>

"ተጨማሪ መከላከያ በኦራል ከመጣ በሗላ ወደ ኦነግ ወታደሮች ሲቀላቀሉ አይተናል..!!!" የግፉ ሰለባ የሆኑ የአይን እማኝ ገበሬዎች

“ተጨማሪ መከላከያ በኦራል ከመጣ በሗላ ወደ ኦነግ ወታደሮች ሲቀላቀሉ አይተናል..!!!”
የግፉ ሰለባ የሆኑ የአይን እማኝ ገበሬዎች
መላኩ ማሩ
 
ሁሉም ነገር እየሆነ ያለው በታቀደና በተቀነባበረ ሁኔታ ነው፤ እስቲ ጥቂት እናስተውል በመጀመሪያ ከሳምንታት በፊት ኦነግ ለሁለት መሰንጠቁንና አዲስ አበባ ካለው አመራር ትእዛዝ እንደማይቀበል የሚያሳይ ድራማ በመግለጫ መልክ ወጥቶ እንድናየው ሆነ ይች እንግዲህ “መንግስት የኦነግ አመራሮችን ሆቴል አስቀምጦ በህዝብ ገንዘብ እየቀለበ አስጨረሰን ” የሚል ከህዝብ የሚመጣን ቅሬታ ዳይቨርት ለማስደረግ ታስቦ መሆኑ ነው ፤ ሲቀጥል ፍጅቱ ኦህዴድ ውስጥ ባሉ አክራሪ አመራሮች ለወራት ጥናትና ዝግጅት ሲደረግበት የከረመ ሰራዊቱም በስልጠናና በትጥቅ ሲደራጅ የቆየ በመሆኑ ወደ ተግባር ሲገባ የኦነግ አመራሮች ነገ ቢያስጠይቀንስ ብለው ተቃውሞ እንዳያነሱ በማለት ባልተጻፈ ግን ሁሉም እንዲያውቁት በተደረገ መመሪያ በየትኛውም መንግስታዊ ሚድያ እንዲሁም በመንግስታዊ ባለስልጣናት አንደበት “ያልታወቁ ታጣቂዎች” በሚል ለአሸባሪው ቡድን ከለላ እስከመስጠት የተደረሰበት የዘር ፍጅት ነው እየተካሄደ ያለው።
አሸባሪው የኦነግ ሰራዊ በግልጽ በሚያራምደው ኦህዴዶች ከጀርባ በሚዘውሩት “የታላቋ ኦሮምያ” ቅዠታቸው ዛሬ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራና የደቡብ ህዝቦች ለሞት ለአካል ጉድለት እና ለመፈናቀል እየተዳረጉ ነው።
በአለም ላይ ከታዩ አሰቃቂ ሁኔታዎች የከፋው የጭካኔ ተግባር ላይ የተሰማራው ጦር ለእነርሱ የታቀደለትን ግብ  እየመታ ያለ “ጀግና” ጦር እንጂ ሽብርተኛ አይደለም ።
ለመሆኑ ያለው መንግስትስ በማን እሚመራ ይመስላችዋል? ለምንስ ከፋተኛ ገንዘብ በተለይም ከአረቡ አለም በስጦታና በብድር ስም ያገኛል? ከኢትዬጲያ የተሻለ ዴሞክራት የምስራቅ አፋሪካ አገር ጠፋቶ ነው? አይደለም አንዳንድ የውጭ መንግስታት እንዲሁም የተለያየ አላማ ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ከ መንግስት ጋር በተጠና መልኩው ትልቅ Operation ውስጥ ናቸው::
 ተላላኪዉ አብይ አስተዳደር  እየፈፀመ ያለዉ የዘረኝነት ግፍና አፈና ከግዜ ወደ ግዜ  እየጨመረ መጥቷል በመሆኑም ሰሞኑን በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ  ዞን በአጣዬ እና አካባቢ እየተፈፀመ ያለዉ የዘር ማጥፋት/ ጄኖ ሳይድ/ መንግስት ተብዬ ዉ ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት አለመስጠቱ  እጅግ አሳፋሪ ተግባር  ከመሆኑም በላይ እርዳታ እንዲሰጡ የተላኩት የመከለላከያ አባላት ወደስፍራው ቢደርሱም  ለአሸባሪው የኦነግ ሰራዊት ሽፋን እና ከለላ ከመስጠትም በላይ እህል ውሀ ሲያቀርቡ ነው የታዩት። ይህ መንግስታዊ ደባ ጉዳዩን የበለጠ አሳዛኝ ከማድረጉም በላይ ህዝቡ በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጎታል ፡፡
 
ከአይን_እማኞች_የምስክርነት_ቃል..!
እውነቱን አለም ይየው አለም ይስማው
“መንግስት የላከው መከላከያ ኦነግን ሲደግፍ ባይናችን አይተናል…።”
☆”የቆሰሉ የኦነጎችን በአንቡላንስ ሲልኩ አይተናል ።
የጦር መሳሪያ ጥይት ሲሰጧቸው አይተናል ።
መኖሪያ ቤት ና ቤተክርስቲያን ሲዘርፉና ሲያቃጥሉ የነበሩ ኦነጎችን ይበቃችሗል የያዛችሁትን ይዛችሁ ውጡ ሲሉ ሰምተናል..።”
•”ተጨማሪ መከላከያ በኦራል ከመጣ በሗላ ወደ ኦነግ ወታደሮች ሲቀላቀሉ አይተናል።በሀይላንድ ውሀ እና የምግብ አቅርቦት ከመከላከያ ሲሰጣቸው በአይናችን አይተናል ..።”
☆”መንግስት ከእነ መከላከያ ሰራዊቱ  ለኦነግ መሳሪያ እየሰጠ ነው ወገኖቻችንን ያስጨረሰው ። “
እንግዲህ ይሄ የዘር ማጥፋት ስራ እንዳይወጣባቸው ነው ጌታቸው ጉዲና የተባለ የመከላከያ ሹም
በኢቲቪ ሀሰት ሲነዛ የነበረው….።”
Filed in: Amharic