>

የባንክ ዘረፋው አዲስ አበባ ደርሷል! 20ኛው ባንክ ያለምንም ግርግር በቀን በብርሃን ተዘረፏል!! (ዘመድኩን በቀለ)

የባንክ ዘረፋው አዲስ አበባ ደርሷል!
20ኛው ባንክ ያለምንም ግርግር በቀን በብርሃን ተዘረፏል!!!
20ኛው ባንክ ያለምንም ግርግር በቀን በብርሃን ተዘረፏል!!
•••
አስከ አሁን በምዕራብ ወለጋ ብቻ ተወስኖ የነበረው የባንክ ዘረፋ አድማሱን በማስፋት እዚያው አዲስ አበባ ከኦህዴድና ከኢህአዴግ ሊቀመንበር፣ ለእኛ ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትራችን ከችግኝ ተካዩ ከአቢቹ ቤተ መንግሥት አፍንጫ ስር፣  ከቄሮው ጠቅላይ ሚንስትር ከሃጂ ጃወር መሃመድ ቤተመንግሥት ባሻገር፣ እንዲሁም ከኦነጉ ፕሬዘዳንት ከኦቦ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ከኢሊሊ ሆቴል አጠገብ በተለምዶ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ – Bank of Abyssinia ሀያ ሁለት ማዞሪያ ቅርንጫፍ በሰላም፣ በጤና ያለምንም ግርግር በቀን በብርሃን በዘራፊዎች ተዘረፏል።  [ ደግሞ ይሄንንም ያን የፈረደበት ጌታቸው አሰፋ ነው ያደረገው በሉኝ አሏችሁ ]
•••
ባንኩ የተዘረፈው ከአንድ ሰዓት በፊት ዛሬ ከቀኑ 10: ከ50 ደቂቃ አካባቢ ሲሆን የአዲስ አበባን ልጆችና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ብቻ በንቃት እንዲጠብቅ የታዘዘው የኦነግኦፒዲኦው ፌደራል ፖሊስም ሆነ የኦቦ ታከለ ኡማ የቄሮ ፎሊስ በአካባቢው ላይ አልነበረም ተብሏል። ዝርፊያው የተፈጸመው በጥቅሴ፣ በሙድ ጭምር ነው ተብሏል። ጨዋታው ፖሊስ ዝር እንዳይል ከተደረገ በኋላ መዝረፍ  በሚለው የዘረፋ ስልት የተካሄደ ይመስላል የሚሉም አዲስ አበቤዎች አሉ።
•••
ዘራፊዎቹ ለዘረፋው ድምቀት የተጠቀሙት የሞተር ሳይክልን ብቻ ሲሆን ባንኩን ዘርፈው ሲያበቁ በመጡበት አኳሃን በሞተር ሳይክላቸው በሰላም ወደመጡበት መመለሳቸው ተነግሯል።
•••
ዘራፊዎቹ ኦፕሬሽናቸውን በሰላም ፈጽመው አከባቢው መራቃቸውን የተመለከተው የኦህዴድኦነግ ፖሊስ ሓይሉን አፍስሶ ይጠብቅ ከነበረበት ከእስክንድር ነጋና ከባልድራስ ቢሮ ተንቀሳቅሶ የተዘረፈው ባንክ ጋ መድረሱም ተነግሯል።
•••
ኤምባሲዎች፣ ቱሪስቶች፣ ባለሀብቶችን በቀን በጠራራ ፀሐይ በአዲስ አበባ መዝረፍ ባህል እየሆነና የአዲስ አበባን ገጽታ እያበላሸ ከመጣ መቆየቱም እየተነገረ ነው።
•••
በቀጣይ የሚዘረፈው ሃያ አንደኛው ባንክ ማን ይሆን? እኔ የምፈራው ግን እነዚህ ስመጥር ዘራፊዎች አንድ ቀን ሆደ ሰፊውንና ችግኝ ተካዩን ጠሚዶኮ ዐብያችንን እንዳይሰርቁብንና እጃችንን አፋችን ላይ እንዳያስጭኑት ነው የምሰጋው።
Filed in: Amharic