>
5:13 pm - Sunday April 20, 7236

የአፄ ቴዎድሮስ ፀባይ በውጭ ዜጎች አንደበት (ጳውሎስ ኞኞ)

የአፄ ቴዎድሮስ ፀባይ በውጭ ዜጎች አንደበት
ጳውሎስ ኞኞ
ሔነሪ ፕላንክ ፦ በተለያዩ ቦታዎች እየሰፈሩ ንፁህ አየር መሳብ የሚወዱ፤ማንበብ የሚወዱ፤ ልዩ የማስታወስ ችሎታ ያላቸው ከወራት በፊት ከአመታት በፊት ለተላከላቸው ደብዳቤዎች በትክክል አስታውሰው መልስ የሚሰጡ፤ ማልደው መነሳት የሚወዱ፤
ዱፋታን፦ አፄ ቴዎድሮስ ድሆችን ራሳቸው እየተቆጣጠሩ ይጠብቃሉ፤ ድኳናቸው በተተከለበት ሁሉ የድሆችን አቤቱታ ማደመጥ ይወዳሉ፤ ሁሌም ስራ ከመጀመራቸው በፊት የድሀን አቤቱታ ይሰማሉ፤ በጉዞ ላይ በሳምንት በሺሆች የሚቆጠር ብር ለድሆች ይሰጣሉ፤
ሔነሪ ብላንክ፦ በምግብ በኩል የማይስገበገቡ በቀን አንዴ ብቻ መብላት የሚወዱ በጾም ወቅት እንጀራ ህምእህል ወጥ በፍስክ አሳና የስጋ ወጥ ይበላሉ፤
ዎልዲሜር፦ አንድ ቀን ከአፄ ቴዎድሮስ ጋር በየባላገሩ ስንዘዋወር አንዲት ደሀ ሴት ምንም ልብስ ያለበስች አጋጠመን ንጉሱም ከበቅሏቸው ወርደው የለበሱትን ሸማ እና በርከት ያለ ገንዘብ ሰተው ሰደዷት
ፕላውዴን፦ የባሪያ ንግድን አጥብቀው የሚቃወሙ ናቸው ፣የተሸጡ ባርያዎችን እሳቸው እንደገና እየገዙ ነፃ ያወጧቸው ነበር ፣
ዎልድሚር፦ ብዙ መቶ ባሪያወችን ነፃ አስወጥተው እነዚህን ወጣቶች ጥበብ እና ሀይማኖት አስተምራቸው፣የሚያስፈልገውን ሁሉ  የምችለው እኔ ነኝ ብለውኛል
ሄነሪ ፕላንክ፦ አፄ ቴወድሮስ ሽጉጣቸውን በትራሳቸው ሳያደርጉ። እና የተለጓመ መሳሪያ ከአጠገባቸው ሳያስቀምጡ አይተኙም ነበር።
Filed in: Amharic