>
5:13 pm - Tuesday April 20, 9784

ታቦተ ጽዮንን መንካትም ሆነ ማየት አይቻልም!!!' (ታደለ ጥበቡ)

ታቦተ ጽዮንን መንካትም ሆነ ማየት አይቻልም!!!’
ታደለ ጥበቡ
*ዶክተር አብይ በጽህፈት ቤታቸው የፕሮቴስታንት ሰዎችን ሰብሰቦ ሳለ ዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ የተባለ ሰው “”ለሙሴ የተሰጠው የቃልኪዳኑ ታቦት (ታቦተ ጽዮን) ኢትዮጵያ ውስጥ አክሱም ጽዮን ነው ያለው። ይህንን ደግሞ ሁሉም ጥንታውያን የታሪክ ማስረጃዎች የሚመሩት ወደዚህ ነው፣ ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎችና የሀይማኖት አባቶችም ያረጋገጡት ይህንኑ ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ የተሰሩ ዓለም አቀፍ ጥናቶችም የሚያሳዩትም ይህንን ነው፤ እኔም በጥናቴ ያረጋገጥኩት እንደዛው ። ታቦተ ጽዮን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው። በሀገራችን የነበሩ የመንግስታት መውደቅ መነሳት ፣ መበልጸግ መጎሳቆልም ከዚሁ ጋር የተያያዘነው ። ቀድሞ ይሄ ታቦት ብዙ ተአምራቶችን ሰርቷል ወደ ሀገራችን ከመጣ በዃላም እንዲሁ። ብዙ ነገስታት ወደ አክሱም ጽዮን በመሄድ በታቦቱ ከብረዋል። ተቀብተዋል። ይህንን ታቦት  ያከበሩ ነገስታት ኖረውም አለፈውም እስከዛሬ ተከብረዋል ፥ ያላከበሩት ደግሞ ተዋርደዋል ፤ እና ክቡር ጠ/ሚ እርሶም የዚህች ሀገር መሪ ኖትና ስኬት እንዲኖሮት  ከባለቤቶ ጋር ሆነው አክሱም ጽዮን ሄደው ያንን ታቦት ያክብሩ እንዲከበሩ  ስል እመክሮታለሁ” ብለዋል  ዶ/ ር ወዳጄነህ።
*አጭሩ መልስ አይቻልም ነው።ዶ/ር አብይ የኦርቶዶክስ አማኝ አይደለም።በ19ኛው መክዘ የአርመን ፓትርያርክ ተወካይ ጢሞቴዎስ ወደ አኩስም ተጉዞ ታቦቱን ማየት አልቻለም።The sign and seal ወይንም ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ ተብሎ በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው ግራሃም ሐንኮክ ደጅ ጠንቶ አልቻለም።
*ግራሃም ሐንኮክ ወደ አኩስም ሄዶ የቃልኪዳን ታቦት እንዲያሳያቸው ጠባቂ መነኩሴውን  ሲጠይቃቸው “አይቻልም”አሉት።
“ለምን?” ብሎ ጠየቃቸው።
“ይህን የመሠለ ክቡር ዕቃ አናወጣም።በበዓላትም ቢሆን ልዩና ወፍራም በሆነ መጎናጸፊያ ከሸፈንኩት በኋላ ነው የሚወጣው” ብለው መለሱት።
*ዶ/ር ወዳጄነህ ጭራሽ ዶክተር አብይ ከነገሥታቶች ጋር እኩል በማነጻጸር ሚስቱንም ይዞ ታቦትን አይቶ እንዲከብር  የፕሮቴስታንት መሪዎችም እንዲጎበኙት መጠየቁ እጅግ አስገራሚ ነገር ነው።ለአርመን ፓትርያርክ ተወካይ ጢሞቴዎስ እንኳን ያላሳዩቱን ታቦት ለዶ/ር አብይ፤ለሚስታቸው ዝናሽ እና ለፕሮቴስታንት መሪዎች እንደ ሙዝየም እንዲጎበኝ ማሰባቸው ምስጢሩን ካለመረዳት የመጣ ድፍረት ይመስለኛል!!
*ታቦቱን ማየት ሆነ መንካት የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው።እርሱም በእግዚአብሔር ፍቅር፣በልብ ንጽሕና፣በኅሊና የአካል ቅድስና የተመረጠ፤ የኦርቶዶክስ አማኝ አንድ ባህታዊ መነኩሴ ብቻ!!
Filed in: Amharic