>

የሌንጮ ለታ ነገር !!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የሌንጮ ለታ ነገር !!!
አቻምየለህ ታምሩ
ሌንጮ ለታና  የወንጀል ግብረ አበሮቹ በተለያየ ጊዜ  እየተናገሩ እኛንም ያናግሩናል። ሌንጮ ከሰሞኑ በሰጠው ቃለ ምልልስ የጎሳ ፌዴራሊዝሙ የሚነካ ከሆነ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ሲል ዝቷል። የጎሳ  ፌዴራሊዝሙን ለመከላከልም  «The Origin of Ethnic Politics in Ethiopia» በሚል  የደረተውን ዝባዝንኬ ሰው እንዲያነብ ጋብዟል። በዚህ ዝባዝንኬ ትርክቱ ሌንጮ  በዋናነት የሚከላከለው ዘረኝነትንና የፋሽሽት ወ ያኔንና የናዚ ኦነግ የአፓርታይድ  ፖለቲካ ነው።
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በመንግሥት መሪ ተዋናይነት የሚደረግ ቋንቋ ወይንም ብሔረሰብ ተኮር ጭቆና  እንደነበር ይከራከርና የጎሳ  ፖለቲካን የወለደው ይህ የዘውዳዊ ስርዓት የቋንቋና የብሔረሰብ ጭቆና  ነው ይለናል።
የሌንጮ ጽሑፍ አላማው መቀሌ ለመሸገው ፋሽስት ደጅ ጥናት ስለሆነ «የዘርና የቋንቋ መድሎ ስለነበረ ነው ወያኔ  ወያኔ የብሔር  ፌዴራሊዝሙን  የተመሰረተው» ብሎ የሚከላከልላቸው ቀንደኛ የወያኔ መስራች ፋሽስቶች በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ውስጥ  በቋንቋና ነገድ ሳይገለሉ «ዲታ» የሚባሉ መሳፍንትና መኳንንት ልጆች እንደነበሩ ማሰብ አይፈልግም።
ሌንጮ በንጉሡ  ዘመን ነበር የሚለውን «መንግሥት መር» የዘርና የቋንቋ አድሎና ጭቆና በአስረጅነት ለማስረገጥ በ1928 ዓ.ም. የትምህርት ሚኒስተር የነበሩት ሳሕሌ ጸዳሉ  አሰራጩት ያለውን  ባሕሩ ዘውዴ በ2002 ዓ.ም.  ባዘጋጀው መፍሐፉ ውስጥ ያሳተመውን ሰርኩላር ነው። ሳሕሌ ጸዳሉ ያሰራጩት የመንግሥት ፖሊሲ ያልነበረ ሰርኩላር የአረማዊ ቋንቋዎች በትምህርት ቦታ አይሰጡ የሚል መልዕክት ያለው ነው።  በዚያ ዘመኗ ኢትዮጵያ  በፈረንሳይኛ፣ በአረብኛ፣ በጥሊያንኛ፣ ወዘተ ቋንቋዎች ትምህርት ይሰጥ ነበር። ሳሕሌ ጸዳሉ ትምህርት በነዚህ  አረማውያን ቋንቋዎች መሰጠት የለበትም፤ በአማርኛና ግዕዝ ይሰጥ ያሉትን ነው  የፓስተር ለታ ልጅ ኦቦ ሌንጮ  አረማዊ የተባለውን የኦሮሞ አድርጎ ኦሮሞውን ይሰድብበታል።
ሌንጮ የብሔር ጭቆና ነበር ብሎ ከሰባ ዓመት በፊት የሳሕሌ ጸዳሉን ሰርኩላር ሊጠቅስ ሲሄድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ15 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለብዙ ዓመታት ይሰጥ የነበረውን ብሔራዊ የፊደል ሠራዊት መርሀ ግብርና  ደርግ ራሱ  የብሔረሰቦችን  ችግሮችን ለማቃለል  በሚል  የብሔረሰብ ኢንቲቲዩት ብሎ ያቋቋመውን ተቋም መጥቀስ አይፍለግም፤  ምክንያቱም  ፋሽስት ወያኔዎችና ናዚ  ኦነጋውያን   የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥትና የደርግን አገዛዝ ማውገዝ እንጅ መጥቀስ አይፈልጉምና።
ሌንጮ ለታ እፍረት የሚባል ነገር ሲያልፍ የማያውቀው ሰው  መሆኑን ለመገንዘብ  ስለ ኤርትራ መገንጠል  የተናገረውን አዳምጡት። ኤርትራ የተገነጠለችው የጎሳ  ፌዴራሊዝሙን የወለደው  የቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሴ መንግሥትና   የደርግ  አገዛዝ የብሔር ጭቆና  ነው  በማለት ሌሎችን  ይከሳል። ጤና ይስጥልን ኦቦ ሌንጮ! ኤርትራን  የሸጣት ማነው? ኤርትራን በቀዳሚነት ከሸጧት ነጋዴዎች መካከል ዋናው  አንተ አይደለህም? በኤርትራ ጉዳይ  ኤርትራውያን እንጂ ኢትዮጵያውያን ምንም አያገባቸውም ብለህ የፋሽሽት ወያኔና የናዚ ኦነግን የሽግግር  መንግሥት ተብዮ ወክለህ በአስመራ አደባባይ ንግግር ያደረግኸው  አንተ አይደለህም? ከ27 ዓመታት በፊት ናዚ ኦነግና  ፋሽስት ወያኔ  ሆናችሁ በመስማማት  የሸጣችኋትን ኤርትራን  ዛሬ የጎሳ ፌዴራሊዝሙን  ለመከላከል  ስትል በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በደርግ የብሔር ጭቆና ስለተካሄደ የተገነጠለች አድርገህ  ልታቀርባትና የጎሳ ፌዴራሊዝሙ ከፈረሰ የኢትዮጵያ  ክልሎች እንደ ኤርትራ ይፈረካከሳሉ ብለህ ለመናገር እንዴት ሞራሉን አገኘህ ?
በማይዋሽበት ዘመን እየኖረን  ደርግና ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የብሔር ጭቆና ስላካሄዱ ተገነጠለች ያልሀት  ኤርትራ እንድትገነጠል  አንተ ያደረግኸውን እስቲ ላስታውስህ? እነሆ ኤርትራ እንድትገነጠል የሽግግር መንግሥት ተብዮውን ወክለህ ያደረግኸው ንግግር አዳምጠው! ኤርትራ እንድትገነጠል ይህንን ንግግር ያደረግኸው ሰውዬ በምን ሞራልህ ነው ደርግንና ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በኤርትራ መገንጠል ልትከስና የጎሳ ፌዴራሊዝም ባለመኖሩ  ኤርትራ ለመገንጠል እንደበቃች አድርገህ  ለመተረክ  የመቃኸው?

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2338831982805404&id=100000358765743

Filed in: Amharic