>

አይቆሜው የህገ ውጥ ቤት ሥራና፤የማፍረስ ዘመቻ (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)


አይቆሜው የህገ ውጥ ቤት ሥራና፤የማፍረስ ዘመቻ

መንገሻ ዘውዱ ተፈራ

ህገ ወጥነት፤ለአንድ ሐገርና ህዝብ፤ትልቅ የስጋት ምንጭ ብቻ ሳይሆን፤የጥፋትም መስረት ነው።ዛሬ በዓለም ላይ፤በተረጋጋ ማህበራዊ፣ባህላዊና፣ኢኮኖሚያው ይዞታቸው የሚገኙ ሐገራት ዋናውና ትልቁ ሚስጥራቸው፤በህጋቸው ላይ አለመደራደራቸውና፤ህጋዊነትን ከአስትንፋሳቸው በላቅ፤ትልቅ ዋጋ ሰጥተው መገኘታቸው ነው።በአፍሪካ በአንድም ሐገር፤የተረጋጋ ማህብራዊ፣ባህላዊና፣ኢኮኖሚያው ይዘት ያለው ሁኔታ ለአለመኖሩ፤ዋናውና ቁልፉ ችግር፤ይኸው በወጣ ህግ ላይ የሚደረግ ድርድርና፤ህገ ወጥነት ነው።ይህ በህግ ላይ የመደራደርና ህግ መጣስን፤የሚጀምረው ደግሞ፤መሪ ተብየው ነው። ሲጀምር በህግ ተገድቦ የተሰጠውን ስልጣን፤ከስልጣን ሱሱ ላለመውጣት፤ህግን በመሻር የስልጣን ዘመኑን ከማራዘም ጀምሮ፤ለሚሰት፤ለልጅ፣ለጓደኛ፤ብሎ የሚሻራቸው ህጎች የትየሌሌ መሆናቸው ነው።ታዲ ይህ ይመራኛል ተብሎ አምነትን ኃላፊነት የተጣለበት፤የመጨረሻውን የኑሮ ጣራ እኖረ ያለው መሪ፤አምነት አጉዳይ ሆኖ ህግ ሲጥስ፤በኑሮ ጫና፤አማራጭ በማጣት፤ህግ የጣሰውን ድሃ ብቻ፤ለምን እንደ ትልቅ ወንጀለኛ እናየውአለን?ይህ ሲባል ህገ ወጥነት ይቅርታ ይደረግለት፤ይስፋፋ፤አንተወው፣ይቀጥል ማለት አንዳልሆን በደንብ ይሰመርበት።ህገ ወጥነት አይቀጡ ቅጣት ሊጣልበት የሚገባ ተግባር ሆኖ ከመሪው ይጀምር ለማለት ነው አለበለዚያ “መበደል መበደል ወታደር በድሎአል፤ግን ገበሬ ይካስ”አስተሳሰብ በ21ኛው አያሰኬድም ለማለት ነው።

ነገር ግን፤ይህ አይቀጡ ቅጣት ምን ይሁን?አንዴት ይፈፃም? በማን ይፈፀም ነው ትልቁ ፈተና? ለዚህ ደግሞ ነገሮችን በቅንነት ከእራስ ፍላጎት ወጥቶ ማሰብ ከተቻል፤የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካልት በመለየት፤በላሙያዎችን በማሰባሰብ ሁኔታዎችን፤በአቅም ተመስርቶ፤ሰፋ አድርጎ ማየትና መወሰን ይቻላል።ህገ ወጥነት ሁልጊዜ የሚከሰተው፤የመንግስት ህግን የማስከበር አቅም ሲዳከም በሎም አለመቻሉ ሲረጋገጥ ነው።ለዚህ የእራሳችን የኢትዮጵያ የህገ ወጥ ቤት መስፋፈት ሂደት ማየት ይቻላል፤ህገ ወጥ ቤት ስራ በኢትዮጵያ የተጀመረው፤ከ1976ዓ/ም፤የቀይ ኮከብ ዘመቻ ማብቃትና፤ከዚህ ዘመቻ ማግስት፤በወታደሩም ሆነ መላው ኢትዮጲያዊ፤ከደግር ይጠብቅ የነበረው፤ስልጣንን፤ለህዝባዊ መንገሥት የማስተላለፍ የቃልኪዳንና፤ህግ መከበር ተግባር የውሃ ሽታ ሆኖ ሲቀር ነው።በዚህም ሐገር ጠባቂ ሰራዊቱም ሆነ፤ሌሌው አስፈፃሚ ስራተኛ፤ህዝብ ኃላፊነቱን ቸላ አለው ወይም ተወው፤ይህ ማኩረፍም ሆነ መድፈጥ ደግሞ የኢትዮጵያን የመቅጫ አርምጃ ነው።ውጤቱም አይደለም ቤት መስራት፤ለደቂቃ ቁጭ ብሎ አርፎ ለመነሳት፤ምን ይለኝ ይሆን ተብሎ ይፈራ የነበረው፤ደርግ ወደ ጥርስ የለሌው አንበሳ መሻጋገሩን አስረዳ። ይህ ደግሞ ለህግ አልበኞች፤ጥሩ አጋጣሚና ትልቅ አድል ሆነ፤ህገ ወጥ ስራን መለማመድና መፈፀምም ተጀመረ።በአዲስ አበባ፤የመጀመሪያው፤ሰፋ ባላ ቤት ቁጥር ህገ ወጥ መሬት ወረራና ግንባታ፤”የጨረቃ ቤት ተብሎ ወርቃማ ስያሜ ተሰጥቶት” መስፋፋት የጀመረው ከ1980 ዓ/ም ጀምሮ ነው።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤በፖሊስ ኃይል ለማስፈረስ ቢሞክርም፤የጨረቃን ቤትን መልሰው ከመሰራታቸው ግን ማቆም አልቻለም። ይህ ማለት፤ህገ ወጥ መሬት ወረራውና ግንባታው፤በዚያ ጊዜ ብቻ ፈነዳ ማለት አይደለም፤ምናልባት አንደዚህ በመደዳ፤ምሪት መስሎ ባይሰራም ከዚያ ሁለት ሦስት ዓመታት ቀደም ብሎ አለፎ አልፎ አንደነበር መገመት ከባድ አይደለም።በየክፍለ ሐገሮች ደግሞ፤የዚህ ወሬ እየተሰማ፤ከ1985ዓ/ም ጀምሮ፤ምናልባት ትንሽ ቀደም ያለባቸውም ቦታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ተጀምሮ ይኸው በመላ ሐገሪቱ መብት ሆኖ ቀረ።

አንዳንዶች ይህ ነገር፤በአስቸኳይ በባለሙያ ጥናት ተካሂዶበት ዘላቂ መፍትሔ ይበጅለት፤አለበለዚያ ነገ የሚፈጥረው ችግር ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል፤በማፍረስ ወይም ቀድሞ ህግ የጣሰውን፤እውቅና በመስጠት፤ይዞታውን ወደ ህጋዊነት መቀየር ችግሩን ይበልጥ ያሰፋዋል አንጅ አይቀርፈውም።ሌላው ዜጋም ነግ ተመሳሳይ ወንጅል ስርቶ፤ለምን በአኔስ ጊዜ ይላል፤የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።ነገር ግን በየጊዜው የሚመጡ ኃላፊዎች፤ከዚህ በኃላ በኃይል እናቆመዋለን የሚል አንድ አይነት መልስ ከመስጠት በስተቀር፤ሲያቆሙትም አይታይም፤ጭራሽ ሲጨምር፤ይባሰ ብሎ ወደ አልታወቀበትም ትንንሽ መንደሮችም ሲስፋፋ በየጊዜው በየዓመቱ፤የሰው ህይወት እልፈት፣አሮሮና ለቅሶ ብቻ፣ የሚታይበት፣ዓለምንም ግራ ያጋባ፤የተለመደ ተግባር ሆኖ ይኸው አሁን ድረስ አለ።

ትላንትም ዛሬም ምናልባት ነገም፤ቤቱን በማፍረሰም ሆነ፤ሰዎችን በማንገላታት፣በማጎሳቆል ህገ ወጥ መሬት ወረራንም ሆነ ግንባታ መስቆም አልተቻለም። ዙሮ ዙሮ የምንጎዳው እኛና፤ይህችው ተሸክማ ይዛን የምትነገላተው እናት ሐገራችን ብቻ ናት። ስለለዚህ ቢቻል ከመጣነው ጊዜ ስለማይበልጥ፤ከላፈው ተሞክሮአችን፤ሰዎቻችን ከምናጣ፤ሁኔታዎች ሰፋ አድርገን በማየት ከማህበረ ሰቡ፤ባለሙያ የተውጣጣ ግብረ ኃይል፤በመመደብ፦

1ኛ. ለዚህ ህገ ወጥ መሬት ወረራና፤ግንባታ መነሻው ምንደን ነው?
2.ኛ. በዚህስ ተዋናዮቹና ተጠቃሚዎቹ አነማን ናቸው?
3ኛ. ይህን ህገ ውጥ መሬት ወረራና ግንባት፤ለአንዴና ለመጨረሻ አንዳይደገም፤አይደለም ህገ ውጥ ቤት መስራትና ወረራ መፈፀም፤ኃሰቡን ለመስማት አሰከሚጠላ የሚያደርስ፤ምን አይነት አርምጃ ይወሰድ?
4ኛ. ሰለ እርምጃውስ ህዝቡን፤ህገ ወጡን ጨምሮ አንዴት ወደ ጋራ ስምምነት እናምጣው፤መጥቶስ በተለይ ማፍረሱንም ሆነ፤ቅጣቱን እራሱ ህገ ውጡ፤ህዝብንና ሐገርን ይቅርታ ጠይቆ አንዲፈፀም የሚያደርግ ምን ስራ እንስራ?
የሚሉ ጥናቶችን አካሂዶና አቅድ አዘጋጅቶ ቢሰራ፤በመንግሰት ደመወዝና ቢሮ ተቀምጦ፤መሪ ፕላን እያነበበ፤ለዚህ ወንጀል፤የመጀመሪያ ህገ ወጥ ስራ ቀያሽ፤አስፈፃሚና፤ፈፀሚውን የመንግሥት የመንግሥት ሰራተኛ፤ፍጥጥ ብሎ ለማግኘት መቻልና፤ኢትዮጵያም ከዚህ “አይቆሜው የህገ ውጥ ቤት ሥራና የማፍረስ ዘመቻ” ተገላግላ፤ህዝቦቿም በየዓመቱ ከምናሰማው ዋይታና ልቅሶ የሚገላግልና ነፃ የሚያወጣ፤በዓለም ዘንድም፤በየዓመቱ የሚታየውን የተባለሽ የዋይታና ልቅሶ ገፅታች የሚቀይር፤ልብ አንዲሰጠን ፈጣሪ ይርዳን።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላዓለም ትኑር።

Filed in: Amharic