>

ለናዝራዊት ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል የተጠረጠረችው ጓደኛዋ በቁጥጥር ስር ዋለች!!! (ኢ.ቢ.ሲ)

ለናዝራዊት ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል የተጠረጠረችው ጓደኛዋ በቁጥጥር ስር ዋለች!!!
ኢ.ቢ.ሲ
በቻይና በእስር ላይ ለምትገኘው ናዝራዊት አበራ ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል ወንጀል የተጠረጠረችው ስምረት ካህሳይ ከጓደኛዋ ሰለሞን ፀጋዬ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡
የናዝራዊት አበራ አብሮ አደግ ጓደኛ እንደሆነች የሚነገርላት ስምረት ካህሳይ በ5 የሻምፖ እቃዎች ኮኬን የተሰኘው አደንዛዥ ዕጽ አታላት ቻይና እንድታደርስላት በማድረጓ ተጠርጥራ ነው በትናንትናው እለት የፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላት፡፡
ከብራዚል ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ቻይና እንዲላክ የተደረገው አደንዛዥ ዕጽ ከመኖሪያ ቤቱ በመገኘቱ የስምረት ጓደኛ ሰለሞን ፀጋዬ የተባለው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በጠቅላይ አቃቢ ህግ የተቋቋመው የምርመራ ቡድን ከብራዚል በኢትዮጵያ ወደ ቻይና ስለተጓጓዘው ዕጽና ከሽያጩ የሚገኘውን የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ወንጀሎችን የማጣራት ስራ መጀመሩ ታውቋል፡፡
የምርመራ ቡድኑ በቻይና በዕስር ላይ የምትገኝ ናዝራዊት አበራ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፋ እንድትሰጥ ጭምር እንደሚሰራ ከጠቅላይ አቃቢህግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሳምራዊት ካህሳይ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በቁጥጥር ስር ዉላ በዋስ የተለቀቀች መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በድጋሚ በቁጥጥር ስር ልትውል የቻለችው ፖሊስ አዲስ መረጃ ማግኘቱን ተከትሎ ፍርድ ቤት እንድትያዝ በመፍቀዱ ነው፡፡
Filed in: Amharic