>

ጠ/ሚ ኣቢይ ከኣሜሪካዉ መስራች ጆርጅ ዋሽንግተን በአዎንታዊ፤ ከጎርባቼብ ደግሞ በኣሉታዊ ሊማሩ የሚገባቸዉ - የተራ ዜጋ ምክር (ኢንጅነር ሰሎሞን ገብረስላሴ)

ጠ/ሚ ኣቢይ ከኣሜሪካዉ መስራች ጆርጅ ዋሽንግተን በአዎንታዊ፤ ከጎርባቼብ ደግሞ በኣሉታዊ ሊማሩ የሚገባቸዉ – የተራ ዜጋ ምክር

 

ኢንጅነር ሰሎሞን ገብረስላሴ

 

የጠ/ሚ አቢይን የአንድ አመት መታሰብያ በንዲህ አይነት የጥርጣሬና የጥያቄ መንፈስ ይከበራል ብሎ የገመተ ብዙ ሰዉ አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆን ይሆናል፡ ፡

በዴሞክራሲያዊ ጎዳና የጀመሩ አገሮች ሁሉ የሄዱበት መንገድ ስለሆነ ብዙ አግራሞት ሊፈጥር አይገባ ይሆናል፡ ፡ ከሁሉም አገሮች በተለይ የግሪክና የሮማ የጥንት ዲሞክራሲን አልፈን፤ በዘመነ አብርሆት አዉሮጳ የመጣዉን ዲሞክራሲና ስልጣኔ አልፈን፤በተሳካ ሁኔታ የስልጣን ክፍፍልን ተግባራዊ አድርጋ ከ 200 አመት በላይ የዘለቀን ዴሞክራሲ ለአለም ያስተዋወቀችዉ አሜሪካ ናት፡ ፡ ለዚህ በረከት ታላቁ ድርሻ የመጀመሪያ መሪዋ የጆርጅ ዋሽንግተን ነዉ፡ ፡ ዋሽንግተን በተፈጥሮ ቁጥብ፤ችሎታ ያላቸዉን አማካሪዎች በቶሎ የሚረዱና የሚሰበስቡ፤ ለጊዜያዊ ሳይሆን በረጅሙ የአሜሪካን የወደፊት የሚያዩ መሪ በመሆናቸዉ ይሄዉ ዛሬ አሜሪካ ዜጎቹዋን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ጨምራ የምትታደግ አገር ለመሆን በቅታለች፡ ፡

በርግጥ ጆርጅ ዋሽንግተን በጦር ሜዳ ዉሎ የክፍለአለማዊ ጦር የሚባለዉን ከብሪቴይን ቅኝ አገዛዝ አሜሪካን ያላቀቀዉን ጦር መሪ ስለነበሩ በዚህ ችሎታቸዉም የተመረጡና የተመሰገኑ መሪ ነበሩ፡ ፡ በድጋሚ የጦሩ መሪ የመሆን ፍላጎታቸዉን ወደ ጎን ትተዉ ምክር ቤቱ ኢንዲሾም ሲያሳስቡ ታላቅነታችዉን ያሳዩ ሰዉ ነበሩ፡ ፡ በተከታይነትም ፌዴራሊስት የተባሉት ከ60 በላይ ጥሁፎች በታወቁ ያሜሪካ መሪዎች መቅረባቸዉ ላገሪቱ የስልጣን ክፍፍልና ህገመንግስታዊ ስርኣት መሰረት ሆነዉ ዘልቀዋል፡ ከ 10 አመታት በሁዋላ የፈነዳዉ የፈረንሳይ አብዮት በተቃራኒዉ ተቁዋማዊና ሰላማዊ ሳይሆንከአሜሪካዉ ባለመማር ቀዉስ በቀዉስ ሆኑዋል፡ ፡

በሌላ በኩል ጎርባቼብ ሰባዊነታቸዉ ከጠ/ሚ አቢይ ጋር ቢያመሳስላቸዉም፤ አክራሪ ብሄርተኞች ሶብዬት ህብረትን ወደፊትና ወደ ሁዋላ ሲጎትቱ፤ የህግ የበላይነትን ባስቼኩዋይ ማስከበር ሲገባቸዉ ሲያመነቱና ዳ ሲሉ፤ አገራቸዉ ፈርሶ ያለ አገር መሪ ሆነዉ በባዶ የቀሩ ሰዉ ለመሆን በቅተዋል፡ ፡ የህግ የበላይነትን ማስከበር ከዴሞክራሲ ጋር ባልተጣረሰ መልኩ ሊተገበር መቻሉን በበርካታ ምሳሌዎች ማሳየት ይቻላል፡ ፡

ላሉብን ችግሮች ሁሉ ዋነኛ ምንጩ ህገመንግስቱና የክልሎች አወቃቀር መሆኑ ታዉቆ፤ በዚህም ዙሪያ ያገሪቱ ልሂቃን የተለያየ አመለካከት ማሳየታቸዉ ታዉቆ፤ የጠ/ሚ ዋነኛ የዉይይት አጀንዳ መሆን ሲገባዉ በቅደም ተከተል ተራ ወደ ታች ተገፍቶ፤ አሁን ላለንበት የፖለቲካ ቀዉስ ያንበሳዉን ድርሻ ይዙዋል፡ ፡

የዉይይቱ ህግና የጨዋታዉ ዳራ በተቻለ መጠን በመግባባት ለመፍታት፤ የተራራቁ ሃሳቦችን ደግሞ በጉልበት ሳይሆን በሰለጠነ መንገድ በህዝበ ዉሳኔ ከተፈቱ ብዙዎችን ችግሮች መቅረፍ ይቻላል፡ ፡ አለበለዚያ ዳር ዳሩን ምርጫ በ 10 ወር ዉስጥ፤ ህዝብ ቆጠራ በቅርቡ ወዘተ መባሉ ከቀጠለ፤ ጋሪዉና ፈረሱ ቦታቸዉን ቀይረዉ፤ አገራችንም በመታመስ ትቀጥላለች፡ ፡ ይህ ለማንኛችንም አይበጅም፡ ፡

Filed in: Amharic