኝ። ከቢሮ እንዳልወጣሁ ነገርኩት። እሱም ያን ያህል ረጅም ሰአት መስራት ለጤናዬ ጥሩ እንዳልሆነ ተቆጥቶኝ በአስቸኳይ ወደ ቤቴ እንድሄድ ነገረኝ። አስቸኳይ መረጃ ስላለ እቤቴ እንደደረስኩ እንድደውልለት አሳሰበኝ። አቶ በረከት አላስችለው ብሎ ከመስቀል አደባባይ ሲኤምሲ እስክደርስ ድረስ አራት ጊዜ መድረሴን ለማረጋገጥ ደወለልኝ። ሁኔታው ግራ ቢገባኝም ሹፌሩን በብርሃን ፍጥነት አስጋልቤ እቤቴ ደረስኩ።
አቶ በረከት መድረሴን ሲያረጋግጥ በተረጋጋ ሁኔታ ” ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ የቢቢሲ ወኪል የሆነችው ጋዜጠኛ ኤልሳቤት ብለንት ትደውልልሃለች። መፈንቅለ መንግስት
የኢታማዦሩም ሆነ የጡረተኛው ጄኔራል መገደል እጅግ የሚያሳዝን ፣ የሚያስቆጭ እና አገራችን ኢትዮጵያ የደረሰችበት የአመራር ቀውስ ግልጥልጥ አድርጐ የሚያሳይ መሆኑ እሙን ነው። ክስተቱ አንገት የሚያስደፋ ከመሆኑም በላይ የአለም መሳቂያ እና መሳለቂያ አድርጐናል። በትረ ስልጣኑን የያዘው የኢህአዴግ አመራር ዘወትር ከእዩኝ እዩኝ እና የታይታ ስራ ወጥቶ ጥገናዊ ሳይሆን ስር ነቀል ለውጥ እንዲያደርግ የጐተጐትነውም ይሄ እንዳይመጣ ነበር። በህግ የበላይነት ማዕቀፍ ውስጥ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት ቢፈጠር ኖሮ የሆነው ሁሉ ባልሆነ ነበር።
Filed in: Amharic