>

"ታግለህ ምን አመጣህ?" (ግንቦት 20 ሲታወስ) ኣብርሃ በላይ

“ታግለህ ምን አመጣህ?” (ግንቦት 20 ሲታወስ)
ኣብርሃ በላይ
“The end justifies the means” ይላል ፈረንጅ። “የትም ፍጪው፣ ዱቄቱን አምጪው” እንደ ማለት ነው።
አንድ ጊዜ የህወሃት ቤዝ ለመያዝ የኢትዮጵያ ሠራዊታችን በድንገት “ዳንሻ ” ደርሶ እነ መለሰ ዜናዊ እና ሌሎች የህወሃት መሪዎች የሚኖሩበት ቤዝ በቁጥጥር ስር ለማድረግ ከፍተኛ ጥቃት ከፈተ። ህወሃት አለቀላት በተባለባት በዛች ቀውጢ ሰዓት፣ በቤዙ የነበሩ እርጉዝ ታጋዮች ሳይቀሩ መሳሪያ ይዘው የመከላከል ውጊያ እያደረጉ ነው።
መሬት ድብልቅልቁ ወቷል። የህወሃት ሴት የጦር አመራሮች (የዛሬዋ ተቃዋሚ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ያሉበት) በዛ ከባድ መሳሪያ መሬትን በሚያንቀጠቅጥበት ወቅት፣ ዋሻው ውስጥ በጠረጴዛ ዙርያ ተቀምጠው ምን አይነት “ፈጣን እርምጃ” ብንወስድ ነው ቤዙን የምናድነውና ህወሃት ከመደምሰስ የምትድነው እያሉ ይነጋገራሉ። የባሩድ ሽታ ሸቶት የማያውቀው የበረሃው ዳንዴው ጨቡዴ ደግሞ ወደ ሱዳን ለማምለጥ ጥቁር ካፖርት ደርቦ፣ ብሪፍ ኬስ ይዞ (ካምፉላጅ መሆኑ ነው) እየተርበተበተ ዋሻው ውስጥ ድራማ ይሰራል። ታድያ ድንገት እጅግ ከባድ የሆነ መሳሪያ ቤዙን ሲመታው ከየት መጣ ሳይባል ዳንዴው ጨቡዴ (መለስ ዚናዊ) ተወርውሮ እነ አረጋሽ የተቀመጡበት ጠረጴዛ ስር ገባ። ከፍርሃት የተነሳ በአራት እግሩ ለጥ ያለው አውሬ ከነ አረጋሽ እግር አለወጣ አለ። እጅግ የምትጠየፈው አረጋሽም “ውጣ አንተ ሽንታም” ስትል ጓዶቿ እንደሳቁ ይነገራል።
ቤዙ የተረፈው ቀን እና ሌሊት ከራያ/እንደርታ አካባቢ ተጎዞ የኃየሎም አርአያ ኃይል ዳንሻ እንደደረሰ ነው። የክልተ አውላሎ ሚሊሻም በገፍ ከቶ፣ ሌት ተቀን ተጉዞ ከተሰዋ በኋላ ነበር የኢትዮጵያ ሰራዊታችን ጥቃት የከሸፈው። የዛ ሁሉ የህወሃት ተዋጊ መሪ ግን – የሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ ሆነና – ወዲ ዜናዊ ነበር። የትግራይ ህዝብ እብሪት የወጠራቸው የህወሃት ሰዎችን ሲያገኝ “ታግላችሁ ምን አመጣችሁ? አገርን አዋረዳችሁ፣ ወደብ አልባ አረጋችሁ እንጂ” ይላል።
ቁም ነገሩ መዋጋት ብቻ አይደለም። “ተዋግተህ ለሀገርና ለወገን ክብር አስገኘህ ወይ?” ነው ጉዳዩ። የተጫወቱብህ ባንዳዎች ሀገራቸውን ባለሁለት ወደብ አርገው፣ ያንተን አገር ብሄራዊ ውርደት አከናነቧት። ጥላቻ አነገሱባት። አንተንም በገዛ አገርህ በክፉ አይን እንድትታይ ተደረክ። ከገባህ በቁምህ ገደሉህ የህወሃት መሪዎች። ማንም ሰው “የጣልያን ባንዳ ነበርኩ” ብሎ ራሱን እንደማያዋርድ ሁሉ፣ የህወሃት ታጋይ ነበርኩ ብሎ የሚመጻደቅ ካለ የእእምሮ ዘገምተኛ ነው።
(ከላይ የተጻፈው እውነተኛ ታሪክ ያወጋኝ ከፍተኛ የህወሃት የደህንነት ሰው ነው)
Filed in: Amharic