>

የአፋኙ ስርአት የአፈና አካል ስለ ነበረው ኢ.ን.ሳ. ጥያቂት ያጫሩብኝ ጉዳዮች ...?!? (ነአምን ዘለቀ)

የአፋኙ ስርአት የአፈና አካል ስለ ነበረው ኢ.ን.ሳ. ጥያቂት ያጫሩብኝ ጉዳዮች …?!?
በነአምን ዘለቀ
ሰላም ወገኖች:
አንድ የከነከነኝ ጉዳይ አለ። ከኢንፎርሜሽን መርብ ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጋር ተያይዞ የወጣውን ዘጋቢ ፊልም ይመለከታል። ዘጋቢ ፊልሙን እንዳአጋጣሚ ሆና በርከታ ጓደኞቼና ጓደኞች እንድመለከተው ልከውልኝ ለማየት ግን ጊዜና ትኩረት የሰጠሁት ትላንት ነበር። እንደዚህ መሰል ፊልሞች ወደ ሁሏ ሄዶ መስራቱ አሰፈላጊም ጠቃሚም ነው ብዬ አላምንም። ይህን መሰል ስራዎች የመሪዎችን ማንነት፣ በጎም ሆነ መጥፎ ሚዛናዊና አስተማሪ በሆነ መልኩ ስለማያቀርብ ህዝብ ያደናግራል፣ ያልሆነም ፐርሰፕሽን ይፈጥርል። በመሪነት ላይ የተቀመጡትንም ወደ ሌላ አደገኛ ዝንባሌ/ቴንደሲ እንዲያመሩ የሚገፋፋ ይመስለኛል፣ ወደ ፐርሰናሊቲ ከልት ይወስዳል ነው ስጋቴ።
በመሰረቱ ኢንሳ የወያኔ ጨቋኝና አፋኝ ስርአት መሳሪያ (instrument of oppression and repression) ሆኖ ያገለገለ ተቋም እንደነበር ግልጽ ነው። ኢሳትንና ሌሎች ሚዲያዎችን ጃም በማድረግ፣ ስልኮችን በመጥለፍ፣ የተቋዋሚው መሪዎችና ጋዜጠኖችን ኢሜል በመስበር የአፈና ተግባሩን ሲያከናውን የነበረው ይህ ተቋም ነበር። እንደሚታወቀውና በአለም አቀፍ ጋዜጦች ጭምር እንደወጣው የኢንሳ የኢሜል ጠለፋ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ኢላማ እንዱ እኔ ነበርኩኝ። ሀቁና መነሻ ይህ ከሆነ በዋና መሪነት ላይ የነበሩ ሃላፊዎች በዚያ ተቋም ለተሰራው አፈና ተጠያቂ ናቸው ማለት ነው። ኢንሳ እንደማንኛውም ሀገራዊ ተቋም ለሀገር ደህነነትና ጸጥታ የሚረዱ በጎ ጎኖች ያሉት ሀገራዊ ተቋም ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በውቅቱና በተግባር የአፋኙ ስርአት ህዝብን ለማፈን ከሚያገለግሉት ዋነኛ የአፈና መሳሪያዎች/ተቋማት አንዱ እንደነበር የሚካድ ሊሆን አይችልም።
በነገራችን ላይ ኢንሳን በሚመልከት ከተቋሙ ለቆ የወጣው ሙያተኛ በጋዜጠኛ አበበ ገላው በድምጽ የተቀረጸውን እኔም አዳምጬው ነበር። በወቅቱ ለትግሉ የሚጠቅሙን በርካታ መረጃ አግኝተንበትም ነበር። ለሁማን ራይትስ ሰዎች እንዲያወጡት የጠየቅናቸው ከአበበ ጋር ተመካክረን፣ ኢሜሉንም ለፈረንጆቹ የላክነው በጋራ ነበር፡፡ አመቱ በፈረንጆች 2013 እኔ ደግሞ የኢሳት ዋና ሰራ አስፈጻሚ በነበርኩበት ወቅት መሆኑ ነው።
ዛሬ የአማራኛውን ቃለ ምልልስ የድምጽ ቅጂ አውጥቼ ሰማሁት። እንዲሁም ሁማን ራትንስ ዋች በፕሮፊሽናል ተርጓሚ ያሰተረጎመውንና የላከልንን ጥሬ እንግሊዘኛ ቅጂ አነበብኩት። ዶ/ር አብይን በሚመልከት በየተቋሙ ማለትም በኢንሳ ዋናው ሰው “co-director” “most powerful person፣ “ከኢሳያስ ቶላ” ጋር፣ ስለትምህርት፣ በስራ ላይ ስለነበሩ ባህሪዎች፣ የማኔጅመንት ስታይል፣ ወዘተ ከማንሳት የዘለሉ መረጃዎች የሉትም ። ስለኢንሳ የአፈና፣ የጠለፋ መሳሪያዎች አይነት፣ ስለተግባራቱ፣ መሳሪያዎቹ አቅምና ከየትኞች ሀገሮች እንደሚገዙ፣ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ወዘተ ይዘረዝራል።
የሆነ ሆኖ ቁም ነገሩና የከነከነኝ ጉዳይ በዚያ ስርአት ለተደረገውና የኢንሳም እንደ አንድ ተቋም የአፈናው አጋዥ ሃይል ሆና ላገለገለው የወያኔ ስርአት ለሰራቸው መጠነ ሰፊ ወንጀሎች ጠ/ሚኒስትሩ ዶ/ር አብይ በይፋና በተደጋጋሚ ይቅርታ የጠየቀበት ስለሆነ፣ ይህን ተቋም ነጥሎ ጥሩ ስራ እንደተሰራ ማቅረብ (በዘጋቢው ፊልም እንደቀረበው) ወይንም ተቋሙ የአፋኙ ስርአት የአፈና አካል እንዳልነበር አድርጎ የማቅረብ የሚመስል ትረካ እንደሀገርና ህዝብ ላሳለፍነው የመከራ ጌዜና ለምንገኝበት የለውጥ ሁኔታ ጠቃሚ ነው ብዮ አላምንም።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለውጡን በሚመለክት በጣም ሚዛናዊና መሬት በረገጠ ምልከታው ዛሬ እንዳስቀመጠው በአንድ አመት ውስጥ በርካታና በጎ የለውጥ እርምጃዎች በሀገራችን በኢትዮጵያ አይተናል። በእነዚህ ብቻ እንኳን ቢገመገም ዶ/ር አብይ የሚመራው ለውጥ ትልቅ ስኬት ለሀገራችንና ለአህጉሩም (በተለይ ከኤርትራ ጋር የተፈጠረው ሰላም) አምጥቶአል። በአንጻፉ በሀገራችን ላይ ያንዣንበቡ ስጋቶችና አደጋዎች መኖራቸውና ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ሁላችንም የምንስተው አይመስለኝም።
ማስታወሻ፥ ኢንሳ የጥቃቱ ኢላማ እንዱ እኔ እንደነበርኩኝ በዊኪሊክ የወጣው ከዚህ በታች ይገኛል። ዛሬ በእስር የሚገኘውና ዘጋቤው ፊልም ላይ የሚታየው የኢንሳው ም/ዳይሬክተር የህወአቱ ኮ/ል ቢኒያም ከጣልያኑ የስለላ ሶፍትዊሬ ኩባንያ ከሃኪንግ ቲም ጋር የተመላለሰው።

ቸር ይግጠመን

Filed in: Amharic