>
5:13 pm - Monday April 19, 1413

"ከሚገዳደሉ፣ በየክልላቸው ይማሩ!" ያዛኝ ቅቤ አንጓች ያሏል ይህ ነው!!! (አብርሀ በላይ)

“ከሚገዳደሉ፣ በየክልላቸው ይማሩ!”
ያዛኝ ቅቤ አንጓች ያሏል ይህ ነው!!!
አብርሀ በላይ
“ከሚገዳደሉ፣ በየክልላቸው ይማሩ!” ማለት ለኛ አዲስ መርዝ ነች፤ ከዘር ፖለቲካ የተቀመመች። ለዘር ፖለቲካ አቀንቃኞች ግን፣ ወደ ሚመኙት የግንጠላ ፍጻሜ የምታደርስ፣ በዘር ማፅዳት (ethnic cleansing) የታጀበች አዲስ ምዕራፍ ነች።
የዛሬው የህግ እስረኛ በረከት ስምኦን በአንድ ወቅት በኩራትና በማን አለብኝነት መንፈስ ሲናገር – “ኢትዮጵያ ወደብ-አልባ መሆንዋን የተቀበለ ትውልድ አድርሰናል።” አለ። ቀጥሎም “አሰብ የኛ ናት!” እያለ ሲያደነቁረን የኖረው ትውልድም እየከሰመ ነው። ስለዚህ የወደብ ጥያቄ ሙቷል።” ብሎ ነበር።
ይህን ግንዛቤ በመንተራስ፣ የበረከት ጓዶች ጊዜ እየገዙ ያሉት እንዲህ ብለው እስኪነገሩን ድረስ ብቻ ነው። “አዲስ ትውልድ አድርሰናል። ለዚህ ትውልድ ሀገር ማለት ‘ኦሮሚያ’ እንጂ፣ ሀገር ማለት ‘ትግራይ’ እንጂ የማያውቃትን ‘ኢትዮጵያ’ ማለት አይደለም። ካሁን በኋላ ኢትዮጵያ በሚሏት በሌለች ሀገር ጊዜያችንን አናጠፋም።”
===
የአንድነት ኃይሎች ተጠናክረን ኢትዮጵያን ካልታደግን፣ በዘውግ ፖለቲካ አቀንቃኞች ላይ ድል ካላተቀዳጀን፣ ከሰሞኑ የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ግድያ እንደምናየው፣ የግንጠላው ሂደት በተጠናከረና በተለያየ መልኩ ይቀጥላል። በስልጣን ላይ ያሉ፣ በወንጀል የሚፈለጉ ባለስልጣናትም ግጭቱን አጥብቀው ይፈልጉታል።
Filed in: Amharic