>

ከኢሳት የስራ አስፈጻሚ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ!!!

ከኢሳት የስራ አስፈጻሚ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ!!!
 
ጉዳዩ – የኢሳትን መዋቅና አሰራር ማስተካከልን ይመለከታል !!
ጊዜው ኢሳትን የመሰሉ የኢትዮጵያዊነትና የዲሞክራሲ ድምጾችን አገራችን ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ የምትፈልግበት ነው። ኢሳትም ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ መልስ ለመስጠት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ተጠናክሮ ለመሥራት ቃል መግባቱን በድጋሜ ለማስታወስ እንፈልጋለን።
የኢሳት ቦርድ ባለፈው ኤፕሪል ወር ውስጥ ይህንን ጥሪ በወጉ ለመመለስ በስድስት አስፈላጊ የሆኑ ኢሳትን የማጠናከሪያና የማሻሻያ አቅጣጫዎች ከተቋሙ ሠራተኛና የድጋፍ ኮሚቴ ተወካዮች ጋር በመመካር መወሰን እንደሚጀመር አስታውቆ ነበር። በዚህ መሰረት ዛሬ ሜይ 28፣ 2019 ቦርዱ ከመላው ዓለም አቀፍ የኢሳት ባልደረቦች ጋር በመሰብሰብ የመጀመሪያውን ውሳኔ ይፋ አድርጓል።
ይህ ውሳኔ ያተኮረው ኢሳት ኢንተርናሽናልን በባጀት፣ በሰው ኃይል፣ በፕሮግራሞች ይዘትና አቅጣጫዎች እንዲሁም በአስተዳደር አቅም ከዘላቂነት ጋር እንዲጣጣም ማድረግን ይመለከታል። ውሳኔው እንደማንኛውም ተቋማዊ የመዋቅር የማስተካከያ እርምጃ ጊዜያዊ ችግሮችን ሊፈጥር ቢችልም በዘላቂነት ግን ኢሳትን በሁሉም ዘርፍ አቅሙንና ሕዝባዊነቱን በማጠናከር የተመሰረበትን መሰረታዊ ዓላማ እውን ማድረግ ነው።
ይህንን መሰረተ ሃሳብ በደንብ ተገነዘቦ በሚሠራ የኢሳት አስተዳደርና ባለሙያዎች የተወሰነን ውሳኔ የፖለቲካ ፉክክር ጨዋታ ውስጥ እያስገቡ መተርጎም ትክክል አይሆንም። ይህ ውሳኔ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰሞኑን እንደሚወራው በኢሳት ውስጥ ያሉ የጋዜጠኞች የሃሳብ ልዩነቶች ጋር የተያያዘ አይደለም። ኢሳት የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም። በባለሙያዎቹ ውስጥ እንደማንኛችንም የህብረተሰብ አባላት የተለያዬ የግል እምነትና የፓለቲካ አመለካከቶች እንደሚንጸባረቁ ግልጽ ነው። ሆኖም እንደ ሚዲያ ተቋም የኢሳት ሚና የመንግሥትን ወይም የማንንም አንድ ወገን ፍላጎትን መቃወም ወይም መደገፍ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት ያለው አስተማማኝና የተጣራ መረጃ የሚያቀርብ የህዝብ ሚዲያ ሆና ማገልገል ነው።
የኢሳት ግብ በነጻነት፣ በሙያዊ የጋዜጠኝነት ስነምግባር፣ እንዲሁም በሕዝባዊ ዓላማ ላይ ተመስርቶ የሚዲያ ምርቶችን በማምረት፡ በፓለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና፣ ባህላዊ ርእሰ ጉዳዮች እንዲሁም የተጣሩ መረጃዎች በማቅረብ ህዝን ማገለገል ነው። በተለይ አሁን ሀገራችን ባለችበት ሁኔታ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት ማበረታታት፣ የሀገሪቱም ችግሮችና ተግዳሮቶች በዲሞክራሲያዊ መንገድና በውይይት የመፍታትን ባህል እንዲስፋፋ መርዳት ነው።
ይህንን መሰረተ ሃሳብ በደንብ ተገነዘቦ በሚሠራ የኢሳት አስተዳደርና ባለሙያዎች የተወሰነን ውሳኔ የፖለቲካ ፉክክር ጨዋታ ውስጥ እያስገቡ መተርጎም ትክክል አይሆንም። ዛሬ የተጀመረው የኢሳት ማጠናከሪያ በቅርቡም በቦርድ፣ በአስተዳደር፣ በኤዲቶሪያልና በአጠቃላይ የኢሳት አሠራር ላይ ይቀጥላል። ኢሳት በመጀመሪያ የሥራ ምዕራፉ ማለትም በሀገራችን ከ 257 መታት በላይ የተሰራፋውን አፋኝና ዘረኛ ሥርአት በማስወገድ ሂደት ያበረከተውን አስተዋጽኦ በሚቀጥለውም የሀገርና የሕዝብ አንድነትና የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሥራ ምዕራፍ ውስጥም እንደሚቀጥል ጥርጥር የለንም። ለዚህም የኢሳት ቤተስቦችና የድጋፍ ኮሚቴዎች እንደወትሮው ኢሳት የህዝን አይንና ጆሮ ሆና እንዲቀጥል የበኩላችሁን እንድታደረጉ ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ጁን 1 ቀን ፣ 2019 ፣ ዋሺንግተን ዲሲ
የኢሳት ቦርድ ሥራ አስፈጻሚ
Filed in: Amharic