>

አዲስ አበባ ትናንት እንዳይኖራት የሴራ ፖለቲካው አንዱ አካል ሆኖ እየተሰራበት ነው!!! (ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ)

አዲስ አበባ ትናንት እንዳይኖራት የሴራ ፖለቲካው አንዱ አካል ሆኖ እየተሰራበት ነው!!!
ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ
* ከምኒልክ ድኩላ ወደ ምኒልክ ትቤት…!
 
* 131 አመት ያስቆጠረውን የዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት ለማፍረስ በግሬደር ዘመቱበት!!!
 
* በ1924 የተመሰረተውና የዘጠና አንድ አመቱ ባለ ታሪክ ቡፌ ዳ ላጋር ሆቴልንም ለማፍረስ ለሰኞ ቀጠሮ ተይዞለታል!!!
 
* የኢትዮጵያን  ታሪክና ቅርስ እያጠፉ ስለ ታሪክ ሰሪነት መደስኮር ታላቅ ስላቅ ነው!!! 
 አዲስ አበባ አራት ኪሎ የሚገኘው የዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ  ት/ት ቤት በመንገድ ማስፋት ዕቅድ ስም ታከለ ኡማ ሊያፈርሰው እንደሆነ አስራት ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ይህንን በ1897 ዓ/ም የተከፈተ ታሪካዊ ትምህርት ቤት ለማፍረስ ግሬደርና እስካቫተር ወደ እጥሩ አካባቢ እያስጠጉ እንደሆነ በዘገባው ተመላክቷል፡፡ት/ቤቱ ከመፍረሱ በፊት ቀድሞ መከላከል ይገባል፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ የኦሮሚያ ባህል ማእከል እየተሰራ በግልባጩ  የአዲስ አበባ ቅርሶች ተፈልገው እየታደኑ እየፈረሱ ነው…።
ቀጣዮቹም በቅርቡ እንደሚፈርሱ ምንጮች ገልጸዋል፡-
እ.ኤ.አ በ1924 የተመሰረተውና የዘጠና አንድ አመቱ ባለ ታሪክ ቡፌ ዳ ላጋር ሆቴል ሰኞ ይፈርሳል።
በልማትና ኢንቨስትመንት ስም ታሪክ እንዳይኖራት እየተደረገች ያለችው አዲስ አበባ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ትናንትን እየተነጠቀች መጓዟን እንድትቀጥል እየተፈረደባት ነው።
ኢንቨስትመንት እና ልማት ታሪክን ጠብቆ መስራት የተከለከለ ይመስል ኢህአዴግ መራሹ አፍራሽ ሀይል አሁንም ለ91 አመታት በአዲስ የኖረውና የበርካቶች የህይወት ትዝታ ማሳያ ተደርጎ የሚነሳውና ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋ ጠንካራ ትስስር ያለው ብፌ ዳ ላጋር ታሪክ ሆኖ ሊቀር የሁለት ቀናት እድሜ ብቻ ቀርቶታል።
ከጥላሁን ገሰሰ እስከ ጎሳዬ ተስፋዬ ያዜሙበት ተወዳጁ ሆቴል ትኩረት እንዲደረግበት መረባረብ ይጠብቅብናል።በዚህ ረገድም የአዲስ አበባ ባህል ቱሪዝምና ኪነጥበብ ዋንኛ ሀላፊነት አለበት።ለቢሮው ሀላፊ ረ/ፕ/ር ስለ ሁኔታው ከትናንት ጅምሮ ስለ ሁኔቴው ጥቆማ ሰጥቻቸዋለሁ።እሳቸውም ሀላፊነታቸውን በመወጣት የበኩላቸውን ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ።
ሆቴሉ ታሪካዊ ስለመሆኑና በተገቢው ምዝገባ ባይደረግለት እንኳን ከጥፋት ታድጎ መስፈርቶቹን እንዲያሟሉ ማድረግ ቢሮው የሚጠበቅበት የቤት ስራ ነው።
ሁላችንም ለአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች መጠበቅ በጋራ መጮኸና ኡስፈላጊውን ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ ስላለብን ሼር በማድረግ የነዋሪነት ግዴታችንን እንወጣ???
Filed in: Amharic