>
5:13 pm - Monday April 19, 3688

ህዝቡን በችግር አረንቋ ዘፍቆ ቤተ መንግስቱን የማስረሳት መንግስታዊ ሴራ ትሆን??? (ጌታቸው አሰፋ)

ህዝቡን በችግር አረንቋ ዘፍቆ ቤተ መንግስቱን የማስረሳት መንግስታዊ ሴራ ትሆን???
ጌታቸው አሰፋ
አንድ ፖለቲካውን  በቅርብ ከሚከታተል ሰው ጋር ስለመብራት ፈረቃ እየተወያየን ነው። እኔ የዋሁ ዝም ብዬ በቀጥታ ሳስብ ሰውዬው አስቆመኝ። “እሱን ተወው” አለኝ።  ለፖለቲካው እሱ ይቀርባልና  ጆሮ ሰጥቼ አዳመጥኩት።
ገዥዎች ሕዝብ ወደ ቤተ መንግስት ጉዳይ ሲያተኩር የሚሸርቡትን ሴራ አጫወተኝ። በሽታ እስከማስፋፋት፣ አሰቃቂ አደጋ እስከመፍጠር፣ አገልገሎት እስከማቋረጥ እንደሚደርሱ አወጋኝ። ሕዝብ ስልጣን ላይ ያሉትን ለመተቸት ቀና እንዳይል እንደሚያደርጉት ዝርዝር ጉዳይ ነገረኝ።
 ሕዝብ በእለት ተዕለት ጉዳይ ተወጥሮ በቤተ መንግስቱን በኩል ሲያልፍ እንኳ ገዥዎቹን ማስታወስ እንዲሳነው፣ የራሱን ጉዳይ በትካዜ እያኘከ የቤተ መንግስቱን አጥር አልፎ ወደ ውስጥ እንዳያስብ ሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደሩ ተቋማትን ተጠቅመው ሴራ እንደሚሸርቡ ገለፀልኝ። ይህ ያለና የሚደረግ የገዥዎች አንዱ ስልት እንደሆነ አስረዳኝ።
ግድቦቹ ውሃ የላቸውም እያሉ ዝናብ በሽ በሽ ሲሆንም የመብራት መጥፋቱ የቀጠለበትን የይሆናል ምልከታውን አጫወተኝ። በዚህ አላበቃም። ገዥዎች ከዚህ ያለፈ ሴራን በሕዝብ ላይ ያሴራሉ። ብዙ ክፉ ክፉ ያስባሉ። ብዙ ክፉ ተግባር ይፈፅማሉ። ሰውዬው ስለ ሰሞኑ “ወረርሽኝም” ሌላ የይሆናል ምልከታውን አካፈለኝ። በአራቱም ማዕዘን “ኮሌራ ተከሰተ” ተብሏል። በአራቱም ማዕዘን አንድ ሰሞን ነው ይህ በሽታ ተከሰተ የተባለው።  ትናንት በሰጡት መግለጫ ደግሞ ስሙን በውል የማናውቀው በሽታም ሶማሊና አፋር አካባቢ ተከሰተ ተብሏል። ይህ በሽታ ክትባት የለውም ተብሏል። ይባስ ብሎም ኢቦላ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ስጋት አለ ተብለናል።  ፖለቲካው በሞቀባቸው ሁሉም አካባቢዎች ወረርሽኝ አለ ተብሏል።  ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ፣ ሶማሊ፣ አፋር፣ ደበቡ ክልል ስድስት ወረዳዎች………።  የገዥዎቹ መቀመጫ በሆነችውና ፖለቲካው በሞቀባት አዲስ አበባ ከአንዱ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ኮሌራ  ተስፋፍቷል ተብሏል።
ታዲያ ሕዝብ ይህ ሁሉ ነገር እያለ እንዴት ወደ ፖለቲካው ያተኩራል?
Filed in: Amharic